Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከውሸት እንጠንቀቅ "April Fool's Day"!

 


ከውሸት እንጠንቀቅ "April Fool's Day"!


የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– «ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ ወሬን እያወራ የሚዋሽ ሰው (ሊገጥመው ከሚችለው ጥፋት ወይም ኪሳራ አልያም ቅጣት) ወየውለት! ወየውለት! ።» 

ሀዲሱን ኢማም አቡ‐ዳውድ፣ ቲርሚዝይ፣ ነሳኢ እና አህመድ ዘግበውታል። አልባኒም ሰሂህ ነው ብለዋል።


ከዚህ ሀዲስ ተያያዥነት ያላቸው ቁም ነገሮች

1/ በማንኛውም ሁኔታ በንግግርም ይሁን በተግባር እውነተኛ  መሆን እንደሚያስፈልግ።

2/ ውሸት ምን ያህል ከባድ ወንጀል መሆኑ።

3/ ውሸት በፆም ሲሆን ደግሞ ፆሙን ምንም ዋጋ የሌለው ረሃብ እና ጥማት ብቻ ሊያደርገው የሚችል መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል። ይህን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– «የሀሰት ንግግርን፣ በሀሰት መስራትን እንዲሁም የመሀይማንን ተግባር ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን  ከመተዉ አላህ  ጉዳይ የለውም። (ቡኻሪ ዘግበውታል)

4/ ርእሱ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከአፕሪል‐1  ጋር ተያይዞ ለቀልድ ለጫወታ በሚል ስም ከሚፈፀመው የውሸት ንግግር እና ተግባር ጋር ተነሳ እንጂ ሌሎቹን የማይመለከት ተደርጎ ሊታሰብ አይገባም በተለይ የተለያዩ "ኢሰላማዊ" በሚሰኙ ሚዲያዎች "አርት" ወይም "ጥበብ" በሚል ስም የሚቀርቡ ፕሮግራሞች ለተመልካች ከመቅረባቸው በፊት ከዚህ ሀዲስ አንፃር ቢገመገሙ እንዲሁም ብዙ ተመልካች ለማግኘት የሚፃፉ ርእሶችም ቢመረመሩ መልካም ነው።

5/ ከዚህ በተጨማሪ እያንዳንዱ ሙስሊም በአቅሙ ልክ ማንን መከተል እንዳለበት ምን ማድረግ እንደሚፈቀድለት እና ምን እንደሚከለከለ ለማወቅ ያለውን አቅም ሁሉ መጠቀም የሚገባው መሆኑን መጠቆም ያስፈልጋል።


አላህ ሀቅን አይተው ከሚከተሉት ያድረገን! 


✍️ ጣሀ አህመድ




Post a Comment

0 Comments