Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰርጎን በዲጄ??? ወይንስ በመንዙማ ባንዶች??? ወይንስ ሸሪዐ ባሳየው መልኩ???


አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ነብዩ ((ﷺ)) የላከበት ዲን ተጨማሪም ቅናሽም የማይፈልግ ዘመን የማይሽረው ለማንኛውም ዘምን እስከ ቂያማ (እለተ ትንሳኤ) ድረስ ለሚመጡ ጉዳዬች ነብያችን……. አብራርተው አሳይተዋል፡፡
ሰርግ እንዴት መምሰል እንዳለበት ምርጡ ነብይ ተናግረዋል፤ በተግባርም ሰርተው አሳይተዋል፡፡ ሙስሊሞች ሙስሊም ካሰኛቸው ነገር ውስጥ በዲናቸው ወይንም በረሱል ((ﷺ)) ሱና በማንኛውም ዘመን ሳያፍሩ፤ ሳይቀይሩ፤ ሳይጨምሩ እና ሳይቀንሱ በቻሉት መጠን ለመተግበር እሺ ብለው እጅ መስጠታቸው ነው፡፡
ሰርግ ቤቶች ላይም ይሁን በማንኛውም አይነት መንገድ ከተጠሉ እና ከተከለከሉ ነገሮች ውስጥ ‹‹ኢኽቲላጥ›› ወይንም ‹‹አጅነቢ ወንድ እና ሴት መቀላቀል ነው›› ዛሬ ዛሬ ይህ ወንጀል የተለመደ ነገር ሆኗል፡፡ ሰርግ ላይ ዘመዳማቾች አብረው ሰርግ ላይ ‹‹እስክስታ መባባል›› አለባቸው ‹‹ወገቡ ይታይለት፤ ወገቧ›› ይታይላት ይባላል፡፡ ለዚህም ሲሉ አንዳንድ እራሳቸውን ‹‹ዘመናዊ ሙስሊሞች›› ብለው የሚጠሩ ‹‹ባንድ ወይንም ዲጄ›› የሚባለውን ሰርግ ላይ በመጥራት ወንድ እና ሴትን አስደብልቀው፤ ዳንስ እና እስክስታ ሲጨፍሩ ይታያል፡፡
ስለ ሙዚቃ መሳሪያ==========ነብያችን ((ﷺ)) ሙዚቃ መሳሪያን ከልክለዋል ((ﷺ)) እንዲህም ሲሉ ‹‹ከእኔ ኡመቶች ሰዎች ይመጣ (ለወንድ) ሃር መልበስን፤ ዝሙትን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ ሰዎች›› ብለው ኮንነዋቸዋል፡፡ ሃዲሱን ኢማሙ ቡኻሪ ሰሂሃቸው ላይ ዘግበውታል፡፡
ሌሎች እንዲህ ሲሉ ዲኑ ያስቀመጠውን ትተው የራሳቸውን አስተያየት ሰጡ‹‹ባንድ እና ዲጄ ከማምጣት፤ መንዙማ እና ሃድራ ባዬች ይሻላሉ›› አሁን አሁን በየሰርጉ የተለመደ ‹‹ድቤ›› የያዙ የተለያዩ ቡድኖች ያን ድቤ እየመቱ ወንዶች ተሰብስበው ‹‹እያጨበጨቡ፤ ዘለል ዘለል›› እያሉ የሚያነሷቸው ስንኞች ላይም ‹‹ሽርክ›› ጭምር የሚደባለቅበት ሁኔታ አለ፡፡በጣም የሚገርመው ‹‹ሰለዋት›› ኢባዳ ነው፤ ‹‹ሰለዋት›› በማለት ወደ አላህ የምንቃረብበት፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚጠሩት ‹‹1500-3000 ብር›› ተከፍሏቸው ነው፡፡ ለምን ይሆን ዲኑን የሚነግዱበት???
እሺ ኢስላም ስለ ሰርግ ምን ይላል???==================1) ሰርግ ላይ የሚጨፍሩት ሴቶች ናቸው፤ እሱም ‹‹ደፍ›› የሚባል መሳሪያ አለ፤ እሱን ብቻ ተጠቅመው ድንበር ማለፍ የሌለበትን ግጥም እየገጠሙ፤ ወንድ ሳይሰማቸው መጨፈር ይችላሉ፡፡2) ወንድ እና ሴት አንድ ላይ በፍፁም ሊደባለቁ አይገባም ያለ መጋረጃ፤ ወይንም የተለያየ ክፍል በማስቀመጥ ቢሆን እንጂ፡፡ አንድ አንድ ቦታ አላህ ይጠብቀን፤ ባል እና ሚስት መድረክ ተሰርቶላቸው ሰው ሁሉ ያያቸዋል፡፡ ነብዩ ((ﷺ)) ‹‹ደዩስ ጀነት አይገባም›› ብለዋል፡፡ ደዩስ ማለት ‹‹በሚስቱ፤ በእህቱ፤ በናቱ፤ በልጁ እንደው በአማኝ ሴቶች የማይቀና›› ጀነት አይገባም፡፡ እንዴት ሰው ሚስቱን እንደምትሸጥ እቃ ለሰው ሁሉ ያሳያታል??? 3) ወንድ ልጅ አያጨበጭብም፡፡ ማጨብጨብ የሴት ነው፡፡ ነብያችን((ﷺ)) እንዳሉት4) ነብዩ ((ﷺ)) እንዲህ ይላሉ ‹‹ከምግብ ሁሉ መጥፎ ምግብ፤ የሰርግ ቤት ምግብ ነው፡፡ (ምግቡን) የሚፈልገው ሰው ይከለከላል፤ የማይፈልገው ሰው ይጠራል›› 
ሸሪዐው ጭፈራን ለሴቶች ብቻ ነው የፈቀደው፤ ያውም በ ‹‹ደፍ›› ብቻ፤ ድንበር ማለፍ የሌለበት ግጥም እየገጠሙ፤ ወንዶች ሳይሰሟቸው፡፡ ሰለዋት ነው እየተባለ ወንድ እና ሴትን ቀላቅሎ አላህን ማስቆጣት ይቅር፡፡
ዘመናዊነት ለሚሉ ሰዎች ‹‹ከኢስላም የበለጠ ዘመናዊነት አለን???›› አላህ ነብዩ ((ﷺ)) የላከበት ዲን ዘመን የማይሽረው በየትኛውም ወቅት እና ቦታ፤ ለየትኛውም አይነት ማህበረሰብ የበላይነቱ የነብዩን ((ﷺ)) ሱና፤ ፋና፤ መንገድ መከተሉ ነው፡፡የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሁላችንም ከራሳችን ጀምረን፤ ቤተሰቦቻችንን፤ እና ዘመዶቻችንን የሱናን ዉበት ልናሳይ ይገባል፡፡ ስለዚህ ‹‹ዲጄም ይሁን የድቤ ባንድ›› የሚባል ነገር በኢስላም የለም፤ ኢስላም የደነገገውን ከላይ ተጠቅሷል፡፡
አላህ ሆይ! ሃቁን አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፤ ባጢልንም አሳየን የምንርቀው አድርገን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በአላህ መልክተኞች ላይ ሁሉ ይሁን፡፡By Sadat Kemal Abu Nuh