Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነብያችን እና ሰለፎች ስለ ኡስማን ኢብን አፋን

ነብያችን እና ሰለፎች ስለ ኡስማን ኢብን አፋን

by Sadat Kemal Abu Nuh
ነብያችን እና ሰለፎች ስለ ኡስማን ኢብን አፋን
ኡስማን የጀነት ነው
አንድ ቀን ቤት ውስጥ በተቀመጡበት ታፋቸው ተገልፆ ነበር፤ አቡበክር ገባ አልሸፈኑትም፤ ኡመር ገባ አልሸፈኑትም፤ ኡስማን ገባ ሸፈኑት ተጠየቁ ለምን እንዳደረጉ፤ እሳቸውም እንዲህ አሉ ‹‹ኢስማንን አደለም በምድር ያለ በሰማይ ላይ ያለ መላኢካ
ያፍረዋል››
ነብያችን ለኡስማን 2 ሴት ልጃቸውን መዳራቸው ቅፅል ስሙም ‹‹ዙኑረይን›› የሁለቱ ኑሮች ባለቤት፤ አንዷን ድረውት ስትሞት ሌላኛዋን ሰጡት፡፡ አንድ ነብይ ሁለት ሴት ልጁን ሲሰጥ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ አይታወቅም፡፡ እንዲያውም ሶስተኛ ቢኖረን እንደግምህ ነበር ብለውታል ይባላል
በነብያችን አንደበት ኡስማን ኢብን አፋን የተቡክ ዘመቻን ሲወጡ 100 ግመል በመስጠቱ የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹ኡስማን የሰራውን ቢሰራ ከዚህ በኋላ አይጎዳውም››
የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ ‹‹ትናንት ማታ መልካም ሰው ታየ (በህልም) እናም አቡበክር ከአላህ መልክተኛ ጋር፤ኡመር ከአቡበክር ጋር እና ኡስማን ከኡመር ጋር የተያያዙ ናቸው›› ጀሪር ኢብን አብዲላህ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልክተኛን ተለይተን ስንሄድ እንዲህ አልንመልካሙ ሰው የአላህ መልክተኛ ናቸው፤ አንዱ ባንዱ መተሳሰራቸው አላህ መልክተኛውን በላከበት ጉዳይ ላይ ሀላፊ ይሆናሉ›› (ሱነን አቢ ዳውድ 2/513)
ኡስማን ስልጣን ላይ ሲወጣ አብደላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ አለ ‹‹ከቀሩት ውስጥ ምርጣችንን ነው የመረጥነው፤ ምርጣችንንም በመምረጥ ላይም አልተሳሳትንም›› (አጠበቃት አል ኩብራ 3/63)
የአላህ መልክተኛ ከአቡበክርን፤ከኡመርን እና ከኡስማን ጋር እሁድ ተራራ ላይ በወጡበት እሁድ ተንቀጠቀጠች የአላህ መልክተኛው በእግራቸው በታ አደረጓትና እንዲህ አሉ ‹‹የያዝሽው እኮ ነብይ፤ ሲዲቅ እና ሸሂዶች ነው››፡፡ ሲዲቁ አቡበክር ሲሆን ሸሄዶች ኡመርና ኡስማን ናቸው
ኡስማን ያለ አግባብ እንደሚገደል የአላህ መልክተኛ ተናግረዋል፡፡ አብደላህ ኢብን ኡመር እንዲህ ይላል የአላህ መልክተኛ ‹‹ፊትና እንደሚመጣና እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ ከዚያም ፊቱን የተሸፈነው ሰው በግፍ ይገደላል አሉ›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ 2/115
ከዐብ ኢብን ኡጅራ እንዲህ ይሉናል፤ የአላህ መልክተኛ ፊትና እንደሚመጣና ወዲያውም እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ አንድ ጭንቅላቱን የተሸፈነ ሰው አለፈ የአላህ መልክተኛም ‹‹ያን ቀን ይህ ሰው ሀቅ ላይ ነው›› እየሮጥኩ ሄጄ የኡስማንን እጅ ይዤ ወደ አላህ መልክተኛ አዞርኩና ‹‹ይህ ሰው›› ብዮ ጠየኳቸው አሳቸውም ‹‹አዎን እሱ›› አሉኝ፡፡ (ሰሂህ ሱነን ኢብን ማጃህ 1/24 (111))
የምእመናን እናት አኢሻ (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ ትላለች የአላህ መልክተኛ ኡስማንን አስጠርተው አዋሩት …… የመጨረሻ ንግግራቸው ጀርባውን ይዘው እንዲህ አሉት ‹‹ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል (ስልጣንን) ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ፡፡ ጥያቄ ሰይድ ቁጡብ የት ነው ያለው የአላህ መልክተኛን ቃል በመቃወም ላይ ‹‹በእስልምና እይታ ላየው፤ መፈንቅለ መንግስቱ በአጠቃላይ የእስልምና መንፈስ ነበረው›› የሙናፊቆች ግድያ እንዴት እስላማዊ መንፈስ ይኖረዋል?
ኢብን ኡመር (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በነበሩበት ወቅት በሰዎች መሃል እናበላልጥ ነበር፤ አቡበክርን ከዛ ኡመርን ከዛ ኡስማንን እንመርጥ ነበር›› ኡማሙ ቡኸሪ.