Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በሱና መርከብ እንሳፈር


በሱና መርከብ እንሳፈር
Ø  በሱና ላይ መጠናከር አዳዲስና መጤ ከሆኑ አመለካከቶችና አምልኮዎች እራስን ማላቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በዲን ዉስጥ አዲስ መጤ ነገር ሁለ ቢድዓ ነዉ፡፡ ቢድዓ ደግሞ የተወገዘ ነዉ፡፡ መልዕክተኛዉ እንዲህ ብለዋሌ ‹‹በዚህ በጉዳያችን (በዲናችን) ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ (ስራው) ተመላሽ ነው።›› ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡ በሌላ ተመሳሳይ ሀዲስ ፡- ‹‹ትዕዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ (ስራው) ተመላሽ ነው።›› ሙስሊም ከዓኢሻ ዘግበውታል፡፡
Ø  ኢስሊም የተሟላ በመሆኑ ምንም አይነት ጭማሪን አይቀበልም፡፡የተላለፈልንን ሱና ብቻ ብንተገብር ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ ታላቁ ሰሀቢይ ኢብን መስዑድ አንዱህ ብለዋሌ፡- "ተከተሉቢድዓንም አትፍጠሩሱና በቂያችሁ ነውና!!" ፡፡ ሁዘይፋ ኢብኑል የማን ደግሞ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የመልዕክተኛው ሰሃቦች ባልሰሩት ማንኛውም የዒባዳ ተግባር አምልኮን አትፈፅሙ! የመጀመሪያዎቹ ለመጨረሻዎቹ ምንም የተዉት ነገር የለም!›› አቡ ዳዉድና ሌሎች ዘግበውታል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ‹ምንም እንኳ ቢድዓ ቢሆን ጥሩ ስለሆነ ቢድአቱል ሀሰናህ ነዉ› ይላሉ፡፡ ለዚህ ምላሹ ተከታዩ የዓብደላህ ኢብን  ዑመር ንግግር ነዉ፡፡ ‹‹ሁሉም የቢድዓ ተግባር ጥመት ነው! ሰዎች መልካም አድርገው ቢያዩት እነኳ!›› ኢብኑበጣናህና አል-ካኢይና ሌሎችም በትክክለኛ ሰነድ ዘግበውታል::
አል-ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹አንድ ሰዉ፤ በኢስላም ውስጥ አዲስ ነገርን ፈጥሮ ያ ፈጠራ ጥሩ መስሎ ከታየው ነቢዩ መልእክታቸውን አጓድለዋል ብል ጠርጥሯል፤ ያኔ ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን አይሆንም!›› ፡፡
ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች! ለብዙ ሰዎች ሱናን ተግብሮ ሱኒይ መሆንን ከባድ የሚያደርገዉ ለመጤ አመለካከቶችና ተግባሮች ልባቸዉን መስጠታቸዉ ነዉ፡፡ እያንዳንዱ ሙስሊም አላህን በመፍራት ሀቅን ሊከተል ይገባዋል፡፡ አቡበከር ኢብኑ-ዒያሽ ‹ሱኒይ ማን ነዉ?› ተብለዉ ሲጠየቁ ‹የፈጠራ መንገድች ሲጠቀሱለት ምንም ወገንተኝነት የማያሳይ ነዉ› ኪታብ አሸሪዓ ሊልአጁሪይ ቁጥር 2058
Ø   አል- ኢማም ማሊክ ኢብኑ አነስ እንዱህ ብለዋል፡- ‹‹ሱና የኑህ መርከብ ናት! የተሳፈረባት ይድናል! ወደኋላ የቀረ ይሰጥማል!›› ሚፍታሁልጀናህ 46
ሱናን አዉቀን በመተግበር ሁላችንም በኑህ መርከብ እንሳፈር!!!በሱና መርከብ እንሳፈር