Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጊዜ በኢስላም ያለው ቦታ


By Ilyas Awel 
 የተለያዩ የማህረሰብ ክፍሎች የጊዜን ጥቅም ለማጉላት የተለያዩ አባባሎችን ከተለያዩ ውድ ቁሳቁሶች ጋር በማዛመድ ለመግለጽ ሞክረዋል::ሙስሊሞች ጋር ግን ጊዜ በቁሳቁስ አይለካም፡፡ሙስሊሞች ዘንድ ጊዜ ትልቅ ቦታ ነው ያለው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-“የሁለት ፀጋዎችን ዋጋ አብዛኛው ሰው አያውቃቸውም እነዚህም ጤናናጊዜ ናቸው”::
 ሐሰነል በስሪ እዲህ ይላሉ፡-
“የአደም ልጅ ሆይ! ህይወትህ የቀናቶች ስብስብ ነው፣ አንድ ቀን ባለፈ ቁጥር ከህይወትህ የተወሰነው ክፍል ያልፋል፣ከህይወትህ የተወሰነው ክፍል ካለፈ በስተመጨረሻ ህይወትህ እንዲያልፍ ያደርጋል” ብለው ነበር::
 ታላቁ ሰሀቢይ ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) እንደተናገሩት፡-
’’ፀሐይ ወጥቶ ጥሩ ስራዎቼ ሳይጨምሩ እንዳለፈች ቀን፣ በህይወቴ እነዲህ አይነት ፀፀት ተሰምቶኝ አያውቅም’’ ይሉ ነበር

 እብነል ጀውዚ  ለልጃቸው እነዲህ ሲሉ ምክር አስተላልፈዋል፣
“ልጄ ሆይ! ጥንቅቅ ሁን በከንቱ ላሳለፍከው ጊዜ ተፀፀት፣ ጊዜ እስካለህ ድረስ እምነትህን ለመሙላት ጥረት አድርግ”
“ልጄ ሆይ! ጥሩ ነገራትን ለመስራት ከዚህ በፊት በከንቱ ያሳለፍካቸውን ጊዜአት አስታውስ ፣ ይህ ማስታወስህ ጥሩ ነገሮችን ለመስራት ይረዳሀልና “
“ልጄ ሆይ! እያንዳንዱ ቀን የሰዓታት ጥርቅም ነው፣ እያንዳንዱ እስትንፋስ ደግሞ ሀብት ነው፣ ስለዚህ ባያንዳንዱ እስትንፋስ ጥሩ ነገሮችን ስራበት፣ አለበለዚያ በትንሳዔ ቀን ካዝናህ ባዶ ይሆናል”::
ኢብነልጀውዚ በመጨረሻ ለልጃቸው የሰጡት ምክር “ልጄ ሆይ! ዱኒያ ላይ የሳለፍከው ስልሳ ዓመት ስታሰላው በሚከተለው መነገድ መሆኑን ትገነዘባለህ፣
Ø      ሀያ ዓመታትን በእንቅልፍ
Ø      አስራአምስት ዓመታትን በህፃንነት
Ø      አብዛኛው ቀረው ከፍል ባለማዊ ደስታ
Ø      እንዲሁም የዒባዳውን ጊዜ ደግሞ በኩራትና በቸልተኝነት ናቸው፣ እስኪ ልጄ ከዚህ  በሗላ ስለ ዘላለማዊ ህይወትህ አስብ! ይህ የሚወሰነው እዚህ ዱኒያ ላይ በምታሳልፈው የሰዐታት ህይወት ነው” ብለው ነበር::
         እዚህ ላይ መጠየቅ ያለብን እኛስ ምን ያህል ኖረናል? ምንያህል ጊዜስ በዒባዳ አሳልፈናል?
ከሁሉም በላይ ማወቅ ያለብን ዕድሜአችን በጨመረ ቁጥር ወደሞት እያመራን መሆናችንን ነው::
አላህ በጊዜያችን የምንጠቀም ሰዎች ያድርገን፡፡አሚን!!!