Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተፈጥሮ ግዴታ ፅዳቶች


ይህን ፈፃሚ አላህ ሰዎችን በፈጠረበት ውበት ከመገኘቱ አንፃር ሱነኑል ፊጥራ (ተፈጥሯዊ ሱና) በመባል ይታወቃል::ይህ ተግባር የተወደደ የሆነበት ምክንያት በሚያምርና በተዋበ ሁኔታ እንዲገኙ ሲባል ነው፡፡ አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:-
“ አምስት ነገሮች ተፈጥሯዊ ፅዳቶች ናቸው፡ 1የብልትን ፀጉር ማፅዳት፣ መገረዝ፣ ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፣ የብብትን ፀጉር መንጨትና ጥፍርን መቁረጥ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
1. ግርዛትለወንድ ግዴታ ሲሆን ለሴት ደግሞ ሱና ነው:: ወንድ መገረዝ ያለበት የወሸላው ሽፋን ከሚይዘው ነጃሳ ለመፅዳት ሲሆን ሴት ደግሞ የስሜቷን ግለት ስለሚያበርድ ነው፡፡ህፃን በተወለደ በሰባተኛው ቀን ቢገረዝ ቶሎ ለመዳንና በተሟላ ሁኔታ ለማደግ ስለሚረዳው የተወደደ ነው፡፡2. ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፡የውበት፣ የንፅህናና ከሃዲያንን የመለየት መገለጫ በመሆኑ የተወደደ ተግባር ነው፡፡ ቀድሞ ቀመስን እንዲያጥርና ፂምን እንዲቀቅ እንክብካቤ እንዲቸረው የሚያነሳሱ ብዙ ሀዲሶች ተዘግበዋል፡፡ፂምን መልቀቅና መንከባከብ የውበትና የወንድነት መገለጫ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ብዙ ቀድሞ ቀመስን በማሳደግና ፂምን በመላጭ ወይም በማሳጠር ይህን ነቢያዊ ትዕዛዝ ሲቃረኑ ይስተዋላል:: ይህ ተግባር የነብዩን መመሪያና ትዕዛዛቸውን መጣስ በመሆኑ ጥንቃቄ ያሸዋል::በዚህ ርዕስ ከተዘገቡ ሀዲሶች ውስጥ አቡ ሑረይራ ከነቢዩ ያስተላለፉት ሀዲስ ይጠቀሳል፡-“ቀድሞ ቀመስን አሳጥሩ ፂማችሁን ደግሞ ልቀቁ መጁሶችን ተቃረኑ” (ሙስሊም ዘግበውታል)
ማንኛውም ሙስሊም ይህን የነብዩ (ﷺ) መመሪያ አጥብቆ በመያዝ ኢ-ኢስላምን መለየትና ሴትንም አለመመሳሰል ይገባዋል፡፡
3. ጥፍርን መቁረጥ፡-የውበት መገለጫና ቆሻሻንም ማስወገጃ ሲሆን ነገር ግን አንዳንድ ሙስሊሞች ይህን የነብዩ (ﷺ) መመሪያ በመቃረን ጥፍራቸውን ወይም ደግሞ የተወሰነ ጣት ጥፍርን በማሳደግ ይህን ነቢያዊ መመሪያ ይቃረናሉ:: ይህ ተግባር የሸይጧን ማታለያና የአላህን ጠላቶች በጭፍን መከተል ነው፡፡
4. የብብትን ፀጉር መንጨት ወይም በመላጨት ማፅዳት፡-በመጠራቀሙ ምክንያት የሚፈጠረውን ጠረን ያስወግዳል፡፡ ይህ የጠራ ዲናችን ይህን በመሰለ ውበትና ፅዳት የሚያዘን ሙስሊሞች በመልካም ሁኔታ እንዲገኙና በዲናቸው የበላይነት ተሰምቷቸው ከሀዲያንና መሃይማንን እንዲርቁ እንዲሁም አላህን በመታዘዝና የነብዩን መመሪያ በመከተል አላህን እንዲያመልኩ ነው፡፡
ኢንሻአላህ በቀጣዩ ትምህርታችን ላይ በሌላ የነብዩ (ﷺ) አስተምህሮት ላይ በተጨማሪ “ተፈጥሯዊ ፅዳቶች” ተብለው የመጡትን ይዘን እንቀርባለን:: 
የዛሬ ከትምህርቱ የወጣ ጥያቄ
ከተፈጥሯዊ ፅዳቶች መካከል ቢያንስ ሁለቱን ጥቀስ/ሽ? 
ዓላማችን የፊቅህ ትምህርትን ቀለል ባለ አቀራረብ ማስተማር ነው:: 
join us on www.facebook.com/easyfiqh