Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ረመዳን ተጋመሰ፤ 14 ቀናቶች ተቆጠሩ። ትላንት ምሽት ደማቅና ሙሉ ውብ ጨረቃ ሰማዩን ውበት ሰጥቶት ነበር

ረመዳን ተጋመሰ፤ 14 ቀናቶች ተቆጠሩ። ትላንት ምሽት ደማቅና ሙሉ ውብ ጨረቃ ሰማዩን ውበት ሰጥቶት ነበር። 

የጨረቃዋ የሚያፈዝ ውበት የታላቁን ሶሀባ ጃቢር ቢን ሰሙራህን ገጠመኝ ያስታውሰናል!

የትላንት ምሽቱን በመሰለ፣ ሙሉ ውብ ጨረቃ በወጣችበት አንድ ምሽት ጃቢር ከመልዕክተኛው ﷺ ጋር ተቀመጦ ነበር።

 ጃቢር የጨረቃዋን ውበትና ድምቀት በአስተውሎት ተመለከተ፤ ከዚያም አንገቱን መልሶ የመልዕክተኞውን ﷺ የፊት ገፅታና ድምቀት በጥሞና ማየት ጀመረ። ልቦናዉ አንድ እርግጠኛ ድምዳሜ ላይ ሲደርስ ተሰማው!

ጃቢር የዚያን ምሽት ገጠመኙን እንዲህ ይተርከዋል፦

 "ጨረቃ ደምቃ በወጣችበት አንድ ምሽት የአላህን መልዕክተኛ ተመለከትኩ፤ ቀይ ልብስ ደርበው ነበር። ወደርሳቸውና ወደ ጨረቃ ደጋግሜ ተመለከትኩ፤ በእኔ ዕይታ መልክተኛው ከጨረቃ የበለጠ ውብ/ደማቅ መሆናቸውን አስተዋልኩ!"

ሐዲሡን ቲርሚዚ ፣ ዳሪሚይ፣ ሐኪምና ሌሎችም የሐዲስ ልሂቆች በመጸሐፋቸው ውስጥ በሰነዳቸው አስፍረውታል። አዝዘሀቢ ሐዲሡ በትክክለኛ ሰነድ የተዘገበ መሆኑን አረጋግጧል።

አባትና እናቴ ፊዳ ይሁንልዎ!  

*اللــــــــهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد .اللـــــــهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد*


#ረመዳን 15
❁ ❁❁ ❁ 

Haider khedir

Post a Comment

0 Comments