Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እርግጠኛ ሁን አንተ ስትሞት

 እርግጠኛ ሁን አንተ ስትሞት 



- ዱንያ አታዝንም

-የዓለም እንቅስቃሴም ይቀጥላል 

-ስራህን ሌሎች ይሰሩታል

-ንብረትህም ለወራሾች ይሆናል 


አንተ ግን ሒሳብ ትደረግበታለህ 


ስትሞት ቅድሚያ ካንተ የሚነሳው ስምህ ነው! ለዚያም ነው "አስክሬኑ የታል?" የሚሉት።

ሊሰግዱብህ ሲፈልጉም "ጀናዛውን አቅርቡት" ይላሉ። አፈር ውስጥ ሊያስገቡህ ሲፈልጉም "መይቱን ቀረብ አድርጉት" ይላሉ። ስምህ ትዝ አይላቸውም። 


ለዚህ ሲባል ንብረት ዘርህ፣ ስልጣንና ልጆችህ እንዳይሸውዱህ። የምንሄድበት ዓለም ግዝፈትና ያለንባት ዓለም ከንቱነት ምን ያህል የተራራቀ ነው? 


አሁን በሕይወት ያለኸው ሆይ! ስትሞት አንተ ላይ ሶስት ዓይነት ሃዘኖች አሉ

1) በደንብ የማያውቁህ ሰዎች ሐዘን:- ሚስኪን አላህ ይዘንለት ይሉሃል።

2) የጓደኞችህ ሐዘን:- ለሰዓታት ቢበዛ ለቀናት ያዝናሉ። ከዚያም ወደ ወጋቸውና ሳቅ ጨዋታቸው ይመለሳሉ።

3) ጥልቁ ሐዘን ቤት ውስጥ ነው። ሳምንታት፣ ወራት ከበዛ ዓመት ያዝናሉ። ከዚያም በትውስታ ማህደር ውስጥ ያኖሩሃል። 


በሰዎች መሃል ያለህ ታሪክ አብቅቶ ትክክለኛው ታሪክህ ጀመረ። እርሱም አኺራ ነው። የሰራኸው ስራህ ሲቀር ውበትና ተክለቁመናህን፣ ንብረትና ጤንነትህን፣ ቤተሰብህንና መኖሪያዎችህን ተለየህ። 


አሁን ጥያቄው ለቀብርና አኼራህ ምን አዘጋጅተሃል ነው?! ይህ ማሰብን የሚሻ እውነታ ነው። ግዴታ የተደረጉ ተግባራትን ብትፈፅም፣ ሱናዎችን ብታበዛ፣ ሚስጥራዊ ምፅዋትን ብትለግስ፣ መልካም ምግባርን ብትላበስ፣ የለሊት ሰላት ልማድህ ቢሆን ትድን ይሆናል። 


ሟች ወደ ዱንያ መመለስን የሚመኘው ሰደቃን ለመስጠት ነው። ዑለሞቹ እንደሚሉት የምንዳውን ፋና ሲያየው ምነው ባበዛሁት ይላል። የቻልከውን ያህል መፅውት።

Post a Comment

0 Comments