Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ ከጀበና ሰባሪዎች ያድርገን፡፡


‹‹ጀበና ተሰበረ ብሎ›› ያዙኝ ልቀቁኝ ለሚሉት ‹‹ኢኽዋኖች›› የተሰጠ ምላሽ፡፡አንድ ቡድን ወይንም አንድ ሰው እንዴት ሃይማኖቱን ጠንቅቆ ሳያውቅ፤ ለሃይማኖቱ ዘብ ቆሚያለሁ ይላል???
በኢኽዋነል ሙስሊሚን አስተምህሮት ልባቸው ከንፁህ የኢብራሂም (አለይሂ ሰለም) እምነት የተሸረሸሩ፤ ሰዎች በፌስቡክም ይሁን፤ በሌሎች ሚዲያዎች፤ ወደ ተውሂድ የሚጣሩ ወንድም እና እህቶችን ሲያሽሟጥጡ እና ሲዘልፉ ይታያሉ፡፡ ብዙ ብለው ፌስቡክ ላይ ፅፈዋል ለአንዷ ለሚከተለው አባባላቸው ብቻ መልስ ልስጥ
1) <<የማህበራዊ ኑሮ ምስቅልቅልነት መንስኤዎችተገንዝበውትም ሁን አሽትተውት ሁሌ የሚዘፍኑለት ዐቂዳ እና ተውሂድ ወደ ሰው ሲያስተምሩት ወደ ጉሮሮ ከተላከ ክሽሽ ካለ ዳቦ ይበልጥ አሳማሚ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ስኬታማ ኤደሉም፡፡ ዘለው ሄደው የእናቶችን ጀበናና ሲኒ ይሰብራሉ፡፡ >>
ይህ የአዛኝ ቅቤ አንጓቾቹ ‹‹ኢኽዋኖች›› አባባል ነው፡፡ እስቲ እንየው በተን አድርገን የመጀመሪያ እንዲህ ብለዋል
1) ‹‹ሁሌ የሚዘፍኑለት ዐቂዳ እና ተውሂድ ወደ ሰው ሲያስተምሩት ወደ ጉሮሮ ከተላከ ክሽሽ ካለ ዳቦ ይበልጥ አሳማሚ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ስኬታማ ኤደሉም››
እስቲ ይህን አባባል ተመልከቱ፡፡ አቡ ለሃብ (አላህ የሚገባውን ይስጠው) በዘመኑ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ ተውሂድ ህዝባቸውን ሲጠሩ እሱ የሚከተለውን ነበር ያላቸው ‹‹ለዚህ ነው የሰበሰብከን፤ እልም ያድርግህ›› ብሎ ነበር የተሳለቀላቸው፡፡ 
በመቀጠል ‹‹ኸጢቡል አንቢያ (የነብያት ሁሉ ኹጥባ አድራጊ)›› የተባሉትን ነብየላህ ሹዓይብ (አለይሂ ሰላም) የገዛ የጠመሙ ህዝቦቻቸው እንዲህ ሲሉ ነበር ያላገጡባቸው ‹‹አብዛኛው የምትናገረው እኮ አይገባንም›› ፤ ዛሬ የነዛን ተምሳሌነት የወሰዱት ኢኽዋኖች ‹‹ዐቂዳ እና ተውሂድ ወደ ሰው ሲያስተምሩት ወደ ጉሮሮ ከተላከ ክሽሽ ካለ ዳቦ ይበልጥ አሳማሚ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ስኬታማ ኤደሉም›› ብለው ወደ ተውሂድ እና ሱና የሚጣሩ ወንድም እና እህቶችን ያማሉ፤ ይቦጭቃሉ፡፡ ያው ለእነርሱ ሲሆን የሰው ስጋ፤ የተውሂድ እና ሱና አስተማሪዎችን ስጋ መብላት ይፈቀድላቸዋል፡፡ የቢድዓ አራማጅን ስናስጠነቅቅ ግን ‹‹የሰው ስም ማንሳት›› ይላሉ፡፡ ምንኛ የሚጋጭ ሎጂክ ነው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ‹‹አንድ ነብይ ይመጣል ከሁለት እና ሶስት ሰዎች ጋር፤ ሌላ ነብይ ይመጣል የሚያምኑለት አጥቶ ብቻውን፤….›› ነብያትም ይሁኑ እነሱን የተከተሉ የተውሂድ ተጣሪዎች የሚጠበቅባቸው ማድረስ ብቻ ነው፤ የሚመራው አላህ ነው፡፡ ችግሩ እንደነሱ ቲፎዞ ያልሰበሰበ ‹‹ዳእዋው ያልተሳካለት›› እነሱ የሰበሰቡትን ‹‹የተለያየ አቂዳ ያላቸው ቡድኖች›› ደግሞ ቁጥራቸው ስለበዛ እና በየሚዴያው ተከታታይ ስላገኙ ድል አድርገው አይተውታል፡፡ አኸይራ ላይ ፍርድ ሰጪው አላህ የነብያት ፈለግን ያልተከተሉ ሰዎችን ስራ ይቀበላልን ????????????
እነሱ የትኛውን ፍሬ ይሆን ያፈሩት፤ ሽርክ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ‹‹አንድ ነን›› ብሎ ፎቶ ከመነሳት ውጭ፤ እስቲ አንድ ወደ ተውሂድ የተጣሩበትን ትምህርት ንገሩን፡፡
ዳእዋ ማለት እየተቅለሰለሱ ‹‹ሴት ማማለል›› አይደለም፡፡ አላህ ሰማይ እና ምድርን የላከበትን ተውሂድ ከእርሱ ጀምሮ ለኡማው ማድረስ ነው፡፡ ይህ ነው ለኡማው መቆርቆር ማለት፡፡ የተውሂድ እና ሱና ተጣሪዎችን አላህ ኢኽላስ ይስጣቸው፤ ያግዛቸው፡፡ አላሁመ አሚን፡፡
2) እንዲሀም ብለዋል ‹‹ዘለው ሄደው የእናቶችን ጀበናና ሲኒ ይሰብራሉ፡፡›› በጣም የሚገርመው አሁንም ኢኽዋኖች ግልፅ የኢስላም ጠላትነታቸውን እያሳዩን ነው፤ በሚፅፉት ፅሁፍ፡፡እስቲ ሁኔታውን እንቀይረው ወደ ጀበና መሰበር ከምምጣታችን በፊት፡፡ አንድ እናት ልጇ እሳት ሊበላባት ቢል (የዱንያውን እሳት) ልጄን አስደነግጠዋለው ሳትል፤ ‹‹ኡኡኡኡኡኡኡ›› ብላ ጮሃ ልጇን ከዱንያ እሳት ትጠብቃለች፡፡
አንድ እናት እና አባት ልጃቸው ሲያጠፋ ‹‹ይገርፉታል›› ለእርሱ አስበው፡፡ ታድያ በተገላቢጦሹ፤ አንድ ወጣት እናት እና አባቱን በጣም ስለሚወድ እና ይህ ውዴታው በዚህ ዱንያ ብቻ ሳይሆን የሚቀጥለው አለም ላይ፤ ወዳጅ እንዲሆኑት ከፈለገ፡፡ 
እናቱ የምትሰራውን ሽርክ ‹‹ባለ 2 አፍ ጀበና (የጠንቋይ ጀበና)፤ ጨሌ፤ ትብታብ፤ የአድባር ዛፍ እና የመሳሰሉትን›› ቢሰብር እና ቢቆርጥ ምኑ ላይ ነው ጥፋቱ????????????????????????ይህ ወጣት የማንን አርአያ ነው የተከተለው????????????????????????
ጥርጥር የሌለው የሁለቱን ኸሊሎች የኢብራሂምን እና የሙሃመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አጅመኢን) ፈለግ ነው የተከተለው፡፡ አላህ ከጀበና ሰባሪዎች ያድርገን፡፡ ነብየላህ ኢብራሂም (አለይሂ ሰላም) አባቱ እና ህዝቦቹ ሲያመልኩ የነበረውን ‹‹ጣኡት›› አፍርሷል፤ ሰባብሯል፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እነደዛው መካን ሲቆጣጠሩ ‹‹360 ጣኦታትን›› አፍርሰዋል፤ ሰሃባዎች እና እነሱን የተከተሏቸውም እንደዛው እንዲህ አይነት የሰው ልጅ ከአላህ ውጭ ልባቸው የሚንጠለጠልባቸውን ነገሮች ሰብረዋል፡፡
በጣም የሚገርመው አዲስ አበባ ላይ አንድ እራሱን ‹‹ኢኽዋኒ ነኝ›› እያለ የሚጠራ ሰው የሰራውን ላጫውታቹ፡፡ የዚህ ሰው አባት ወደ ወሎ ‹‹ሙወከል ወይንም ማድማት›› የሚባለውን የጂን አምልኮ ሊፈፅም ሲል፤ ለምን ለአባትህ አትነግረውም ተብሎ ሲነገረው፤ ይህ ሰው ‹‹በሂክማ ነው፤ ትንሽ ፋዘርን ስለምፈራው አልነግረውም›› አለ፡፡ 
በጣም የሚገርመው አባቱ የሚሰራውን ሽርክ አለመናገሩ ሳይሆን፤ ‹‹አል ጀዚራ›› ቲሊቭዥን ከፍቶ ለአባቱ ‹‹አረብኛ›› እየተረጎመለት የሚከተለውን አለው ‹‹አባቴ ሆይ! ግብፅ ላይ የተመረጡት ሙሃመድ ሙርሲ ..›› ብሎ ኹራፋቱን የሚለፋለትን ፓርቲ፤ ሽርክ ለሚሰራ አባቱ አስተዋወቃቸው፡፡ ታድያ ይህ ኢኽዋኒ እውነት ለአባቱ ያስባል???????????????????????? ለአባቱ ካላሰበ ለኢትዬጵያ ሙስሊም ያስባልን????????????????????????
ጀበና ተሰበረ ብለው ለጀበና ጥብቅና ከቆሙ የማንን ዲን የበላይ ለማድረግ ነው እየለፉ ያሉት ‹‹የኢብራሂም (አለይሂሰላም) እና የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)ን ተውሂድ ወይንስ የነ አቡ ጀህልን››???????????????????????? የነሱን ስራ አላህ ይፍረደው፡፡አላህ የተውሂድ እና የሱና ጠበቆች ያድርገን፡፡ አላህ ሆይ! የሽርክ እና ቢድዓ ጠበቃ ከመሆን ባንተው እንጠበቃለን፡፡
የአላህ ባርያ ሆይ! አላህ በሰጠን ንፁህ ጭንቅላት ተጠቅመን ሃቁን እንከተል፡፡ አላህ የሚረዳው የነብያቱን መንገድ የተከተለውን ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ ግብፅ ላይ ይህን ፓርቲ ከስንት ዘመን ውሸት በኋላ አላህ ሊፈትን ‹‹ስልጣን›› ሰጣቸው፤ አይደለም ለኢስላም ሊሰሩበት ‹‹ሺአ›› እምነትን በአንድ አመት ውስጥ አስፋፉበት፡፡
አብዛኞች ኢኽዋን ሲጋለጥ ‹‹እኛ የኢትዬጵያ ሙስሊሞች ነን፤ የግብፅ ጉዳይ አይመለከተንም›› ይላሉ፡፡ በጣም የሚገርመው ግን አላህ እንዳለው ‹‹በልቦቻቸው የሌለውን፤ በአፎቻቸው ይናገራሉ›› እንዳለው፤ እውነታውን ፌስቡክ ላይ አይተነዋል፡፡ ልክ ኢኽዋን ስልጣን ሲይዝ በጣም ተደስተው ፈነጠዙ ፕሮፋይል ፒክቸራቸውን ሁሉ በሙሃመድ ሙርሲ አደረጉ፡፡ ሙርሲ ሲወርድም እንደዛው በየቀኑ ግብፃዊ የሆኑ እስኪመስል ድረስ የየደቂቃውን የግብፅ ዜና በፌስቡክ ፖስት አደረጉ፡፡
ታድያ የሚገርመው ይህ አይደለም፤ በጣም የሚገርመው እኛ ግብፅ ውስጥ ያለውን ‹‹ሽርክ›› ለምሳሌ ‹‹የበደዊ ቀብር›› ብለን ስንፅፍ፤ ሽርኩ መጋለጡ በጣም ይከፋቸዋል፡፡ ምክንያቱም የጀመዓቸው መመስረቻ አገር ውስጥ ይህ ሽርክ እየተሰራ እና እነሱ ለኢስላም ሳይሆን ኢስላምን ተጠቅመው ስልጣን አሳዳጆች መሆናቸውን መግልፅ ስለሚያሳይባቸው በጣም ይበሳጫሉ፡፡
ታድያ ወዴት ወዴት ???????????? ለምን መዋሸቱ አስፈለገ???????????? የትም ቦታ ያ ሙስሊም ስለ ሌላ አገር ላይ ስላሉ ሙስሊሞች የሚያሳስበው፤ አንድ ፖሊቲካ ፓርቲ ‹‹ኢስላምን ሽፋን›› አድርጎ ስልጣን የሚያሳድ መሾሙ እና መውረዱ ወይንስ ኢስላሞችን ሙስሊም ያሰኛቸው የተውሂድ ጉዳይ እና ከሽርክ መራቅ??????????????????????
በሽርክ አንደራደርም ስንላቸው ‹‹ሙስሊም ሁሉ አንድ ነው›› አትከፋፍሉን ይሉናል፡፡ እሺ ታድያ ‹‹ሙስሊም ሁሉ አንድ ከሆነ›› ሙባረክን ከስልጣን አምፀው ስያወርዱት ‹‹ሙስሊም›› መሆኑን ረሱትን???????????? ወይንስ እናንተ የፈለጋችሁትን ካፊር ነው ማለት ትችላላችሁ????????????ሌላው ለሙስሊም መሬ መታዘዝ የሚለውን ሃዲስ ለሌች ሙስሊም መሬዎች ለምን ተግባራዊ አታደርጉትም???????????? ለምን ለሙርሲ ብቻ ይሁን ትላላችሁ???????????? ይህ እራሳችሁን ሰፊ እና የሌሎችን ሀሳብ እናስተናግዳለን የሚለው ውሸታችሁ፤ ይሀው ደብቃችሁ፤ ትታችሁ የነበሩትን ሀዲሶች ሁሉ ለጀመዓችሁ እና ለሙርሲ ተጠቀማችሁባቸው፡፡
ስለዚህ አላህ ውሸታሞችን ከማዋረድ ወደኋላ አይልም፡፡ ተጠንቀቁ ፌስቡክ ላይ ውጭ አገር በሰላም ተደብቃችሁ ተቀምጣችሁ ሙስሊሙ ላይ ፊትና እየፈጠራችሁ ያላችሁ ሰዎች፤ አላህ የምትሰሩትን ሁሉ፤ የምንሰራውን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
አላህ ሆይ! ወደ ነብያት ሁሉ ወደለፉለት ተውሂድ እና ወደ እውነተኛ አንድነት ምራን፡፡ ‹‹በውሸት አንድነት ስም›› ከነብያት መንገድ አዘናግተው ፖለቲከኛ ሊያደርጉን ከተነሱ ‹‹ኢኽዋኖች›› ጠብቀን፤ በአህባሽም ላይ ድልን አጎናፅፈን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኞቹ፤ ሃቅን እስከ ቂያማ ድረስ በተከተሉ ሁሉ ላይ ይሁን፡፡ አላሁመ አሚን፡፡