Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥሩ የመፋቂያ አይነት

       ጥሩ የመፋቂያ አይነት 

እርጥብ የማይፈታተልና የማያቆስል እንጨት ቢሆን ይመረጣል፡፡
“ነብዩ በአራክ እንጨት ይፍቁ ነበር፡፡”
መፋቂያውን በቀኝም ይሁን በግራ እጁ ይዞ መፋቅ ችግር የለውም፡፡ ውዱእ በሚያደርግ ሰዓት መፋቂያ ከሌለው ዓሊይ ስለነብዩ ውዱእ አደራረግ በዘገቡት መልኩ በጣት መፋቅ ይቻላል፡፡
የመፋቂያ ጥቅሞች
ከወሳኝ ጥቅሞቹ ውስጥ ከላይ ባሳለፍነው ሀዲስ የተጠቀሰው ለአፍ ፅዳትና አላህንም ማስወደጃ መሆኑ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:-
“መፋቂያ አፍን የሚያፀዳና አላህንም የሚያስወድድ ነው፡፡”(ቡኻሪ ዘግበውታል) 
ስለዚህ ጥቅሙ የላቀ በመሆኑ አንድ ሙስሊም ግለሰብ ይህን ሱና ቸል ሳይል ሊከታተለው ይገባል፡፡አንዳንድ ሙስሊሞች ወር ሁለት ወር የሚያህል ረዥም ጊዜ ባለማወቅ ወይም በቸልተኝነት ጥርሳቸውን ሳይፍቁ የሚቆዩበት ሁኔታ አለ፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው ነብዩ (ﷺ) የሚንከባከቡትን ሱና በመተዉ ከፍተኛ ምንዳና ብዙ ጥቅሞች ያመልጠዋል፡፡ነብዩ ህዝቦችን ማስቸገር ይሆንብኛል ብለው እንጂ በግዴታ መልክ ሊያዙት ነበር፡፡ መፋቂያ ከላይ ከተገለፁ ጥቅሞች ውጭም ብዙ ተነግሮለታል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ጥርስንና ድድን ማጠናከሩ፣ ድምፅን ማጥራቱና ሰውዬውን ማነቃቃቱ ይጠቀሳሉ፡፡አላህ የነብዩ (ﷺ) ሱናህ በአግባቡ መከተልን እንዲያገራልን እንለምነዋለን !!!
ከትምህርቱ የወጣ ጥያቄከመፋቂያ ጥቅሞች መካከል ቢያንስ አንዱን ጥቀስ/ሽ?ዓላማችን የፊቅህ ትምህርትን ቀለል ባለ አቀራረብ ማስተማር ነው:: 
join us on www.facebook.com/easyfiqh