Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የከተሞች እናት


በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በአበል ቃሲም ላይ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና የነሱን ፈለግ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡መካ፤ ኡመል ቁራ፤ የከተማዎች እናት አላህ እና መልክተኛው ዘንድ የተወደደች እና የተከበረች ከተማ ናት፡፡ አላህ የተቀደሰው ቤቱን፤ ነብየላህ ኢብራሂም እና ነብየላህ ኢስማኢልን (አለይሂሙ ሰላም) ካእባን፤ መካ ላይ እንዲገነቡ አዘዘ፡፡ እነሱም ትዕዛዙን ሞሉ፡፡ አላህ ይህችን ውድ ከተማ ‹‹ኡመል ቁራ›› የከተሞች እናት ብሎ ጠራት፡፡ ረሱሉል ሁዳ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እነዛ አጋሪያን ከመካ ሲያባሩዋቸው እሳቸውም ዞር ብለው እንዲህ አሉዋት‹‹መካ ሆይ! እወድሻለሁ፤ ህዝቦችሽ ነው ያባረሩኝ›› አዛኙ አላህ ልባቸውን ሊያረጋው ምርጥ ሰዎች እና ምርጥ ከተማን ለገሳቸው፡፡
የስሪብ ‹‹መዲና›› የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከተማ በመባል የምትታወቀው፡፡ ሁሉም ነብያት ከሱ ያስጠነቀቁት የሆነው ደጃል አለምን ሲያዳርስ፤ መካ አና መዲና መግባት አይችልም፡፡ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከዘመን ሁሉ ይበልጥ ውብ የነበሩበት ዘመን፤ ነብያችን እና ሰሃባዎቻቸው በነበሩበት ዘመን ነው፤ ተራራ ያንቀጠቀጠው የተቅዋ ትውልድ፤ ድንጋይ እና ግኡዝ አካላት በነብያችን እጅ ተስቢህ ያደረጉበት፡፡
እንዚህ 2 ከተሞች ‹‹ሀረመይን›› የሚባል ስምም ተሰጣቸው፡፡
አላህ ሆይ! የተከበረውን ቤትህን እና የነብያት እና የሩሱሎች ኢማም የሆኑትን ነብይህን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም) መስጂድ፤ መስጂደ ነበዊ፤ ለመዘየር አብቃን፡፡
ናፍቀናል፤ ጀነት ገብተው ፊትህን ከሚያዩት፤ ከምርጥ ፍጡራንህ፤ ከነብያት፤ ከሲዲቆች፤ ከሸሂዶች፤ ከደጋጎቹ ጋር ቀስቅሰን፡፡ ያለንበትን ወቅት እና ሁኔታ አንተው ታውቀዋለህ፤ አላህ ሆይ! ያንተ እውነተኛ ባሪያዎች ሆነን፤ 2 አገር የተድላ እና የደስታ ባለቤቶች አድርገን፤ ከሚፈራው ሁሉ ከጣረ ሞት፤ ከቀብር ቅጣት፤ ከእሳት ጠብቀን፡፡
አንተ ቻይ ነህና፡፡ አላሁ አሚን፡፡
የስሪብ ‹‹መዲና›› የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከተማ በመባል የምትታወቀው፡፡ ሁሉም ነብያት ከሱ ያስጠነቀቁት የሆነው ደጃል አለምን ሲያዳርስ፤ መካ አና መዲና መግባት አይችልም፡፡ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከዘመን ሁሉ ይበልጥ ውብ የነበሩበት ዘመን፤ ነብያችን እና ሰሃባዎቻቸው በነበሩበት ዘመን ነው፤ ተራራ ያንቀጠቀጠው የተቅዋ ትውልድ፤ ድንጋይ እና ግኡዝ አካላት በነብያችን እጅ ተስቢህ ያደረጉበት፡፡እንዚህ 2 ከተሞች ‹‹ሀረመይን›› የሚባል ስምም ተሰጣቸው፡፡ አላህ ሆይ! የተከበረውን ቤትህን እና የነብያት እና የሩሱሎች ኢማም የሆኑትን ነብይህን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም) መስጂድ፤ መስጂደ ነበዊ፤ ለመዘየር አብቃን፡፡ ናፍቀናል፤ ጀነት ገብተው ፊትህን ከሚያዩት፤ ከምርጥ ፍጡራንህ፤ ከነብያት፤ ከሲዲቆች፤ ከሸሂዶች፤ ከደጋጎቹ ጋር ቀስቅሰን፡፡ ያለንበትን ወቅት እና ሁኔታ አንተው ታውቀዋለህ፤ አላህ ሆይ! ያንተ እውነተኛ ባሪያዎች ሆነን፤ 2 አገር የተድላ እና የደስታ ባለቤቶች አድርገን፤ ከሚፈራው ሁሉ ከጣረ ሞት፤ ከቀብር ቅጣት፤ ከእሳት ጠብቀን፡፡አንተ ቻይ ነህና፡፡ አላሁ አሚን፡፡