Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መስጂድን መዳፈር መዘዙ ብዙ ነው!

መስጂድን መዳፈር መዘዙ ብዙ ነው!

🔸መስጂድ የተከበረ የአላህ ቤት ነው። መስጂድ ላይ ጥቃት የሚሰነዝርም የአላህና የአላህ ባሮች ጠላት ነው።
◼️አላህ ይታገሳል እንጂ አይረሳም! ጥፋተኞችን ሲይዝም አያያዙ ብርቱ ነው።
ሞትን እየተመኙ እንዳያገኙት ለሌሎችም መቀጣጫ ሆነው እንዲቀሩ ማድረግ ይችላል! አድርጓልም።
◼️መስጂድን መድፈር በመስጂዱ የሚገለገሉ ምዕምናንንም መናቅ ነው።
ይህ ደግሞ አብሮ በሰላም መኖር የሚፈልግ ሰው ስራ አይደለም።
🔸ኢስላም ማንንም ያለ አግባብ እንደማይነካው ሁሉ እርሱም መነካት የለበትም!
መስጂድን ማቃጠል በሌላ በኩል ደግሞ የአላህን እና የዲኑ ጠላቶችን የጥላቻቸውን ጥግ ማሳያም ነው።
◼️በንዴት ይሙቱ እንጂ የኢስላምን ስርጭትና የሙስሊሞችን ጥንካሬ መስጂዶችን በማቃጠል መግታት አይቻልም!
ዛሬ አንድ መስጂድ ቢፈርስ ወይም ቢቃጠል በምትኩ ሌላ ይሰራል! የአማኞች ልብ ላይም ብዙ መስጂዶች ይገነባሉ!
 "ከሃዲያን ቢጠሉም አላህ ብርኃኑን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያዳርሳል"
🔸ቁርኣን እና መስጂድን በማቃጠል ኢስላምን ለማጥፋት ሙስሊሞችን ለመጉዳት መሞከር የጸሐይን ብርሃን በእጅ ለመከለል እንዲሁም ጸሐይ ላይ ለመትፋት እንደመሞከር ነው!
በጫማ ምት ትልቅን ጋራ ለመናድ እንደመታገልም ነው!
ይህንንም ማድረግ ትርፉ ድካም ነው።
ሙስሊሞች ሆይ የመስጅድ መቃጠል ለኛ ትልቅ ፈተና ነው ሆኖም በፈተና ጊዜ ደግሞ ትዕግስትና ማስተዋል ፍሬው ብዙ ነው።
◼️ምንም ብንከፋና ውስጣችን ቢጎዳም በስሜት ተነሳስተን በሸሪዓ ያልተደገፈና እውቅና የሌለውን እርምጃ አንወስድም!
ይልቅ በመታገሳችን ከአላህ የተሻለን ነገር  ተስፋ እናደርጋለን።
የተሻለ ነገር የሚመጣበትን መንገድም አብረን እንፈልጋለን
ታላቁን መሳሪያችንም ሌት ተቀን በአግባቡ እንጠቀማለን።
🔹የሙስሊም ታላቁ መሳሪያው ምን ነበር?... መልሱን ለናንተው ልተወው!

  ሙስሊሞች ሆይ
እኛው እራሳችን በዘርና በድንበር እንዲሁም በስንዴና በብር ባንነቋቆር!
መች ይደፍሩን ነበር?!
ሐላል ሐራሙንስ አውቀን ብናከብር መች ነስሩን አጥተን የጠላት መጨወቻ እንሆን ነበር?!
አላህ ሆይ ዲንህን... ልባቸው የተሰበረ ባሮችህን... እርዳ!
የሸረኞችን ሴራ አክሽፍ
ለኛም ሰብርና ህብር ስጥ
✍🏻ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
25/4/1441ዓ.ሂ@ዛዱል መዓድ

Post a Comment

0 Comments