Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ታላቅ መሪ እውነተኛ አፍቃሪ!

ታላቅ መሪ
እውነተኛ አፍቃሪ!

ብዙ ምላሶች ስለ ነብዩ ፍቅር አነብንበዋል ፤ እልፍ ብዕሮች ስለዚህ ታላቅ መሪ ውዴታ ከትበዋል! ገሚሱ በተግባር ውዴታውን ለመግለፅ ሲፍጨረጨር ገሚሱ ውዴታው ከተከሸኑ ቃላት ባለፈ ከላንቃው አልወርድ ብሎት ምላሱና ጣቶቹ ጫፍ ተንጠልጥሎ በተግባሩ እጅጉን ርቆ ይባስ ብሎ በተግባሩ አስተባብሏቸዋል!

 ከተለያዩ የቃላት ጋጋዎች ይልቅ ግን የዚህ እውነተኛ አፍቃሪ ሰሐቢይ ውዴታውን በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የገለፀበት አጋጣሚ እስከመጨረሻው ቀልቤን ገዝቶታል!

 ኹበይብ በመካ ጣዖታዊያን እጅ ከገባ በኃላ! ይህ ተከሰተ!

አቡ ሱፍያን (ከመስለሙ በፊት) እንዲህ አለው ፦

«ሙሐመድ ﷺ ባንተ ቦታ ሆኖ እሱን ብንገድለውና አንተ ከቤተሰቦችህ ጋር ብትሆን ትፈልጋለህን?» ብሎ ጠየቀው

ኹበይብም ፦

 «በፍፁም በአላህ እምላለሁ እኔ ከቤተሰቦቼ ጋር  ሆኜ ሙሐመድ ﷺ አሁን ባለበት ቦታ እሾህ እንዲነካው እንኳ አልፈቅድም»  ሲል መለሰ! ከዚያም ሰቀሉት! ረዲየላሁ ዐንሁ!

ማብራሪያ አይሻም!

ቀኑ ጁምዓ ነው እርሳቸውን ማውሳት እናብዛ !!!

ሁሌ የሚወሱ ድንቅ ነብይ!  እንዴታ ጌታቸውስ

"መወሳትህን ላንተ ከፍ አድርገንልሃል።" (95:4)

ብሏቸው የለ!

*اللــــــــهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد .اللـــــــهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد*

Post a Comment

0 Comments