Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጫት ወይንስ ቻት (chat)???


by Sadat Kemal Abu Nuh

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ፈለጋቸውን ሁሉ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ሸይጧን ጠላታችን እንደሆነ እና ጠላት አድርገን እንድንይዘው አዟል፡፡ ነገር ግን እኛ የአላህን ምክር ችላ ብለን፤ የሸይጧን መጫወቻ እየሆን ይገኛል፡፡
የአላህ ባሪያ ሆይ! ፈጅር ሰላትን በሰዓቱ ላለመስገድ ምንድን ነው ሰበብ የሆነህ??? ጫት ወይንስ ቻት (chat)???
የትኛውም ይሁን ሁለቱንም ተጠንቀቃቸው፡፡ አላህ የሰውን ልጅ ሲፈጥረው ደካማ አድርጎ ፈጠረው፡፡ ቀን ሲሰራ ውሎ ሌሊቱን ማረፍ ግዴታ እንዲሆንበት አድርጎ ፈጠረው፡፡ አላርፍም ቢል እንኳን እንቅልፍ ጥሎት ይሄዳል፡፡ ይህ የማይካድ እውነታ ከሆነ፤ አንድ ሰው ቀን ሲሰራ ውሎ ከዛም ማታ ጫት ሲቅም ካመሸ፤ ሰው ነው እና የሆነ ሰዓት ላይ ይደክማል፤ ከዛም እንቅልፍ ጥሎት ይሄዳል፡፡ አላህ ሰላትን ግዴታ አድርጎት ሲያበቃ፤ ያውም ለወንድ ልጅ በጀመዓ፤ ስንቶች ጫት ቅመው እያመሹ ሱቢህ ሰላት ሲያመልጣቸው ይታያል፡፡ አደለም በጀመዓ መስጂድ ውስጥ ሊሰግዱት፤ ቤታቸውም በሰዓቱ ተነስተው መስገድ እያቃታቸው ነው፡፡ ጫትን ዱዓ ልናደርግበት ነው ብለው የሚገምቱ ይኖራሉ፤ አትሳሳቱ አላህን በትክክለኛ መንፈስ እንጂ የምናመልከው እንደ ጫት አይነቱን አእምሮ የሚቀይር አደንዛዥ እፅ በመጠቀም አይደለም፡፡ ስለዚህ እራሳችንን ከጫት እንጠብቅ፡፡
በመቀጠል፤- ቻት (chat)??? ሸይጧን ከዘመን ዘመን ዘዴዎቹን በመቀየር የሰው ልጆችን ከአላህ መንገድ ሲያወጣ ይታያል፡፡ አሁን አሁን facebook and social medias ብዙ ሰው እየተጠቀማቸው ይገኛል፡፡ ሁሉን ነገር ስንጠቀም ግን አላህ በፈቀደው እና ልክ ባስቀመጠለት መንገድ ብቻ መሆን አለበት፡፡ ሰው ቀኑን ሙሉ ስራ ሰርቶ፤ ከዛ ማታ ማረፍ ሲገባው፤ ስንቶች ቻት (chat)??? ወይንም ፖስት እያነበብን ነው፤ ወይንም ፖስት እያደረግን ነው በሚል በጣም አምሽተው እንቅልፍ ጥሏቸው ይተኛሉ፡፡ ልብ በሉ እኔ ማንሳት የፈለግኩት ዲናዊ ለሆነ ነገር facebook and social medias የሚጠቀሙትን ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሰው ናቸው እና ይህን ተግባር የሚፈፅም ሰው፤ ታላቁን የፈጅር ሰላት አልጋው ላይ ተኝቶ ያሳልፈዋል፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሁሉ ነገር ፍሬ ይኖረው ዘንድ በእውቀት የታገዘ መሆን ግድ ይላል፡፡ ጫትን ሙሉ በሙሉ መራቅ ግድ ሲል፤ ቻት (chat) ግን ሰዓት እና ወቅቱን ማወቅ ግድ ይላል፡፡
አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በሃዲሰል ቁድሲ ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ወደ እኔ ለመቃረብ፤ ለባሪያዬ ከግዴታ ትዕዛዛት የበለጠ የለም….›› ሰላት ግዴታ ነው፤ ፈጅር ሰላት ደግሞ ታላቋ ሰላት ናት፤ ወንድ ልጅ ደግሞ የአላህ ቤት መስጌድ ሄዶ መስገድ በእርሱ ላይ ዋጂብ ነው፡፡
ይህን ትምህርት ላልሰማ ሁሉ እንዲያስተላልፉ በአላህ ስም ይጠየቃሉ፡፡ ፍጡራን ከአላህ ጋር ያላቸው ግንኙነት ሲስተካከል፤ ሁኔታቸው ሁሉ ይስተካከላል፡፡ ከነፍሴ ጀምሮ ሁላችንም እራሳችንን እናስተካክል፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ፈለጋቸውን ሁሉ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
የአላህ ባሪያ ሆይ! ፈጅር ሰላትን በሰዓቱ ላለመስገድ ምንድን ነው ሰበብ የሆነህ??? ጫት ወይንስ ቻት (chat)???የትኛውም ይሁን ሁለቱንም ተጠንቀቃቸው፡፡ አላህ የሰውን ልጅ ሲፈጥረው ደካማ አድርጎ ፈጠረው፡፡ ቀን ሲሰራ ውሎ ሌሊቱን ማረፍ ግዴታ እንዲሆንበት አድርጎ ፈጠረው፡፡ አላርፍም ቢል እንኳን እንቅልፍ ጥሎት ይሄዳል፡፡ ይህ የማይካድ እውነታ ከሆነ፤ አንድ ሰው ቀን ሲሰራ ውሎ ከዛም ማታ ጫት ሲቅም ካመሸ፤ ሰው ነው እና የሆነ ሰዓት ላይ ይደክማል፤ ከዛም እንቅልፍ ጥሎት ይሄዳል፡፡ አላህ ሰላትን ግዴታ አድርጎት ሲያበቃ፤ ያውም ለወንድ ልጅ በጀመዓ፤ ስንቶች ጫት ቅመው እያመሹ ሱቢህ ሰላት ሲያመልጣቸው ይታያል፡፡ አደለም በጀመዓ መስጂድ ውስጥ ሊሰግዱት፤ ቤታቸውም በሰዓቱ ተነስተው መስገድ እያቃታቸው ነው፡፡ ጫትን ዱዓ ልናደርግበት ነው ብለው የሚገምቱ ይኖራሉ፤ አትሳሳቱ አላህን በትክክለኛ መንፈስ እንጂ የምናመልከው እንደ ጫት አይነቱን አእምሮ የሚቀይር አደንዛዥ እፅ በመጠቀም አይደለም፡፡ ስለዚህ እራሳችንን ከጫት እንጠብቅ፡፡በመቀጠል፤- ቻት (chat)??? ሸይጧን ከዘመን ዘመን ዘዴዎቹን በመቀየር የሰው ልጆችን ከአላህ መንገድ ሲያወጣ ይታያል፡፡ አሁን አሁን facebook and social medias ብዙ ሰው እየተጠቀማቸው ይገኛል፡፡ ሁሉን ነገር ስንጠቀም ግን አላህ በፈቀደው እና ልክ ባስቀመጠለት መንገድ ብቻ መሆን አለበት፡፡ ሰው ቀኑን ሙሉ ስራ ሰርቶ፤ ከዛ ማታ ማረፍ ሲገባው፤ ስንቶች ቻት (chat)??? ወይንም ፖስት እያነበብን ነው፤ ወይንም ፖስት እያደረግን ነው በሚል በጣም አምሽተው እንቅልፍ ጥሏቸው ይተኛሉ፡፡ ልብ በሉ እኔ ማንሳት የፈለግኩት ዲናዊ ለሆነ ነገር facebook and social medias የሚጠቀሙትን ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሰው ናቸው እና ይህን ተግባር የሚፈፅም ሰው፤ ታላቁን የፈጅር ሰላት አልጋው ላይ ተኝቶ ያሳልፈዋል፡፡የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሁሉ ነገር ፍሬ ይኖረው ዘንድ በእውቀት የታገዘ መሆን ግድ ይላል፡፡ ጫትን ሙሉ በሙሉ መራቅ ግድ ሲል፤ ቻት (chat) ግን ሰዓት እና ወቅቱን ማወቅ ግድ ይላል፡፡አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በሃዲሰል ቁድሲ ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ወደ እኔ ለመቃረብ፤ ለባሪያዬ ከግዴታ ትዕዛዛት የበለጠ የለም….›› ሰላት ግዴታ ነው፤ ፈጅር ሰላት ደግሞ ታላቋ ሰላት ናት፤ ወንድ ልጅ ደግሞ የአላህ ቤት መስጌድ ሄዶ መስገድ በእርሱ ላይ ዋጂብ ነው፡፡ይህን ትምህርት ላልሰማ ሁሉ እንዲያስተላልፉ በአላህ ስም ይጠየቃሉ፡፡ ፍጡራን ከአላህ ጋር ያላቸው ግንኙነት ሲስተካከል፤ ሁኔታቸው ሁሉ ይስተካከላል፡፡ ከነፍሴ ጀምሮ ሁላችንም እራሳችንን እናስተካክል፡፡የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ፈለጋቸውን ሁሉ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡