Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹ጎሽቶ›› ፤ ‹‹ሶማ ሶማ›› የአልከሶ ሙሪዶች ድንበር ሲያልፉ

ከላይ ያነበባችኋቸው ቃላት የአልከሶ ተከታዮች ወይንም ሙሪድ በመባል የሚታወቁት የሚሉዋቸው ናቸው፡፡ ምን ስላሉ ነው ድንበር አለፉ ያልናቸው???
==)‹‹ጎሽቶ›› ማለት ጌቶች ማለት ነው ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ ‹‹ጌታ›› የሚለውን ቃል ከአላህ ውጭ ለማንም እንዳንጠቀመው ከልክለዋል፡፡ ‹‹ጌታ››፤ ‹‹ጌቶች›› የሚሉትን ቃላት በአረብኛም፤ በአማርኛም፤ በሌላም ቋንቋ ከአላህ ውጭ ለፍጡራን ማዋል አይቻልም፡፡ ነብያችን እንኳን ‹‹አብድ (ባርያ)›› ናቸው፡፡

==)‹‹ሶማ ሶማ››፤ ሌላኛው ድንበር ማለፋቸው ደግሞ የአልከሶ ሸይኽ ትክክለኛ ስማቸው ‹‹በሽር›› ነው፤ የአልከሶ ሙሪዶች ዘንድ ልጃቸውን በሽር ብሎ ስም ማውጣትም ይሁን የአልከሶን ሸህ በሽር ብሎ መጥራት እንደ ክብር መንካት ስለሚቆጥሩት፤ ቁርዐን እየቀሩ ‹‹በሺረን ወነዚረን›› የሚለው ጋር ሲደርሱ ‹‹በሺረን›› የሚለውን ‹‹ሶማ (ሞክሼ)›› ብለውት ያልፋሉ፡፡ የሚገርመው ሰዎች በነብያት ስም እየተጠሩ፤ የአልከሶ ሸህ ስምን ማንሳት ያውም ‹‹በሽር›› የሚለውን ‹‹ሶማ›› ብሎ ማለፍ ምን ይባላል???

ለወገን ደራሽ ወገን ነው፤ ህዝባችንን ከምንም ነገር በፊት ከሽርክ እንዲቆጠብ እናስተምር፤ የአላህ እርዳታ የሚገኘው ተውሂድን በመያዝ እና ሽርክን በማጥፋት ነው፡፡ ወገኖች ቢያውቁ ኖሮ፡፡ አላህ ያሳውቀን፡፡