Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢኽዋን የሁሉም “አባት”

by Ibnu Munewor
ኢኽዋን ከማንም በላይ ስለአንድነት ይጮሃል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ኡማውን ይበታትናል፡፡ አንዲት ሀገር ውስጥ ኢኽዋን ከገባ በርግጠኝነት ሌሎች ቡድኖች ተከትለው ይገባሉ፡፡ ኢኽዋን “አንድነትን ያናጋል” በሚል ፈሊጥ የየትኛውንም አንጃ ጥመት እንዲጋለጥ አይፈልግም፡፡ አሳሳች ቡድኖችንና የተለያዩ ጥመታቸውን ለማጋለጥ ስትሞክሩ ኢኽዋንና ባምሳሉ የቀረፃቸው ሮቦቶች ህዝብ አትበታትኑ በሚል ፈሊጥ አጥፊዎቹ ጡንቻ የሚያወጡበት ጊዜ ይሰጣቸዋል፤ “ጥሩ” የሚለውን ጎናቸውን እያጎላ ህዝብ ዘንድ እንዲሰርጉ ያመቻችላችኋል፡፡ “ኧረ ይቺ ባቄላ...” ካላችሁ ካጥፊዎቹ ጋር ሆኖ በናንተ ላይ ይዘምታል፡፡ ይህን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሺአዎች ወደ ሱኒው አለም እየሰረጉ ነው፡፡ ተክፊሩ እግሩን እየዘረጋ ነው፡፡ ተብሊጉ እያጥለቀለቀው ነው፣ አሕባሹ እያመሰው ነው…፡፡ አሕባሽን እንደምሳሌ ብንወስድ አሳሳች አስተምህሮቶቻቸውን የጀመሩት ከሁለትና ከሶስት አመት ጀምሮ አይደለም፡፡ ካስር አመት በላይ ሆኗቸዋል፡፡ ያኔ እነሱን የሚያጋልጥ እንደ ከፋፋይ ሲቆጠር፣ ባደባባይ ሲጠቆር ነበር፡፡ ለባለ ጥመቱ አረንጓዴ፣ ጥመታቸውን ለሚያስጠነቅቀው ግን ቀይ! ኢኽዋን!!! አሕባሽ “ጎራ” ተጠግታ እንደ እብድ ውሻ ሁሉን መናከስ ስትጀምር፣ የተሰጣትን የቤት ስራ ልትፈፅም አይኗን ጨፍና ስትቧጥጥ ጊዜ፣ ሰፊ ዘመቻ ተከፈተባት፡፡ አዎ ሊከፈትባትም ይገባል፡፡ ግን ቀድመው የነቁባት “ሳይቃጠል በቅጠል” ሲሉ፣ መጥሀፎቿን እያጣቀሱ ሲያጋልጧት አንዳንድ ከልክ በላይ ሰፍተው ሰፍተው... የተንቦረቀቁ እሷን ከነጥመቷ ትተው የሚያጋልጧት ላይ ዘመቱ፡፡ “አትጥበቡ! ልዩነት አታፈንፍኑ” እያሉ እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ ሰበኩ፡፡ “ሰበኩ” ማለት በኛ አካባቢ ቋንቋ “አታለሉ፣ ሸወዱ” ማለት ነው፡፡
አሁን አሕባሽ የምታደርስብንን ሰቆቃ ሁላችንም እያየን ነው፡፡ ግን የአላህ ቀደር ቢሆንም በጊዜ ተባብሮ በደንብ ብትኮረኮም ቢያንስ ቢያንስ የምታደርሰው በቀለለ ነበር፡፡ “አሁንስ ወደ ህዝብ መቼ ገባች” ይባል ይሆናል፡፡ የዋህነት! እሷማ ለመግባት ያለ የሌለ ሀይሏን እየተጠቀመች ነው፡፡ አብዛሃኛው ህዝባችን ግን ብዙውን ብልሹ ዐቂዳዎቿን አያውቅም፡፡ እሷ ግን የራሷን ልትጭንበት እየጣረች ነው፡፡ እኛ ደግሞ እያወራን፡፡ በሂደት ምን ያህል ህዝብ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አስቡት፡፡
ሺዐዎችም ከስንት አመት ጀምሮ ስውር በሆነ መልኩ እየሰረሰሩን እንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ሀይ እስኩልና ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እየሰሩ ነው፡፡ ይሄ ከባድ አደጋ ነው፡፡ ኢኽዋንን ግን አያሳስበውም፡፡ እኔ እንኳን በማውቀው በአዲስ አበባ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ለጊዜው መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም እየሰረጉ ነው፡፡ “እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ትንሽ ናቸው” ሊባል ይችላል፡፡ አህባሽስ ሲጀምር እንዲሁ አልነበር? ደግሞ ልክ እንደ አሕባሽ ወደ ህዝቡ ለመግባት እንዲያግዛቸው በማሰብ የታላላቅ “መሻኢኾች” አካባቢ ላይ አትኩረው እየሰሩ ነው፡፡ ደግሞ የቢድዐን ባህሪ የሚያውቅ “ትንሽ ነው” እያለ አያቃልልም፡፡ ቢድዐ ማለት እሳት ነው፤ እንዳውም የከፋ፡፡ በጊዜ ካላጠፋሃው ልትቆጣጠረው አትችልም፡፡ ለዚህም ነበር ከሰለፎች አንዱ “መስጂድ ውስጥ ማጥፋት የማልችለው ቢድዐ ከማይ ማጥፋት የማልችለው እሳት ባይ እመርጣለሁ” ያለው፡፡ አዎ ይህን የሚረዳው ግን “መጤ የሆኑ ነገሮችን ተጠንቀቁ!” ለሚለው ነብያዊ ትእዛዝ ዋጋ የሚሰጥ ነው፡፡በመልካም ቀደምቶቹ አጉሊ መነፅር አሻግሮ የሚመለከት፡፡ እይታው እንደ አህያ የተገደበው ግን በኢስላም ስም የጮኸ ሁሉ ለኢስላም እየሰራ ይመስለዋል፡፡ አህያ አይኗ ትልቅ ነው፡፡ እይታዋ ግን ደካማ፡፡ ለዚያም ነው ከርቀ...ት የሚያጠቃት አካል ሲመጣ ከወደ ጭንቅላቷ ወደ መሬት ዝቅ ብላ እስከምታረጋግጥ ታፈጣለች፡፡ ታፈጣለች እንጂ ቶሎ አትወስንም፡፡ በገንብ አይሌላትማ፡፡ “ተፈኩሯን” እንደቀጠለች አጠገቧ ሊደርስ ትንሽ ሲቀረው ድንገት አራት እግሯን አንስታ ትዘላለች!! ለቢድዐ የሚከላከል የዋህም ምሳሌው እንዲህ ነው፡፡ ለኢስላም የሚታገል እየመሰለው በኢስላም ስም ለጮኸ ሁሉ ይከላከላል፡፡ ሙብተዲዖቹ ጉልበት አግኝተው ማጥቃት ሲጀምሩ ግን የሞት ሽረት ትግል ያደርጋል፡፡ ሀይሃተ ሀይሃት!
እናም ሺዐዎች እየሰረሰሩ እየሰረጉ ነው፡፡ ኢኽዋንና ግርፎቹ ግን ሺፋን መስጠታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ገና አልባነኑም፡፡ መጅሊሱን ካልያዙት መስጂድ ካልነጠቁ መንቃታቸውን እንጃ፡፡ ተብሊጉም #በበርካታ-ዐቂዳው ከአሕባሽ አይለይም፡፡ ባጭሩ ተብሊግ ማለት በር ላይ ቆሞ የሚያንኳኳ አሕባሽ ማለት ነው፡፡ ወይም አሕባሾችን ወደ ህዝቡ የሚያደርስ ፈረስ በሉት፡፡ ዛሬ አሕባሾች ተብሊግን እየጋለቡ ወደ ህዝብ ለመግባት እየጣሩ ነው፡፡ እንዳውም አንድ ወንድም ተብሊግ ተመስሎ ከአንድ የአሕባሽ “ትልቅ” መሪ ጋር ቢቀርብ “እናተማ የኛው አይደላችሁ እንዴ” ብሎታል፡፡ ኧረ ይሄ ነገር ዝም ሊባል አይገባም” ካላችሁ “አትለያዩ” “አይደላችሁም እንጂ ትክክል ብትሆኑ እንኳ ለአሕባሾች ጉልበት ትሰጣላችሁ” ይላሉ፡፡ ቢያውቁ ግን ጉልበት እየሰጣቸው ያለው በመጀመሪያ የነሱ ሽፋን ነው፡፡ በመቀጠል የኛ ዝምታ ነው፡፡ በዝምታችን ተከልለው ዐቂዳችንን እየወጉ ነው፡፡ በቃ ኢኽዋን እያለ ሺዐንም፣ ተብሊግንም፣ ወዘተንም ማስጠንቀቅ አይቻልም፡፡ ልክ ትላንት ከአሕባሽ ማስጠንቀቅን እንደ ከፋፋይ አጀንዳ እየሳለ ለህዝብ ሲያቀርብ እንደነበረው፡፡ ለእያንዳንዱ ከፋፋይ አንጃ ከለላ እየሰጠ እስከሚፈረጥሙ ድረስ ጉልበት መግዣ ጊዜ ይሰጣቸዋል፡፡ ለህዝብ ምንም ስጋት እንደሌለባቸው እንዳውም የሌሎችን ቀዳዳ እንደዘጉ ለሙስሊሙ እንደሚያስፈልጉ ስሜት ቀስቃሽ ውሸቶችን ጭምር እየለቀቁ ይከላከሉላቸዋል፡፡ ስለዚህ መፍትሄው የችግሩ ዛፍ የሆነውን ኢኽዋንን መቆረጥ ነው፡፡ አይቻል እንዳይመስላችሁ፡፡ ቢድዐ ስር የለውም፡፡ በቀላሉ ይጎለሰሳል፡፡ እርግጥ ነው አጃቢዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ ከለላ የሚሰጣቸው የቢድዐ ቡድኖች ሁሉ ከጎኑ ናቸውና፡፡ የሁሉም አባት ሊሆን ስለሁሉም ይጮሃልና፡፡ ቢሆንም (አረፋውማ ግብስብስ ሆኖ ይቀራል፡፡ ለሰዎች የሚጠቅመው ግን በምድር ላይ ይቆያል፡፡)
አዎ ኢኽዋን ትንሽ ሲነካ ብዙ ይጮሃል፡፡ ጥቂት ሲጋለጥ ብዙ ያሴራል፡፡ ብዙ ይወነጅላል፡፡ የጭቁኖች ሁሉ አለኝታ ሆኖ ያስተጋባል፡፡ እኔን የሚገርመኝ ጩኸቱ አይደለም፣ ሴራውም አይደለም፣ ውንጀላውም አይደለም፡፡ እንዳውም እኔን የሚገርመኝ እሱ አይደለም፡፡ እኔን የሚገርሙኝ ጩኸታቸውንና ሴራቸውን እየፈሩ አፋቸውን የሚሸብቡት ናቸው፡፡ ሙብተዲእ ማንነቱ ሲጋለጥ እንዴት በቀላሉ ዝም ይላል? እንዴትስ ሐቅ ይናገራል? እንኳን በዚህ ቢድዐ ጉልበት ባወጣበት ዘመን፡፡