Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድ ተጠልቶ.........

by Berekah Ummu Ayemen
ተውሒድ ተጠልቶ............ ስለተውሂድ ሲነገር ሊመረን ሊያነገሸግሸን ይችላል መነገሩ ግን ግድ ስለሆነ
ሁሌም ይነገራል ፡፡ ምክኒያቱም አንዱን ትቶ አንዱን አንጠልጥሎ ስለማይሆን ያም ማለት ‹‹ነስር ተፈልጎ ተውሒድ ተጠልቶ ስለማይሆን›››
መሰረቱ ተዘንግቶ አንገብጋቢው ጉዳይ ተረስቶ ነገር ግን ሰዎች በሌሎች አንገብጋቢ ናቸው በሚሉዋቸው ነገሮች ተጠምደው ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ
ግና የሽርክን አሳሳቢነት ወደ ጎን ችላ ብለው ትተውታል ነብያቶች የተላኩበት አላማ ተረስቱዋል፡፡ ስለሱ ለማስተማር ቀነ ቀጠሮ ተይዞልታል መች
እንደሆነ ግን በውል አይታወቅም ብቻ በቀጠሮ ላይ ነው ይህም ማለት ሞት በነሱ ላይ መች እነደሚመጣ ያውቁታል ይገርማል ሞትን እኮ የቅርብ
አማካሪያቸው አርገውታል፡፡ ግና ታላቁ ነብይ መሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተውሒድን ለማስተማር ቀጠሮ አልያዙም የድሎት ወቅት
እስኪመጣ አልጠበቁም ስንት ስቃይ እየደረሰባቸው እንኩዋን ተውሒድን ከማስተማር አልተወገዱም ነበር ታዲያ ለ ተውሒድ ትምህርት ቀነ ቀጠሮ
ማያዝ የማን ፈለግ ነው?? የሆነው ሆነ እና በ ሃገራችን ላይ የሚሰሩ ሽርኮች ከ ቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቱዋል ይህ የሚያሳየው
የተውሒድ ትምህርት ለህብረተሰቡ ማስተማር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ነው ፡፡ በ አላህ ላይ ድንበር ሲታለፍ ያልከነከነን የኛ መብት
ሲረገጥ ለምን የወራጨናል ቅድሚያ የሚሰጠው የቱ ነው የፈጣሪ መብት ወይስ የሰው?? በ አላህ ላይ ድነበር ሲታለፍ ዝም ብለን እራሳችንን
በሌሎች ጉዳዮች አስጠምደን ተውሒድን ወደ ጎን ትተን ነገር ግን በየጊዜው ነስር ነስር እያልን እንጮሃለን ሆኖም ለሁሉም ነገር ቅድመ ሁኔታ አለው
ቅድሚያ እሱን አንወቅ ከዛም በ አላህ ፈቃድ ሁሉም ነገር ይስተካከላል ፡፡ ‹‹‹አሁንም ቢሆን መቸም ቢሆን ተውሒድ ተጠልቶ ነስርን መናፈቅ ዘበት ነው ስለዚ የአላህ ባሮች ሆይ በ ተውሒድ ላይ እንበርታ ወደ አላህ አንመለስ ከዛም በ አላህ ፈቃድ ነስር ይመጣል፡፡›››