Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ታርዳ የተገደለችው ሴት

by Sadat Kemal Abu Nuh

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ በሆነው፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያችን፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና የነብያችን እና የሰሃባዎች ፈለግ ላይ እስከቂያማ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ 
ከሽርክ እራሳችንን እንጠብቅ፡፡ ልብ ብሎ ላየው ለተመለከተው፤ የአላህ መልክተኛ የተነበዩት እውነት ሆኖ እየታየ ይገኛል፡፡ የአላህ መልክተኛ ‹‹ዘምን ይመጣል እውነተኛው ውሸተኛ፤ ውሸተኛው እውነተኛ የሚባልበት›› እንዲሁም የአላህ መልክተኛ ‹‹ከንግግርም ድግምት አለ›› ይሉናል፡፡ በአላህ ፈቃድ ማንሳት የፈለግኩት አርዕስት ሰውች ዘንድ ‹‹ወልይ›› በመባል የሚታወቅ፤ ነገር ግን ሴት ልጅ አርዶ ስለገደለው አብዲ በይዲ ይሆናል፡፡

1) አብዲ በይዲ ማን ነው???
አብዲ በይዲ ተከታዬቹ ዘንድ ‹‹ወልይ ነው››፤ ‹‹እሳት ላይ ይቆማል››፤ እና የመሳሰለውን የሚሉለት ነው እውነታው ግን የሚከተለው ይሆናል፡፡
የእርሱ ተከታይ ከነበሩ እና አላህ ተውበት ከወፈቃቸው ወንድሞች አንዱ ስለ አብዲ በይዲ ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡ 2 ሊትር ውስኪ ይጠጣል ያለ በረዶ አይሰክርም፡፡
ይህ አላህ ተውበት የወፈቀው ወጣት ሲነግረኝ እነዲህ ይላል ‹‹ጫት እየቃምን በተቀመጥንበት፤ አንድ ሃብታም ሴት መጣች፤ ከዛም እዛ የተሰበሰቡት እንዲህ ሲሉ አጫወቱን ‹እቺ ሴት ቻንሰኛ የሆነችው እና ቡና ላኪ ባል ያገኘችው፤ እናቷ በልጃገረድነቷ አብዲ እንዲባርካት ስላደረገቻት ነው› ተባልን›› ይላል፡፡ መባረክ ብለው የሚጠሩት ዝሙትን መሆኑን አትርሱ ውድ አንባቢያን፡፡ ይህ ሰው ነው ‹‹ወልይ›› ተብሎ የሚጠራው
2) ይህች የዚህ ፅሁፍ መነሻ የሆነችዋ ሴት፤ ለዚህ ሰይጣን አምላኪ፤ ‹‹ጀባታ›› ብላ በግ እርድ ይዛለት ሄደች፤ እሱ ግን እሷን አርዶ ገደላት፡፡ በአሁን ሰዓት እስር ቤት ውስጥ ይገኛል፡፡
3) አገራችን ላይ ብዙ ሴቶች ዱዓ አድራጊ ቤት ሄደናል እያሉ፤ ተደፍረው የሚመጡ፤ ‹‹ሩሃኒያዩ ፈልጎሽ›› ነው እየተባለ ዝሙት እየተሰራ፤ ሽርክ እየተስፋፋ ይታያል፡፡ ታድያ ለምን ይሆን ዝም የሚባለው፡፡
4) ይህ ወንጀል የተፈፀመው እሩቅ ሳይሆን እዚሁ አዲስ አበባ፤ መሳለሚያ አካባቢ መሆኑ፡፡ በጣም የሚገርመው ስንት ወደ እስልምና ዳዕዋ እናደርጋለን የሚሉ ሰዎች ይህን ጉድ ሰምተው ዝም ማለታቸው፡፡ ለምን ይሆን ዝም የሚሉት????
5) ነብያት ሁሉ (አለይሂሙሰላም) ህዝቦቻቸውን ‹አላህን በብቸኝነት አምልኩ፤ ሽርክን ራቁ ያሉ ሲሆኑ ነው አላህ ለህዝቦቻቸው የላኳቸው፡፡ ለምን ይሆን ስለ ሽርክ ሲወራ፤ አላህ በብቸኝነት ይመለክ ሲባል ብዙዎች የሚከፋቸው????
6) ለኡማው መጨነቅ ማለት ምን ማለት ነው???? ስንቶች ናቸው አላህ ያዘነላቸው ጥቂት የአላህ ባሪያዎች ሲቀር አብዛኞች ተውሂድን ችላ ብለውታል፡፡
7)እውነት እንደዚህ አይነት ወንጀሎች፤ ሽርክ፤ ቢድዐ፤ ሰሃባዎችን መስደብ እና መተቸት አላም ላይም ይሁን ኢትዬጵያ ላይ እያየን፤ አላህ ይረዳናል ብለን እንገምታለን???? ይህ ከባድ የሆነ ሞኝነት ነው፡፡ አለም ቢሰበሰብ፤ አለም ቢጮህ፤ ተውሂ እና ሱና ሳይዙ፤ ሽርክ እና ቢድዐና ሳይቃወሙ ሳያጠፉ ድል የለም፡፡
 ሰሃቦችን የአላህን ውዴታ፤ እና ለድል ያበቃቸው ተውሂድ እና ሱናን በመያዛቸው፤ ሽርክ እና ቢድዐን በመቃወማቸው እና በመታገላቸው ነው፡፡ የሰሃባዎች ታሪክ እና ተሞክሮ ለኛ ምሳሌ ካልሆነ፤ ለማን ሊሆን ነው????
9) ሽርክ ማለት ሰዎችን ዱንያ ላይ የሚያዋርድ፤ ቀብር ላይ ከባድ ቅጣት የሚያስቀጣ፤ አኸይራ ላይ አሳማሚዋን ጀሃነም የሚያስገባ ተግባር ነው፡፡ አላህ ይጠብቀንና፡፡ ታድያ የሽርክ እውነታው ለምን ይሆን አብዛኞች ዝም የሚሉት ???
10) ከሽርክ እና ቢድዐ የሚያስጠነቅቁ፤ ወደ ተውሂድ እና ሱና የሚጣሩ ወንድም እና እህቶች ናቸው እውነት ለኡማው አሳቢ፡፡ በመጥፎ ሊጠረጠሩ አይገባም፡፡ ማንም ያለውን ቢል፤ ፍርድ ሰጪው አላህ ነው፡፡
11) እስከ ቂያማ ድረስ እስልምና የበላይ ይሆናል፡፡ እስልምናን ሰሃባዎች በተረዱት መንገድ የተረዱ፤ የተገበሩ የበላይ እንደሆኑ ይቀጥላሉ፡፡ ሽርክ ላይ፤ ቢድዐ ላይ፤ ወንጀል ላይ የተዘፈቁ፤ ሌላው ሲዘፈቅ እያዩ ዝም የሚሉት የበታች እንደሆኑ ይሞታል፤ የሚቀጥለውም አለም ላይ ውርደትን እንጂ ሌላን አይጠብቃቸውም፡፡ የበላይ የሆነውን እስልምና በሽርክ ለመለወስ ሲሞከር እያዩ ዝም ማለት ምን ይባላል????

አላህ ወደ ተውሂድ፤ ሱና እና ወደ ሰሃባዎች መንገድ ይመልሰን፡፡ አላሁመ አሚን
አላህ በሽርክ እና ቢድዐ ከማይደራደሩ፤ ሽርክ እና ቢድዐን ከሚጠሉ ተውልዶች ያድርገን፡፡ አላሁመ አሚን፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በአበል ቃሲም፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና እስከቂያማ ድረስ እውነትን በተከተሉ ላይ ይሁን፡፡

1) አብዲ በይዲ ማን ነው???አብዲ በይዲ ተከታዬቹ ዘንድ ‹‹ወልይ ነው››፤ ‹‹እሳት ላይ ይቆማል››፤ እና የመሳሰለውን የሚሉለት ነው እውነታው ግን የሚከተለው ይሆናል፡፡የእርሱ ተከታይ ከነበሩ እና አላህ ተውበት ከወፈቃቸው ወንድሞች አንዱ ስለ አብዲ በይዲ ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡ 2 ሊትር ውስኪ ይጠጣል ያለ በረዶ አይሰክርም፡፡ ይህ አላህ ተውበት የወፈቀው ወጣት ሲነግረኝ እነዲህ ይላል ‹‹ጫት እየቃምን በተቀመጥንበት፤ አንድ ሃብታም ሴት መጣች፤ ከዛም እዛ የተሰበሰቡት እንዲህ ሲሉ አጫወቱን ‹እቺ ሴት ቻንሰኛ የሆነችው እና ቡና ላኪ ባል ያገኘችው፤ እናቷ በልጃገረድነቷ አብዲ እንዲባርካት ስላደረገቻት ነው› ተባልን›› ይላል፡፡ መባረክ ብለው የሚጠሩት ዝሙትን መሆኑን አትርሱ ውድ አንባቢያን፡፡ ይህ ሰው ነው ‹‹ወልይ›› ተብሎ የሚጠራው2) ይህች የዚህ ፅሁፍ መነሻ የሆነችዋ ሴት፤ ለዚህ ሰይጣን አምላኪ፤ ‹‹ጀባታ›› ብላ በግ እርድ ይዛለት ሄደች፤ እሱ ግን እሷን አርዶ ገደላት፡፡ በአሁን ሰዓት እስር ቤት ውስጥ ይገኛል፡፡ 3) አገራችን ላይ ብዙ ሴቶች ዱዓ አድራጊ ቤት ሄደናል እያሉ፤ ተደፍረው የሚመጡ፤ ‹‹ሩሃኒያዩ ፈልጎሽ›› ነው እየተባለ ዝሙት እየተሰራ፤ ሽርክ እየተስፋፋ ይታያል፡፡ ታድያ ለምን ይሆን ዝም የሚባለው፡፡4) ይህ ወንጀል የተፈፀመው እሩቅ ሳይሆን እዚሁ አዲስ አበባ፤ መሳለሚያ አካባቢ መሆኑ፡፡ በጣም የሚገርመው ስንት ወደ እስልምና ዳዕዋ እናደርጋለን የሚሉ ሰዎች ይህን ጉድ ሰምተው ዝም ማለታቸው፡፡ ለምን ይሆን ዝም የሚሉት????5) ነብያት ሁሉ (አለይሂሙሰላም) ህዝቦቻቸውን ‹አላህን በብቸኝነት አምልኩ፤ ሽርክን ራቁ ያሉ ሲሆኑ ነው አላህ ለህዝቦቻቸው የላኳቸው፡፡ ለምን ይሆን ስለ ሽርክ ሲወራ፤ አላህ በብቸኝነት ይመለክ ሲባል ብዙዎች የሚከፋቸው????6) ለኡማው መጨነቅ ማለት ምን ማለት ነው???? ስንቶች ናቸው አላህ ያዘነላቸው ጥቂት የአላህ ባሪያዎች ሲቀር አብዛኞች ተውሂድን ችላ ብለውታል፡፡ 7)እውነት እንደዚህ አይነት ወንጀሎች፤ ሽርክ፤ ቢድዐ፤ ሰሃባዎችን መስደብ እና መተቸት አላም ላይም ይሁን ኢትዬጵያ ላይ እያየን፤ አላህ ይረዳናል ብለን እንገምታለን???? ይህ ከባድ የሆነ ሞኝነት ነው፡፡ አለም ቢሰበሰብ፤ አለም ቢጮህ፤ ተውሂ እና ሱና ሳይዙ፤ ሽርክ እና ቢድዐና ሳይቃወሙ ሳያጠፉ ድል የለም፡፡