Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ድራማ


Sadat Kemal Abu Nuh

‹‹ድራማ››
1) ‹‹ኢስላማዊ›› የሚባል ቅጥያ ቢለጥፉበትም፤
2) ማንም ይፈቀዳል ቢልም፤
3) የትኛውም ቻናል ላይ ቢቀርብም፤
4) በየትኛውም ቋንቋ ቢሰራም
ድራማ የሚባል ነገር የለም፡፡
ቁርዓን እና ሀዲስ ያልገሰፀውን ተውልድ ድራማ ይለውጠዋል ማለት ዘበት ነው፡፡ ከነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ከሰሀባዎች ባህሪ ያልተማረ ትውልድ፤ ጫት ቃሚ እና አጉል አስፀያፊ ባህሪ ካለባቸው አርቲስቶች ኢስላምን እና ጥሩ ስነምግባርን ሊማር አይችልም፡፡
ኢስላም የአርቲስቶች መነገጃ አይደለም፡፡ ኢስላምን የምንማርበት መንገድ አለው እሱም እውቀትን በመማር ነው፡፡ ኢስላም ከቁርዓን፤ ከሃዲስ፤ ከደጋግ ሰለፎች እና እነሱን በበጎ ከተከተሉ ኡለማ እንጂ ዲንን ጠንቅቆ ከማያውቁ በሰላት ሰዐት አላህ የጠላው ቦታ ከሚገኙ አርቲስቶች አይደለም፡፡

አርቲስቶች አላህን ፍሩ ህዝቡን አታጥምሙ፡፡ ያለ እውቀት ወይንም እውቀት እያላችሁ ስሜታችሁን ተከትላችሁ ድራማ ይቻላል እያላችሁ የምትናገሩ ሰዎች አላህን ፍሩ፤ ነገ ባሳሳታችሁት ሰው ልክ ትጠየቃላችሁ፡፡ ህዝባችን ኢልም ተጠምቷል ኢልም ይማርበት፡፡ ኢልም በኢኽላስ ለተማረው የጀነት መንገድ ነው፡፡ መስጂድ በሮች ላይ የሚለጠፉት ሴት እና ወንድ የሚሰሯቸው ፊልሞች ወደ ጥመት የሚጣሩ ሰይጣናት መሸንገያዎች ናቸው፡፡ ሁላችንም አላህን እንፍራ፡፡