Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መፋቂያ

www.facebook.com/easyfiqh
የመፋቂያ ሸሪዓዊ ድንጋጌ
መፋቂያ መጠቀም በየትኛውም ወቅት ሱና (የተወደደ) ነው፡፡ ፆመኛም ጠዋትም ይሁን ከቀትር በኋላ ጥርሱን ቢፍቅ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ጥርስን በመፋቅ ሲያነሳሱ አንዱን ወቅት ከሌላው አልለዩም፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:-“መፋቂያ አፍን የሚያፀዳና አላህንም የሚያስወድድ ነው፡፡”(ቡኻሪ ዘግበውታል) 
እንዲህም ብለዋል:-
“ለህዝቦቼ ማስቸገር ባይሆንብኝ ለእያንዳንዱ ሰላት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ይበልጥ የሚወደድበት ወቅትመፋቂያን መጠቀም በተለይ በነዚህ ወቅቶች ላይ ይበልጥ የተወደደ ነው፡፡ ውዱእ በሚደረግበት ጊዜ፣ ከእንቅልፍ ሲነቃ፣ የአፍ ጠረን ሲለወጥ፣ቁርአን ለመቅራት ሲባል፣ ሰላት ለመስገድ፣ መስጂድ ሲገባና ቤት ሲገባ፡፡ 
ለዚህ ማስረጃው ሚቅዳም ኢብኑ ሹረይህ እንዳስተላለፈው አባቱ ነብዩ (ﷺ) ቤት ሲገቡ በምን እንደሚጀምሩ ዓኢሻን ጠይቋቸው ሲመልሱ “ጥርሳቸውን በመፋቅ፡፡” ብለዋል:: (ሙስሊም ዘግበውታል)
ለረዥም ሰዓት በዝምታ ሲቆይና ጥርስ ሲበልዝም ይበልጥ ይወደዳል፡፡ 
“ነብዩ(ﷺ) ሌሊት ሲነሱ አፋቸውን በመፋቂያ ያፀዱ ነበር”(ሙስሊም ዘግበውታል) 
በጌታው አምልኮ ሲሆንና ወደርሱ ሲቃረብ በፀዳና ባማረ ሁኔታ መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
አላህ በትምህርቱ የምንጠቀምና እየተረሳ ያለውን የጠበቀ የነብዩ (ﷺ) ሱናህ የምንተገብር ያድርገን !!! አምባቢ ብቻ ሳይሆን ተሳታፊም ይሆኑ ዘንድ መፋቂያ (ሲዋክ) መጠቀም ከሚወደድባቸው ወቅቶች መካከል comment ላይ ቢያንስ አንዱን ይጥቀሱ:: ዓላማችን የፊቅህ ትምህርትን ቀለል ባለ አቀራረብ ማስተማር ነው::