Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢስላምና ሽብር

ሽብር በየትኛውም አገላለፅ ብንመለከተው አደገኛ በሽታ፣ እርኩስ ተግባር፣ ታላቅ አደጋ ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ እርሱም በእያንዳንዱ አገር ውስጥ ራሱን የቻለ አፈፃፁም፣ መንስኤና መፍትሄ አለው፡፡ እንደየሀገሩ ህገ መንግስት፣ ስርአት፣ ባህል፣ እምነት፣ ስነምግባርና ሚዛናዊነት ይለያያል፡፡ኢስላም ሽብርን እንደሚያወግዝ ባሳለፍነው ማብራሪያ ለመጥቀስ ተሞክሯል፡፡ ይህንም የሚያስረዳው አላህ ሱ.ወ በምድር ውስጥ ጥፋት ፈፃሚ ክፍሎች ላይ መወሰድ ያለበትን እርምጃ ሲገልፅ ያስቀመጠው የቅጣት እርምጃ ምሳሌ ያልተገኘለት የትኛውም ፀረ ወንጀል መመሪያና ህግ ያላረቀቀው ሊያረቀውም የማይችለውን የቅጣት እርምጃ ወስኖበት እናገኛለን፡፡ ይህም የወንጀሉን ክፋት ያሳያል፡፡ እንዲህም ሲል ነበር መቅጣጫሉን የጠቀሰው

‹‹የእነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚዋጉ በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚተጉ ሰዎች ቅጣት መገደል ወይም መስቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከአገር መባረር ነው፡፡ ይህ ለእነርሱ በቅርቢቱ አለም ውርደት ነው በመጨረሻይቱም ለእነርሱ ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡›› አል ማኢዳህ 33

ታዲያ ኢስላም የሽብር ምንጭ እንዴት ሊሆን ይችላል? ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡
ግና አንድ ጥያቄ ሊነሳ ይችላላ እርሱም “ሽብር አይቻልም እንዴት ይባላል?አላህ በቁርአን ላይ እንድናሸብር ገልፅ እያለ? ቢባል ሊሰጥ የሚችለው መልስ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

በእርግጥም አላህ ሱ.ወ በቁርአን ላይ እንዲህ ብሏል፡-

‹‹ለእነርሱም ከማንኛውም ሐይልና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ ውጭ ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን (መናፍቃን) የምታሸብሩበት ስትኾኑ አዘጋጁላቸው፡፡›› አል አንፋል 6ዐ
ነገር ግን “የምታሸብሩበት” የሚለውን ቃል ከመነሻው እስከነመድረሻው ካስተዋልን መልዕክቱ ሽብርን እንድንፈፅም የሚገፋፋ ሳይሆን ይልቁንስ ለማጥቃት ወይም ለመተናኮል የሚመጣን ጠላት አደብ ማስያዝ እንደተፈለገበት በትክክል መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህም የተፈለገው ጠላቶቻችሁ እንዳይተናኮሏችሁ ቅድመ ጥንቃቄ በመውሰድ ልዩ ዝግጅት አድርጋችሁ ስጋት፣ ፍርሃትና፣ ሽብር ተሰምቷቸው እንዲታቀቡ ያደርጋቸዋልና፡ ይህ ከሆነ ታዲያ ሽብርን ለማጥፋት አልያም ለመቀነስ ሊወሰድ የሚገባው የመፍትሄ እርምጃ ምን ይሆን? ብዚዎችን ሊያነጋግርና ሊያስጨንቅ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም መፍትሄው ኢስላም ዘንድ ለመሆኑ ምንም አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ይሁንና መፍትሄው ይልቁንም መከላከያው የተስተካከለ እስላማዊውን ግንዛቤ ማስረፅ ሲሆን ይህን ኃላፊነት በትክክል በመወጣቱ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ የሚችሉት አላህ ፈሪ የሆኑ የሰለፊይ ዑለማዎች እንጂ ማንም ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መገሰፅና ለመምራት የሚንደረደሩት የተከበሩና ላቁ ነብያቶች የሰው ልጅ አስተማሪዎች የተንደረደሩበትና የተነሱበት መሰረት ላይ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ መንደርደሪያና መሻ ታዲያ አምላካዊው ራዕይ (ወህይ) ነው፡፡ ልብ ከበሽታው ህያው የሚሆንበት፣ ነፍስን ግራ ከመጋባትና ከመደንበር አውጥቶ የመንፈስ እረፍት የሚሰጥ መሰረት ነውና፡፡ መወሰድ ያለበት እርምጃ መፍትሄ
1.ወጣቶችን ቁርአንና ሐዲስን አጥብቀው እንዲይዙና በማንኛውም ጉዳይ ላይ ወደ እነርሱ እንዲመለሱ መጥራትና ማስተማር፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላልና

‹‹የአላህንም (የማመን) ገመድ ሁላችሁም ያዙ አትለያዩም›› አል ዒምራን 1ዐ3
ቁርአን አጥብቆ መያዝ አደጋ ላየ እንዳይወድቅ አላህ ያዘጋጀልን ጥሩ ምሽግ ነው፡፡
2.ቁርአንና ሐዲስን በመልካም ቀዳሚ አበዎች ግንዛቤ መረጃትን ማስረገጥ ይህም ሊገኝ የሚችለው ሙስሊሞች አላህን ፊሪ የሆኑ ዑለማዎች እጅ ላይ ሲማሩ ብቻ ነው፡፡ አላህም እንዲህ ይላል፡-
‹‹የማታውቁም ብትሆኑ የእውቀት ባለቤቶች ጠይቁ›› አል ነህል 43
እንዲህም ብላልና

‹‹ከፀጥታ ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላችውም ጊዜ እርሱን ያጋንናሉ ወደ መልዕክተኛውና ከእርሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች (ወደ አዋቂዎች) በመወሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር፡፡›› አል ኒሳህ 83

3.የፈተናና የጥፋት ቦታዎችን መራቅ፡፡ ችግሩን ለመራቅና መዘዙን ለመጠንቀቅ ሲባል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

‹‹ከእናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ፡፡›› አል አንፋል 25

ይህም የሚሆነው ከፈተና መጠበቂያ የሆነን መልካም ስራን በመስራት ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ “አንድ ድቅድቅ ጨለማ የሆነን ፈተና በመልካም ስራ ተሽቀዳደሙ (ቅደሙ) ግለሰቡ በእርሷ (በፈተናው) ምክንያት ሙስሊም ሆኖ ያድርና ከሀዲ (ካፊር) ሆኖ ያረፍዳል ሙስሊም ሆኖ ያረፍድና ከሀደ ሆኖ ያመሻል ይኸውም ሃይማኖቱን በዱንያ ሸቀጥ ይለውጣል፡፡”

4.በአምልኮትና አላህን በመፍራት ላይ ትጉህ መሆን ነው፡፡ ከከአደጋ መትረፍ መንገድ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላልና

‹‹አላህን የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጣ ደርግለታል›› አጠላቅ 2

5.ነገሮችን በመቻልና በአስተዋይነት ለመፍታት መሞከር፣ በውሳኔ ላይ አለመቸኮል፣ ከስሚታዊነትና ከግንፈልተኝነት መራቅ፡፡ ይህም የመልዕክተኞችና የቅን ተከታዮቻቸው ፈለግ ነውና፡፡ አላህ ሱ.ወ ስለ ነብዩ ኢብራሂም ዓ.ሰ እንዲህ ብሏልና

“ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ አልቃሻ መላሳ (የወደ አላህ ተፀፃች) ነውና፡፡” ሁድ 75

በጥቅሉ እስላማዊው መፍትሄ ያለው ቁርአንና ሐዲስ ውስጥ ነው፡፡ በንግግርና በምክር ያልተለወጠ በብትር ይለወጣል፡፡ ማህበረሰቡም የራሱን ግንዛቤ በማስተካከል የምፍትሄ እምዳ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡

‹‹የእነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚዋጉ በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚተጉ ሰዎች ቅጣት መገደል ወይም መስቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከአገር መባረር ነው፡፡ ይህ ለእነርሱ በቅርቢቱ አለም ውርደት ነው በመጨረሻይቱም ለእነርሱ ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡›› አል ማኢዳህ 33
ታዲያ ኢስላም የሽብር ምንጭ እንዴት ሊሆን ይችላል? ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ግና አንድ ጥያቄ ሊነሳ ይችላላ እርሱም “ሽብር አይቻልም እንዴት ይባላል?አላህ በቁርአን ላይ እንድናሸብር ገልፅ እያለ? ቢባል ሊሰጥ የሚችለው መልስ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
በእርግጥም አላህ ሱ.ወ በቁርአን ላይ እንዲህ ብሏል፡- 
‹‹ለእነርሱም ከማንኛውም ሐይልና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ ውጭ ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን (መናፍቃን) የምታሸብሩበት ስትኾኑ አዘጋጁላቸው፡፡›› አል አንፋል 6ዐነገር ግን “የምታሸብሩበት” የሚለውን ቃል ከመነሻው እስከነመድረሻው ካስተዋልን መልዕክቱ ሽብርን እንድንፈፅም የሚገፋፋ ሳይሆን ይልቁንስ ለማጥቃት ወይም ለመተናኮል የሚመጣን ጠላት አደብ ማስያዝ እንደተፈለገበት በትክክል መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህም የተፈለገው ጠላቶቻችሁ እንዳይተናኮሏችሁ ቅድመ ጥንቃቄ በመውሰድ ልዩ ዝግጅት አድርጋችሁ ስጋት፣ ፍርሃትና፣ ሽብር ተሰምቷቸው እንዲታቀቡ ያደርጋቸዋልና፡ ይህ ከሆነ ታዲያ ሽብርን ለማጥፋት አልያም ለመቀነስ ሊወሰድ የሚገባው የመፍትሄ እርምጃ ምን ይሆን? ብዚዎችን ሊያነጋግርና ሊያስጨንቅ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም መፍትሄው ኢስላም ዘንድ ለመሆኑ ምንም አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ይሁንና መፍትሄው ይልቁንም መከላከያው የተስተካከለ እስላማዊውን ግንዛቤ ማስረፅ ሲሆን ይህን ኃላፊነት በትክክል በመወጣቱ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ የሚችሉት አላህ ፈሪ የሆኑ የሰለፊይ ዑለማዎች እንጂ ማንም ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መገሰፅና ለመምራት የሚንደረደሩት የተከበሩና ላቁ ነብያቶች የሰው ልጅ አስተማሪዎች የተንደረደሩበትና የተነሱበት መሰረት ላይ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ መንደርደሪያና መሻ ታዲያ አምላካዊው ራዕይ (ወህይ) ነው፡፡ ልብ ከበሽታው ህያው የሚሆንበት፣ ነፍስን ግራ ከመጋባትና ከመደንበር አውጥቶ የመንፈስ እረፍት የሚሰጥ መሰረት ነውና፡፡ መወሰድ ያለበት እርምጃ መፍትሄ1.ወጣቶችን ቁርአንና ሐዲስን አጥብቀው እንዲይዙና በማንኛውም ጉዳይ ላይ ወደ እነርሱ እንዲመለሱ መጥራትና ማስተማር፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላልና
‹‹የአላህንም (የማመን) ገመድ ሁላችሁም ያዙ አትለያዩም›› አል ዒምራን 1ዐ3ቁርአን አጥብቆ መያዝ አደጋ ላየ እንዳይወድቅ አላህ ያዘጋጀልን ጥሩ ምሽግ ነው፡፡2.ቁርአንና ሐዲስን በመልካም ቀዳሚ አበዎች ግንዛቤ መረጃትን ማስረገጥ ይህም ሊገኝ የሚችለው ሙስሊሞች አላህን ፊሪ የሆኑ ዑለማዎች እጅ ላይ ሲማሩ ብቻ ነው፡፡ አላህም እንዲህ ይላል፡-‹‹የማታውቁም ብትሆኑ የእውቀት ባለቤቶች ጠይቁ›› አል ነህል 43እንዲህም ብላልና 
‹‹ከፀጥታ ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላችውም ጊዜ እርሱን ያጋንናሉ ወደ መልዕክተኛውና ከእርሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች (ወደ አዋቂዎች) በመወሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር፡፡›› አል ኒሳህ 83
3.የፈተናና የጥፋት ቦታዎችን መራቅ፡፡ ችግሩን ለመራቅና መዘዙን ለመጠንቀቅ ሲባል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
‹‹ከእናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ፡፡›› አል አንፋል 25
ይህም የሚሆነው ከፈተና መጠበቂያ የሆነን መልካም ስራን በመስራት ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ “አንድ ድቅድቅ ጨለማ የሆነን ፈተና በመልካም ስራ ተሽቀዳደሙ (ቅደሙ) ግለሰቡ በእርሷ (በፈተናው) ምክንያት ሙስሊም ሆኖ ያድርና ከሀዲ (ካፊር) ሆኖ ያረፍዳል ሙስሊም ሆኖ ያረፍድና ከሀደ ሆኖ ያመሻል ይኸውም ሃይማኖቱን በዱንያ ሸቀጥ ይለውጣል፡፡”

4.በአምልኮትና አላህን በመፍራት ላይ ትጉህ መሆን ነው፡፡ ከከአደጋ መትረፍ መንገድ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላልና
‹‹አላህን የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጣ ደርግለታል›› አጠላቅ 2
5.ነገሮችን በመቻልና በአስተዋይነት ለመፍታት መሞከር፣ በውሳኔ ላይ አለመቸኮል፣ ከስሚታዊነትና ከግንፈልተኝነት መራቅ፡፡ ይህም የመልዕክተኞችና የቅን ተከታዮቻቸው ፈለግ ነውና፡፡ አላህ ሱ.ወ ስለ ነብዩ ኢብራሂም ዓ.ሰ እንዲህ ብሏልና 
“ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ አልቃሻ መላሳ (የወደ አላህ ተፀፃች) ነውና፡፡” ሁድ 75
በጥቅሉ እስላማዊው መፍትሄ ያለው ቁርአንና ሐዲስ ውስጥ ነው፡፡ በንግግርና በምክር ያልተለወጠ በብትር ይለወጣል፡፡ ማህበረሰቡም የራሱን ግንዛቤ በማስተካከል የምፍትሄ እምዳ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡

Post a Comment

0 Comments