Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እውቀትን እንዴት እና ከማን መያዝ አለብን ?

መንሀጅን (የሰለፎችን መንገድ) ከትክክለኛ ባለቤቱ አለመያዝ እና እውቀትን እንዴትና ከማን መያዝ እንዳለብን አለማወቅ የፊትና ሰበብ ነው።http://www.facebook.com/wesetiyaእውቀት የሚያዘው በእውቀት ከተካኑ ዑለማዎች (ምሁሮች) ሲሆን እነሱም ቁርአንና ሀዲስን በተገቢው መልኩ የሚረዱ የሃይማኖትን መሰረቶች የሸሪዓን አላማና ፅንሰ ሐሳብ የሚያውቁ ሊሆኑ ይገባል፡፡
وَإِذَا جَاءَهُمْ أَمْرٌ مِنَ الْأَمْنِ أَوِ الْخَوْفِ أَذَاعُوا بِهِ وَلَوْ رَدُّوهُ إِلَى الرَّسُولِ وَإِلَى أُولِي الْأَمْرِ مِنْهُمْ لَعَلِمَهُ الَّذِينَ يَسْتَنْبِطُونَهُ مِنْهُمْ

‹‹ከጸጥታ ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላቸውም ጊዜ እርሱን ያጋንናሉ፡፡ ወደ መልክተኛውና ከእነርሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች (ወደ ዐዋቂዎቹ) በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር፡፡›› አል ኒሳእ 83

فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِنْ كُنْتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

‹‹የማታውቁም ብትሆኑ የእውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ›› አል ነህል 43

እውቀትን ዐሊም ካልሆነ ሰው መውሰድና መያዝ ከጥመት ምክንያቶች ውስጥ አንዳ መሆኑን ነብያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሲያስተምሩ እንዲህ ብለዋል፡-

“አላህ እውቀትን ከሰጣችሁ በኃላ መንጠቆን አይነጥቃችሁም ነገር ግን የእውቀት ባለቤቶችን ከነእውቀታቸው በመግደል ይነጥቃችኋል ከዚያም መሀይም ሰዎች ይቀራሉ ሰው ስለዲን ይጠይቃቸዋል በሐሳባቸው (በግምት) ይመልሳሉ ራሳቸው ጠመው ሰው ያጠማሉ፡፡” ይህ የቡኻሪ ዘገባ ሲሆን በሙስሊም ዘገባ ደግሞ
“አላህ እውቀትን ከሰዎች ልብ መንጠቅን አይነጥቀውም ነገር ግን ዑለማዎችን በመያዝ (በመግደል) እውቀቱን ያነሳዋል ምንም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ ሰዎች ጃሂሎችን መሪ አድርገው ያዙ ስለዲን ተጠየቁ ያለ እውቀት በመመለስ ጠመው አጠመሙ፡፡”

እንደዚሁ እውቀትን ከቢድዓና ከስሜት ባለቤቶች መውሰድ ከሙብተዲዕ ቡድኖች እውቀት መያዝ በሚያሳዩት ብልጭልጭ ነገር መታለል በማስታወቂያቸው መሸወድ መሸንገል አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ግልፅ የሆነው ሸይጣንም ብልጭልጭ ነገሮችን በማሳየትና በውሸት በመማል ነው ሰውን የሚያታልለው፡፡

فَوَسْوَسَ لَهُمَا الشَّيْطَانُ لِيُبْدِيَ لَهُمَا مَا وُورِيَ عَنْهُمَا مِنْ سَوْآتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَاكُمَا رَبُّكُمَا عَنْ هَذِهِ الشَّجَرَةِ إِلَّا أَنْ تَكُونَا مَلَكَيْنِ أَوْ تَكُونَا مِنَ الْخَالِدِينَ
وَقَاسَمَهُمَا إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ النَّاصِحِينَ

‹‹ሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፡፡ «ጌታችሁም መልኣኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም» አላቸው፡፡ እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ» ሲልም አማለላቸው፡፡›› አል አዕራፍ 2ዐ-21

Post a Comment

0 Comments