Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ይነበብ ፤ ተነቦ ይተግበር


بسم الله الرحمن الرحيم-----------------------------------በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ፈለጋቸውን በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም አሉ:- "እኔ ለእናንተ የምፈራላቹ ትንሹን ሽርክ ነው"ሰሀቦች ጠየቁ..:- "ያ ረሱሉላህ ! ምንድን ነው ትንሹ ሽርክ?"ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም አሉ:- "ሪያዕ (እዩልኝ፤ስሙልኝ) ነው" አሉ
አብዱላህ ኢብን ሙባረክ እንዲህ ይላሉ:- "ኢብኑ ሀሪስ እንዲህ ይሉኝ ነበር 'ዝናን ተጠንቀቅ! ያገኘሁዋቸው ሰሀቦች ሁሉም ያስጠነቅቁኝ ነበር' " (ኣስ ሲያር 7/260)
አቡ አሊይ እንዲህ ይላሉ "ሁሉም የነቢዩ ሰለላሁአለይሂወሰለም ሶሀቦች እንዲህ ይሉኝ ነበር ስራክን ለአላህ ብቻ ብለክ እንጂ አትስራ ያለበልዚያ ለሰራክለት ነገር አላህ ይተውካል" (አል ሙሰናፍ 7/207)
ሙሀመድ ኢብነል ቃሲም እንዲህ ይላሉ "ሙሀመድ ኢብን አስለምን ከሀያ ዓመታት በላይ አብሬው ቆይቻለው በቆይታችን አንድም ቀን ከሰላት ብኍላ ያለውን ሱና ሰላት ከጁምዓ ቀናት ውጪ መስጂድ ውስጥ ሲሰግድ አይቼው አላውቅም እንዲህ ሲል ሰምቼዋለው 'ወላሂ ብችል ከሁለቱ መላዒከዎቼ ተደብቄ ብሰግድ እመርጥ ነበር ለእዩልኝ እንዳይሆንብኝ እፈራለው' ዘወትር ከሰላት በኍላ ወደ ቤቱ በመሄድ በሩን ይዘጋና ይቀመጥ ነበር በአላህ ይሁንብኝ አንድም ቀን ምን እንደሚሰራ አላውቅም ነበር አንድ ቀን ልጁ እንዲህ ሲል ባልሰማው 'አባዬ ሁሌ ከሰላት ብኍላ ወደ ቤት በመሄድ በሩን ዘግቶ ያልቅሳል ነገር ግን ሁሌም ወደ ውጪ ሲወጣ እንዳለቀሰ እንዳያስታውቅበት ፊቱን ታጥቦ ክሁል ተቀብቶ ይወጣ ነበር ለምስኪኖች ልብስ እየገዛ ያከፋፍላል ነገር ግን መልዕክተኛውን ልብሱን እንዲያከፋፍል ሲልከው እኔ እንደላኩክ ማንም እንዳያውቅ ይለው ነበር" (ኣስ ሲያር 12/201)
ሁርሙላህ እንዲህ ይላሉ :- "ኢማሙ ሻዕፊ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለው 'ባገኘሁት እውቀትና ለሰዎች ባስተማርኩት ከ አላህ ምንዳን እሻለው ነገር ግን ሰዎች ባያሞግሱኝ እመርጣለው' " (ኣስ ሲያር 10/55)
ፉድይል ኢብኑ ኢያድ እንዲህ ይላሉ :- "ማንም ሰው ብቸኛ ሲሆን ካስጠላውና ከከፋው ነገር ግን ሰዎች ሲያካብቡት ደስተኛ ከሆነ ከ ሪያዕ (እዩልኝ) አልፀዳም" (ኣስ ሲያር 8/436)
በሽር ኢብኑ ሀሪስ እንዲህ ይሉ ነበር "አላህ ሆይ! በሰዎች ዝንድ ገናና አድርገክ የቂያማ ቀን ከምታዋርደኝ ዝናን ከኔ አርቀው"(አዝ ዝ ሁድ አል በያቂ :147)
አቡ ሀዚም እንዲህ ይላሉ:- "ጥሩ መጥፎ ስራክን እንደምትደብቀው ጥሩ ስራክንም እንደዚያው ደብቅ (አል ሙሰነፍ 7/195)
አቂል ኢብን ሙዋቂል እንዲህ ይላሉ:- "ከሙናፊቅ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ብቸኛ ሲሆን ይሳነፋል ሰዎችን ሲያይ ብርታትን ያገኛል። ከምቀኝነት ምልክቶች ውስጥ ደግሞ በዝነኝነቱ የሚደሰት ነው"(አል ሂልያህ: 4/47)
አብዱሰመድ አብዱልዋሪስ እንዲህ ይላሉ "ሀውሻብ 'ስሜ መስጂደ ጃሚ ደረሰ?' እያለ ያለቅሱ ነበር"
በሽር ኢብኑ ሀሪስ እንዲህ ይላሉ:- " ዝናን የሚወድ አላህን አይወድም "እንዲህም ይሉ ነበር:- "ስምክ እንዲጠራ አት ስራ መጥፎ ስራክን እንደምትደብቀው ጥሩ ስራክንም ደብቅ" (ሲያር10/476)
ፉደይል ኢብኑ ኢያድ እንዲህ ይላሉ:- "ማንም ዝናን የሚሻ አይሳካለትም ማንም ዝናን የማይፈልግ ሳይፈልገው (ያገኘዋል" አል ሲያር 8/432)
ሱፍያን አጠወሪ እንዲህ ይላሉ:- "ደኅንነት የሚኖርክ መታወቅ ሳትፈልግ ስትቀር ነው" (አስ ሲያር: 7/257)
ዳውድ ኢብን አቡ ሂንድ ለአርባ ዓመታት ያክል ሲፆሙ ቤተሰቦቻቸው አያውቁም ነበር ጠዋት ሲወጡ ምግብ ይዘው ይወጡና መንገድ ላይ ለምስኪን ይሰጡታል ማታ ቤት ሲመለሱ ከቤተሰባቸው ጋር እራት ሲበሉ ያፈጥሩ ነበር (ህኢልያተል አውሊያእ3/94).
ሃማድ ኢብኑ ዘይድ እንዲህ ይላሉ "አዩብ ሁሌም አንዲት ሀዲስ ሲነበብላቸው እየተንቀጠቀጡ ያልቅሱ ነበር ከዚያም እንዳይታወቅባቸው አፍንጫቸውን እያሻሹ በርድዋቸው በማስመሰል 'ይሄ ብርድ' ይሉ ነበር" (ሙሰነድ ኢብን ጂያድ (1246)) (ሲያር ኢልያመል ኑቡላ6/20).
አብደላህ ኢብን መብሩክ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው:- "አቡ አስ ሳሊህ ሁሌ ሀዲስ ባነበቡ ቁጥር ያለቅሱ ነበር ከዚያም ላለማሳወቅ የሚስቁ ያስመስሉ ነበር" (አል ኢኽላህ ወኒያ)
አል አማሽ እንዲህ ይላሉ:- "አብድረህማን ኢብን አቢ ለይላህ ሁሌም በሰላት ያሳልፉ ነበር ሰው ቤታቸው መጥቶ በራቸውን ሲያንኳኳ ከእንቅልፋቸው የተነሱ ያስመስሉ ነበር" (አስ ሲያር 4/264).-------------------------አላህ ልክ እንደ ሰለፎቻችን ለስራችን ኢኽላስ ይለግሰንአሚንwww.facebook.com/selefoch