🍒 اصبر واحتسب
🍒 ታገስ! ተሳሰብም!
🎓በሸኽ ሷሊህ አል_ዑሠይሚን
📖በሀዲስ እንደመጣው መልክተኛው ﷺ ታገስ! ተሳሰብም! ብለዋል።
👉🏽ታገስ! ማለታቸው ግልፅ ነው። ተሳሰብ ያሉትን ቢያብራሩልን?
✒ምላሽ
🔺ሰውየው ችግር አጋጠመውና በትዕግስት አሳልፎ ነገር ግን ከአላህ ምንዳ እንደሚያገኝበት ካላሰበ፣ በዚህ ወንጀሉ ይማርለታል እንጂ አጅር አያገኝበትም።
🔺ትእግስት ሲያደርግ አጅር እንደሚያገኝበት በማሰብ ከነበር፣ ወንጀሉን ከማስማር አልፎ ምንዳም ይፃፍለታል።
🔹ስለሆነም መተሳሰብ ማለት ሰውየው ባጋጠመው ችግር ላይ በመታገሱ ከአላህ ምንዳ እንደሚፃፍለት በውስጡ ማሰቡና በአላህ ላይም መልካም ጥርጣሬ ማሳደሩ ነው። አላህም በመልካም የጠረጠረውን ይሰጠዋል።
📚ተዕሊቅ ዓላ ሰሂህ ሙስሊም
☀ሁዳ መልቲሚዲያ
0 Comments