Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መሃርታን መጠየቅ እና ተውሒድ

መሃርታን መጠየቅ እና ተውሒድ።
عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ  قَالَ: سَمِعْت رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ: قَالَ اللَّهُ تَعَالَى: "يَا ابْنَ آدَمَ! إِنَّكَ مَا دَعَوْتنِي وَرَجَوْتنِي غَفَرْتُ لَك عَلَى مَا كَانَ مِنْك وَلَا أُبَالِي، يَا ابْنَ آدَمَ! لَوْ بَلَغَتْ ذُنُوبُك عَنَانَ السَّمَاءِ ثُمَّ اسْتَغْفَرْتنِي غَفَرْتُ لَك، يَا ابْنَ آدَمَ! إنَّك لَوْ أتَيْتنِي بِقُرَابِ الْأَرْضِ خَطَايَا ثُمَّ لَقِيتنِي لَا تُشْرِكُ بِي شَيْئًا لَأَتَيْتُك بِقُرَابِهَا مَغْفِرَةً" .
📚 روَاهُ التِّرْمِذِيُّ [رقم:3540]، وَقَالَ: حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ
               የሓዲሱ ትርጉም
አነስ ኢብን ማሊክ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ አለ፦ አላህ እንዲህ አለ “አንተ የአደም ልጅ ሆይ!አንተኮ በጠራሃኝ እና መሃርታን በጠየቅከኝ ግዜ ካንተ ምንም ቢኖርም እምርሃለሁ ወንጀልህ ቢበዛም ምንም አይመስለኚም። አንተ የአደም ልጅ ሆይ!ወንጀልህ ሰማይ ቢደርስኳ መሃርታን ከጠየቅከኝ እምርሃለሁ። አንተ የአደም ልጅ ሆይ!አንተኮ ምድርን የሞላ ወንጀል ይዘህ በእኔ ግን ሳታጋራ ወደኔ ብትመጣ ከዚያም ብትገናኘኝ እኔም እሷን በሞላ መሃርታ ወዳንተ እመጣ ነበር።” 📚ሓዲሱን ቲርሚዚይ ዘግቦታል።
       ከሓዲሱ የምንወስዳቸው  አንኳር
                    ትምህርቶች
#• የሰው ልጅ ኣላህን በለመነ እና ከኣላህ በከጀለ ቁጥር ኣላህ እንደሚምረው። 
#• የኣላህ እዝነትን እንረዳለን። 
#• የሰው ልጅ ወንጀል ቢበዛም፣ ከኣላህ መሃርታን ከጠየቀ ኣላህ እንደሚምረው።  
#• ተውሒድ (ኣምልኮን ለኣላህ ብቻ ማድረግ እና ኣምልኮን ለኣላህ ብቻ ብሎ መስራት)በጣም ትልቅ ደረጃ እንዳለውና ወንጀላችንን እንድንማር እንደሚያደርግ።
✍️ አቡ ኢብራሂም
ተህሳስ 13/04/2012 ዓ ል
ረቢሳኒ 26/04/1441 ዓ ሂ

Post a Comment

0 Comments