Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአላህ ባሪያዎች ሆይ...🔹በሰማይም ይሁን በምድር ላይ የሚከሰት ነገር በሙሉ በአላህ ውሳኔና እርሱም ለሚያውቀው የላቀ ጥበብና ምክንያት ነው

የአላህ ባሪያዎች ሆይ...

🔹በሰማይም ይሁን በምድር ላይ የሚከሰት ነገር በሙሉ በአላህ ውሳኔና እርሱም ለሚያውቀው የላቀ ጥበብና ምክንያት ነው።አላህ የሚወስናቸው ውሳኔዎችም በሙሉ ለባሮቹ መልካምና በሁለቱም ዓለም (በገሃድ ሲታይ ጎጂ ቢመስሉም) ጠቃሚዎች ናቸው።

🔸የግልም ይሁን አጠቃላይ በሽታዎች (ወረርሽኞች) ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ይከሰታሉ፣ከምክንያቶቹም አንዱ ለበዳዮች ቅጣት ሲሆን ለምእምናን ደግሞ እዝነት፣ ወንጀል ማበሻና የሰምዓትነትን ማዕረግ ማግኛ መንገድ ነው።

🔹{በግፋቸው(የአላህን መልእክተኛ በማስተባበላቸው) ምክንያት እነሆ ቤቶቻቸው ፈራርሰው ባዶ ሆነዋል። በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሰዎች ትልቅ ተአምር አለ።እነዚያ ያመኑና ጌታቸውን ይፈሩ የነበሩትን አዳናቸው!}ሱረቱ አን'ነም 51- 53

▪️ከበሽታዎች ለመዳን ሰበቦችን ከማድረስ ጋር ይበልጥ ደግሞ አላህን እንፍራ፣ ልንቶብትና ወንጀሎችንም ልንርቅ ይገባናል!
 ዞሮ ዞሮ መሞትም ይሁን መታመም ቀድሞ የተቀደረ/ የተከተበ ነውና በቀደር አምነን እራሳችንን እናረጋጋ። ከበሽታ ይልቅ ብዙኃኑን የሚጎዳው ከልክ ያለፈ ጭንቀትና ስጋት ነው!
"አላህ የከተበልን ወይም የከተበብን ነገር እንጂ እኛ ላይ አይደርስም!" 

🔸ከዚህም ጎን ለጎን በምንችለው ያክል እራሳችንና ቤተሰቦቻችን እንጠብቅ።
በበሽታው የተጠቃ ሰውም ሌሎችን ላለመጉዳት የሚችለውን ሁሉ ማድረግና የባለሙያዎችን ምክር መስማት ግዴታ ይሆንበታል!

🔹ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረርሽኝ በሽታ መሞት ለሙእሚኖች *የሸሂድነትን ደረጃ* የሚያስገኝ በመሆኑም አማኞች ሆይ አብሽሩ !ሁሉም ለኸይር ነው!
 ዳሩ ሞት እንኳ ቢሆን "ኣኺራ ለሙተቆች ከዱኒያ ትሻላለች!"
በበሽታ የተያዘ ሁሉ ይሞታል ማለትም አይደለም!
ደግሞስ ተውሒድና ሱንና ላይ ከሆኑ መሞት ምን ችግር አለው?!
ሆን ብሎ ራስን ላደጋ ማጋለጥ ግን በዲኑ የተከለከለ ነው።
በመልካም ስራም እድሜ መርዘሙ ሌላ መልካም ነገር ነው።

🗞️በተረፈ የጠዋትና የማታ እንዲሁም በአጠቃላይ ከጊዜና ከሁኔታዎች ጋር ተያይዘው የሚባሉ ዚክርና ዱዓዎችን እናብዛ።ችግሮችን በሙሉ ማስወገድ የሚችለው ጌታ አላህ የመጣውን በላ እንዲያነሳልንም ዱዓ እናዘውትር።

🔸በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎችና የዘርፉ ተጠሪዎች የሚሰጧቸው መመሪያዎችን ከዲኑ እስካልተጋጩ  ድረስ በመከተል ከቀደር ወደ ቀደር እየሸሹ ራስንና ሌሎችንም መጠበቅ ተገቢ ነው እንላልን።

✍🏻ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ረጅብ 21/1441ዓ.ሂ@ዛዱል መዓድ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹

Post a Comment

0 Comments