Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንድነት


በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላት አና ሰላም በመጨረሻው ነብይ በሰው ልጆች ፈርጥ በነብያችን ላይ ይሁን፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና የነሱን ፈለግ እስከቂያማ ድረስ በተከተሉት ላይ ይሁን፡፡ በመቀጠል
1)የሰሃባዎችን አንድነት አስመልክቶ አላህ
እንዲህ ይላል َﻦﯿِﻨِﻣْﺆُﻤْﻟﭑِﺑَو ۦِهِﺮْﺼَﻨِﺑ َكَﺪﱠﻳَأ  ٓىِﺬﱠﻟٱ َﻮُھእርሱ (አላህ) ያ በእርዳታውና በምእምናን (በሰሃባዎች) ያበረታህ ነው፡፡  َﻦْﯿَﺑ  َﻒﱠﻟَأَو
ُﮫَﻨْﯿَﺑ  َﻒﱠﻟَأ َﻪﱠﻠﻟٱ  ﱠﻦِﻜ َٰﻟَو  ْﻢِﮫِﺑﻮُﻠُﻗ  َﻦْﯿَﺑ  َﺖْﻔﱠﻟَأ ﺂﱠﻣ ﺎًﻌﯿِﻤَﺟ ِضْرَ ْﻷٱ ﻰِﻓ ﺎَﻣ  َﺖْﻘَﻔﻧَأ ْﻮَﻟ ۚ  ْﻢِﮫِﺑﻮُﻠُﻗ ٌﻢﯿِﻜَﺣ ٌﺰﻳِﺰَﻋ ۥُﻪﱠﻧِإ ۚ  ْﻢ በልቦቻቸውም መካከል
ያስማማ ነው፡፡ በምድር ያለውን ሁሉ (ሀብት) በለገስክ ኖሮ በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር፡፡ ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ፡፡ እርሱ
አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ አላህ ሰሃባዎችን ለምሳሌ ቢላልን ከሀበሻ፤ ሰልማንን ከፋርስ፤ ሱሀይብን ከሩም፤ ለ100 አመት የተዋጉትን አውስ እና ኸዝረጅ አንድ ያደረጋቸው በተውሂድ እና ሱና ነው፡፡ ተውሂድ እና ሱናን ስላሟሉ፡፡
2)በመቀጠልም ስለ የሁዳዎች አንድነት ሲያወራ እንዲህ ይላል ٰﻰﱠﺘ َﺷ  ْﻢُﮫُﺑﻮُﻠُﻗَو ﺎًﻌﯿِﻤَﺟ  ْﻢُﮫُﺒ َﺴْﺤَﺗ ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲኾኑ የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠረጥራቸዋለህ፡፡
3) የሰው ልጆችን አንድ ሊያደርጋቸው የሚችለው አላህ ብቻ ነው፡፡ አላህ አንድ የሚያደርጋቸው ደግሞ እሱ ያዘዛቸውን ሲተገብሩ፤ በመልክተኛው በኩል ያዘዛቸውንም ሲተገብሩ፤ እሱ የከለከላቸውን እና መልክተኛው የከለከላቸውን ሲከለከሉ ነው፡፡ አለበለዚያ ልቦቻቸውን እንዳይስማማ ያደርገዋል፡፡ አላህ የሰው ልጆችን ልብ ከማያስማማበት ነገር አንዱ ‹‹በጥሩ የማያዙ፤ ከመጥፎ የማይከለክሉ እና ወንጀል ሰሬን ተው ብለው እጁን ካልያዙት፤ አላህ ይረግማቸዋል፤ ልቦቻቸውንም እንዳይስማሙ ያደርጋል›› ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት አማኞችን አስመልክቶ ልቦቻቸውን እንዳስማማ ተናገረ፤ ዩዳዎችን አስመልክቶ ልቦቻቸው የተለያዩ መሆኑን ተናገረ፡፡ ዋና ልብ መባል ያለበት የሰው ልጆችን ልብ አንድ የሚያደርገው አላህ ብቻ ነው፡፡ አላህ አንድ እንዲያደርገን ከተፈለገ፤ ሰሃባዎች እንዳመኑት አምኖ መገኝት በተውሂድ እና ሱና መተሳሰር ከሽርክ፤
ቢድዐ እና አራማጆቹ መራቅ፤ መጠንቀቅ ማስጠንቀቅ፡፡
4) አላህ ኡማዉን አንድ እንዲያደርገው ኡማው ምን ይጠበቅበታል፡፡ አላህ ያዘዘውን መታዘዝ፤ ከትዛዞች ሁሉ ትልቁ ተውሂድ ነው፤ ነብያችን የከለከሉትን መከልከል፤ ነብያችን ከከለከሉት ታላቅ ወንጀል ብለው ከጠሩት ውስጥ ‹‹ሽርክ›› የመጀመሪያው ነው፡፡ ስለዚህ ተውሂድ እና ሱናና መያዝ ከሽርክ እና ቢድዐ እናም ከባለቤቶቹ እና አራማጆቹ መራቅ ይህ ነው አንድነት ፈጣሪው፡፡
5) ነብያችን ከነማን ጋር አንድ ሆኑ ከነማን ጋርስ ተለያዩ ነብያችን ከነቢላል፤ ከነሰልማን፤ከነ ሱሃይብ (ረድየላሁ አንሁም) ከነ ሸሂድ ሀምዛ ጋር አንድ ሲሆኑ ከነ አቡ ለሃብ ጋር ግን ተለያዩ ምንም እንኳን አጎታቸው ቢሆንም፡፡ ከዚህ የምንረዳው ከሽርክ ባለቤቶች ጋር እንመክራቸዋለን፤ እናስተምራቸዋለን እንጂ ‹‹አንድ ነን›› አንልም
6) ሰሃባዎች ከነማን ጋር አንድ ሆኑ ከነማን ጋር ተለያዩ ሰሃባዎች ኸዋሪጆች ሲመጡ አንድ አልሆኑም እንዲያውም ተዋጓቸው፡፡ ቀደርያዎች ከኢራቅ ሲመጡ አብደላህ ኢብን ኡመር እንዳለው ‹‹እኔም ከነሱ አይደለሁም፤ እነሱም ከእኔ አይደሉም›› ነው ያለው፡፡ ሰሃባዎች እንደነ ሀሰን አል በስሪ፤ ቀታዳ፤ ሙጃሚድ፤ ኢክሪማ፤ ሰይድ ሙሰየብ እና የመሳሰሉት ታላላቅ ታብእዬች ሲመጡ፤ አንድ ሆኑ፤ እውቀታቸውንም አስተላለፉላቸው፡፡ ይህ ታላቅ እውነታ ነው፡፡
የሚያሳዝነው ባለንበት ወቅት ታላላቅ ሰሃባዎችን የሚሳደብ ሰው ማጋለጥ (ለህዘበ ሙስሊሙ ማስጠንቀቅ) ‹‹አንድነታችንን ይበትናል›› ያስብላል፡፡ የእኛ አንድነት የተመሰረተው በተውሂድ በሱና ሰሃባዎችን በማክበር እንጂ እንሱን ለሚሰድብ ሰው ጥብቅና በመቆብ አይደለም፡፡
ተውሂድ እና ሱናን ወደ ኋላ ብሎ፤ በጥሩ ሳያዙ ከመጥፎ ሳይከለክሉ፤ በምንም አይነት ሰበብ ቢሆን አላህ አንድ አያደርገንም፡፡ ሺህ አመት ቢለፋም፡፡ አላህ የሱን ዲን ተውሂድ እና ሱናን በመከተል፤ በኸይር በማዘዝ ከመጥፎ በመከልከል የሚረዱትን ነው አንድ የሚያደርገው፡፡ አላህ ወደ እውነተኛው አንድነት ይምራን ከውሸት አንድነት አላህ ይጠብቀን፡፡ አላህ ይህን አድርገው አንድ ከሚያደርጋቸው ያድርገን፡፡ አላሁመ አሚን፡፡