Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እውነተኛ አንድነት ግድ ነው፡፡ መለየት ባለብህም ቦታ መለያየት ግድ ነው፡፡

===================================
አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) አንድ ሁኑ ብሎ አዙዋል፡፡ አንድ ሁኑ ሲልም በምን አንድ መሆን እንዳለብን አስቀምጧል፡፡ እሱም በአላህ ገመድ ላይ፡፡ በአላህ ገመድ ላይ የሚለውን (ቁርኣን፤ ሱና) ተብሎ ተተርጉሟል፡፡አላህን አንድ አድርጎ መገዛት፤ ተውሂድ አንድ ሲያደርግ የዚህ ተቃራኒ ደግሞ ሽርክ እንድንለያይ ግድ ይለናል፡፡ ለምሳሌ ከአላህ ውጭ አገራችን ላይም ይሁን አለም ላይ ‹‹ያ አብድል ቃድር ጀይላኔ፤ ያ ሰይድ በደዊ፤ ያ ኑር ሁሴን፤ ያ አልይ፤ ያ ሁሴን›› ብሎ በአምልኮ ክፍል ከአላህ ውጭ ያለን ከጠራ ሰው ጋር አንድ ነን በለን አንሄድም፡፡ ምክንያቱም አንድ የሚያደርገንን ነገር ስለጣሰ፡፡ ሌላው ቁርዓን ስሙ ‹‹ፉርቃን›› ይባላል፡፡ ፉርቃን ማለት ሃቅን ከባጢል የለየ ማለት ነው፡፡ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹ፈርቁን በይነናስ›› (በሰዎች መሃል የሚለያይ (የሚበታትኑ) ናቸው)፡፡ ኢብራሂም አለይሂ ሰላም ከሚወዱት ከነበረው አባታቸው እና ህዝቦቻቸውን ጥለው የሄዱት አባታቸው እና ህዝቦቻቸው ‹‹በአላህ አንድነት›› ስላላመኑ ነበር፡፡ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን ኡመር (ረድየላሁ አንሁማ) ስለ ከኢራቅ አካባባ ስለነበሩ የጥመት ቡድኖች ‹‹ቀደርያዎች›› የሚከተለውን ተናግሯል ‹‹በአላህ መንገድ ላይ የኡሁድ ተራራን የሚያክል ወርቅ ቢሰጡ አላህ አይቀበላቸውም፤ እኔም ከነሱ አይደለሁም እነሱም ከእኔ አይደሉም›› ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል፡፡ ታድያ ሰዎች ለምን ይሆን ‹‹አንድነትን›› ሽፋን አድርገው 124000 ነብያት ሁሉ የተላኩበትን የተውሂ ትምህርት ሲሰጥ የሚበሳጩት፡፡ ወደ እውነተኛ አንድነት ‹‹ተውሂድ እና ሱና›› ብቻ ሲባል አይመቻቸውም፤ እነሱ አንድነት ብለው የቀረፁት ‹‹የውሸት አንድነት›› ላይ ያልገባውን ሰው ‹‹አንድነት በታታኝ›› ‹‹የኡማው ጉዳይ የማያሳስባቸው›› ብለው ይጠሩታል፡፡ ግን ተነቅቶባቸዋል፡፡የገዛ አገራችን ላይ ነጃሺ፤ አሊ ጎንደር፤ የዳንግላው ሸይኽ፤ የቡሪው፤ አባድር፤ ኑር ሁሴን፤ አብሬት፤ አልከሶ፤ ቃጥባሬ፤ ዳና፤ ደግዬው፤ ጀማ ንጉስ እየተባለ ስንቶች ተወልደው ያደጉበት ቦታ ላይ የገዛ ቤተሰቦቻቸው ከአላህ ውጭ ያለን ይጠራሉ፤ ይመኩበታል፡፡ ነገር ግን ይህን ሁሉ እያዩ ዝም ይላሉ፤ ብሎም ‹‹እኛ ለኡማው አንድነት እንጨነቃለን›› ብለው የውሸት አንድነትን ይመሰርታሉ፤ ልቦቻቸው ግን የተለያዩ ናቸው፡፡ እስቲ ሰው የገዛ እናት እና አባቱ ‹‹የቦረናው ደግዬእርዱኝ አባብዬ›› ብሎ ከአላህ ውጭ እየጠራ፤ የወለዱት እና በመከራ ያሳደጉት እናት እና አባት፤ ካልቶበቱ ዘላላም ጀሃነም እሳት ውስጥ የሚከታቸውን ነገር እያየ ዝም የሚል፤ እውነት የኡማው አንድነት እና የኡማው ጉዳይ ያስጨንቀዋል???አላህ ከአስመሳዬች ይጠብቀን፡፡ አላህ እንዲህ ይላል ‹‹ምድር ከተስተካከለች በኋላ አታበላሹዋት ሲባሉ፤ አረ እኛ አሳማሪዎች ነን ይላሉ፡፡ አዋጅ (ንቁ) እነሱ አበላሾች (ሙፍሲዶች) ናቸው፡፡››ከአላህ በላይ ማን ይናገር፡፡ ሂሳብ ለሚገባው የተጠየቀ ጥያቄ ሃቅ ስንት ነው???መልሱም 1 ናት፡፡ የማትከፈል የማትሸረፍ፡፡ እዚህ ሃቅ ላይ መሰባሰብ ግዴታችን ነው፡፡ በቁርዓን እና ሀዲስ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለውን የውሸት አንድነት እንድንርቅ ታዘናል፤ ከላይ እንዳለፈው፡፡ አህባሽም፤ ሺኣም፤ ሱፊም፤ ኢኽዋኑም፤ ሌላውም ሌላውም ‹‹ሙስሊም ነኝ›› ይላል፡፡ እኛ የትኛውን ኢስላም ነው የምንከተለው??? የአህባሹን፤ የሱፊዩን፤ የሺአውን፤ የኢኽዋኑን ወይንስ የጥንት የጠዋቱን ያልተበረዘውን የነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና የሰሃባዎችን፤ የታቢኢኖችን፤ የአትበአ ታቢኢኖችን???መልሱም የጥንት የጠዋቱን፡፡ ወደ ስሌቱ ልመለስ እና ሱፊ + አህባሽ + ኢኸዋን + ሺኣ = የተለያዩ ጀመአዎች እንጂ 1 ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ስለ ‹፣ውሸተኛው አንድነት›› የምትሰብኩ መጀመሪያ ሂሳብ ተማሩ፡፡ታድያ ለምን ይሆን በአንድነት ስም ሽርክ እና ቢድዓ ያለበትን ሱፊ እና ኢኽዋን አትናገሩት የሚሉት??? እውነት ስለ አንድነታችን አስበው ወይንስ ይህ በድብቅ የሚያራምዱት ጀመዓቸውን ሽፋን ለመስጠት፡፡አሁንም ቢሆን አላህ ያዘዘውን የተውሂ እና ሱናን አንድነት እንጣራለታለን፤ ከዚህ ውጭ ያለውን ጀመዓዎችን ሁሉ ተዋቸው አትንኳቸው የሚባለውን ከኋላ የመጣ አይን አወጣ፤ ቅጥፈት አላህ ያግዘን ሞት እስኪመጣን ድረስ እንታገለዋለን፡፡ እነዚህ ሰዎች በሱና እና በተውሂድ 1 መሆን ለምን ከበዳቸው??? ምክንያቱም የነሱ ቡድን የተመሰረተው የዛሬ 90 አመት፤ መፀሃፍም ፃፉ፤ ብዙ ለፉለት ሊያስተዋውቁት፡፡ አራህማን ግን የተመሰረቱበት አገር ላይ ውርደትን አከናነባቸው፡፡ ነብያት ሁሉ ለተላኩበት ተውሂድ የለፉ ቢሆን ኖሮ እኛም እንደግፋቸዋለን ባሉበት፤ ነገር ግን 3 ሚሊዬን ሰው ‹‹በደዊ›› ቀብር ላይ ተሰብስቦ ‹‹በደዊ ሆይ ልጅ ስጠኝ›› ብሎ ሲለምን ዝም ያሉ ቡድኖች ናቸው፡፡ የአላህ መብት ያላሳሰባቸው፤ አላህ ይረዳቸዋልን??? መልክቱም ሲጠናቀቅ፡፡ ስለ ተውሂድ እና ሱና የሚያስተምሩ ወንድም እና እህቶች ሁሉ አላህ ኢኽላስ ይስጣቸው፤ ኡማውን ሁለት አገር አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኘው ብለው ነው፤ የስድብ ሁሉ ውርጅብኝ የሚወርድባቸው፡፡ ሌሎቹ እማ አቂዳን ወደ ኋላ ብለው፤ ሌላ አርስት አውርቶ ዛሬ በሰው ይወደድ ይሆናል፤ ነገ ግን????????? ተራቹ ሲተርት ‹‹የደባ ገበያ በሬው 10 ብር፤ ቆዳውን 20 ብር›› አለ፡፡ ተውሂድን ‹‹በውሸተኛው አንድነት›› ስም ማስቆም፡፡ አህባሽ ደግሞ በቀጥታ፡፡ አላህ ለአህባሽም ለኢኽዋንም አያሳካላትም፡፡