Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጂኖች ትክክለኛ ማንነት ፣ የሚያደርሱት ተጽዕኖና መድሃኒቱ



የጂኖች ትክክለኛ ማንነት ፣ የሚያደርሱት ተጽዕኖና መድሃኒቱ

ጥያቄ፡- የጂኖች ትክክለኛ ማንነት ፣ የሚያደርሱት ተጽዕኖና መድሃኒቱ ምን ይሆን?

መልስ፡- የጂኖችን ትክክለኛ ማንነት ከአላህ በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ ነገር ግን ጂኖች አካል እንዳላቸው ከእሳት እንደተፈጠሩ የሚበሉ የሚጠጡ የሚጋቡ እና ዝርያ ያላቸው መሆኑን እናውቃለን፡፡
ሰይጣናት ዝርያ እንዳላቸው አላህ ሲናገር፡-
أَفَتَتَّخِذُونَهُ وَذُرِّيَّتَهُ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِي وَهُمْ لَكُمْ عَدُوٌّ ۚ
“እነርሱንና ዘሮቹን እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ሲሆኑ ከእኔ ላይ ረዳቶች አድርጋችሁ ትይዛላችሁን?” (ከሕፍ፡ 50)

ጂኖች አላህን ለማምለክ የተፈጠሩ አካላት ናቸው፡፡ ጂኖች ከነብዩ ﷺ ዘንድ ተገኝተው ቁርዓንን አዳምጠዋል፡፡ ከነብዩ ﷺ የሰሙትን ለወገኖቻቸው አድርሰዋል፡፡
ይህን አስመልክቶ አላህ ሲናገር፡-
قُلْ أُوحِيَ إِلَيَّ أَنَّهُ اسْتَمَعَ نَفَرٌ مِّنَ الْجِنِّ فَقَالُوا إِنَّا سَمِعْنَا قُرْآنًا عَجَبًا (1) يَهْدِي إِلَى الرُّشْدِ فَآمَنَّا بِهِ ۖ وَلَن نُّشْرِكَ بِرَبِّنَا أَحَدًا
“(ሙሐመድ ሆይ!) በል “እነሆ ከጂን የሆኑ ጭፍሮች (ቁርአንን) አዳመጡ፡፡ እኛ አስደናቂ የሆነን ቁርአን ሰማንም አሉ፡፡” ማለት ወደእኔ ተወረደ፡፡ “ወደቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርዓን ሰማን)፡፡ በእርሱም አመንን፡፡ በጌታችንም አንድንም አናጋራም፡፡” (ጂን፡ 1-2)

አላህ አሁንም የሚከተለውን ተናግሯል፡-
وَإِذْ صَرَفْنَا إِلَيْكَ نَفَرًا مِّنَ الْجِنِّ يَسْتَمِعُونَ الْقُرْآنَ فَلَمَّا حَضَرُوهُ قَالُوا أَنصِتُوا ۖ فَلَمَّا قُضِيَ وَلَّوْا إِلَىٰ قَوْمِهِم مُّنذِرِينَ (29) قَالُوا يَا قَوْمَنَا إِنَّا سَمِعْنَا كِتَابًا أُنزِلَ مِن بَعْدِ مُوسَىٰ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ يَهْدِي إِلَى الْحَقِّ وَإِلَىٰ طَرِيقٍ مُّسْتَقِيمٍ
“ከጋኔን የሆኑን ጭፍሮች ቁርኣንን የሚያዳምጡ ሲሆኑ ወዳንተ ባዞርን ጊዜም (አስታውስ) ፡፡ በተጣዱትም ጊዜ ዝም ብላችሁ አዳምጡ ተባባሉ፡፡ በተጨረሰም ጊዜ አስጠንቃቂዎች ሆነው ወደ ሕዝቦቻቸው ተመለሱ፡፡ አሉም “ሕዝቦቻችን ሆይ! እኛ ከሙሳ በኋላ የተወረደን መጽሐፍ በፊቱ ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛ መንገድ የሚመራ የሆነን ሰማን፡፡” (አህቃፍ፡ 29-30)

የተወሰኑ የጂን ጀማዓዎች ወደነብያችን ﷺ በመሄድ ስለስንቃቸው ጠይቀዋቸው ነበር፡፡ የሚከተለውንም መልስ እንደሰጧቸው በሀዲስ ተረጋግጧል፡-

"لكم كل عظم ذكر اسم الله عليه يقع في أيديكم أوفر ما يكون لحما" رواه مسلم : 450
“የአላህ ስም ተነስቶበት ከእጃችሁ ላይ የሚወድቅ አጥንት ሁሉ ከነበረው እጅግ በዝቶ ስጋ ይሆንላችኋል፡፡” (ሙስሊም/450) (¹)

የሰው ልጅ ምግብ ሲመገብም ይሁን ሲጠጣ የአላህን ስም ካላወሳ በምግቡም ይሁን በመጠጡ (ከሐዲ) ጂኖች ይጋሩታ፡፡ ይህም ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ተረጋግጧል፡፡(²)

ስለዚህ ስንበላም ይሁን ስንጠጣ ቢስሚላህ ማለት ዋጅብ ይሆናል ማለት ነው፡፡
ጂኖች በዚህ ዓለም መኖራቸው የተረጋገጠ ነው፡፡ የእነርሱን መኖር መቃወም ቁርዓንን መቃወም ብቻ ሳይሆን በአላህም መካድ ነው የሚሆነው፡፡ ጂኖች ልክ እንደ ሰው ልጆች ይታዘዛሉ ይከለከላሉ፡፡ የጂን ከሀዲዎች እሳት ይገባሉ፡፡ የጂን አማኞች ደግሞ ጀነት ይገባሉ፡፡

የጂን ከሐዲዎች እሳት እንደሚገቡ የሚከተለው የቁርዓን አንቀጽ ያስረዳል፡-
قَالَ ادْخُلُوا فِي أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِكُم مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ فِي النَّارِ ۖ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا
“ከጋኔንም ከሰውም ከእናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ሕዝቦች ጋር ሆናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ” ይላቸዋል፡፡ አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር (ያሳሳተቻትን) ብጤዋን ትረግማለች፡፡” (አእራፍ፡ 38)

የጂን አማኞች ጀነት እንደሚገቡ የሚከተለው የቁርዓን አንቀጽ ያስረዳል፡-

وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ (46) فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ (47) ذَوَاتَا أَفْنَانٍ (48) فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
“በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? የቀንዘሎች ባለቤቶች የሆኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? (አር'ረህማን፡ 46-49)

ጂኖችን እና ሰዎችን የሚመለከተው የቁርዓን አንቀጽ ደግሞ የሚከተለው ነው፡-
يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا ۚ قَالُوا شَهِدْنَا عَلَىٰ أَنفُسِنَا ۖ وَغَرَّتْهُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا وَشَهِدُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا كَافِرِينَ

“የጋኔን እና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ! ፡- “አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን (ቅጣት) ማግኘትን የሚያስፈራሩዋችሁ ከእናንተው የሆኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን” (ይባላሉ)፡፡ “በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን ፤ (መጥተውልናል) “ ይላሉ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት አታለለቻቸው፡፡ በነፍሶቻቸውም ላይ እነርሱ ከሃዲዎች የነበሩ መሆናቸውን መሰከሩ፡፡”
(አል'አንዓም፡ 130) (³)

(ከሐዲ) ጅኖች በሰው ልጆች ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ መሆናቸው የተረጋገጠ እውነታ ነው፡፡ በሰው ልጅ ሰውነት ውስጥ ገብተው ሰዎችን በአውድቅ በሽታ ይጥላሉ፡፡ ያሸብራሉ ወይም ያስጨንቃሉ፡፡
በጅን ለተጠቃ ሰው መፍትሄው ሸሪዓዊ ዚክሮችን መዝከር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- እንቅልፍ ከመተኛት በፊት “አየተል ኩርስይን” ቀርቶ መተኛት፡፡
ለዚህ ማስረጃችን የሚከተለው የነብዩ ﷺ ሐዲስ ነው፡-
"من قرأ آية الكرسي في ليلة لم يزل عليه من الله حافظ ولا يقربه شيطان حتى يصبح" رواه البخاري 2311
“በሌሊት ውስጥ አየተል ኩርስይን የቀራ በእርሱ ላይ ከአላህ ጠባቂ አይወገድም፤ እስከሚነጋ ሰይጣን አይቀርበውም፡፡” (⁴)

الشيخ ابن عثيمين – فتاوى العلاج بالقرآن والسنة – الرقى وما يتعلق بها .
ص (67-69)


=======================================
(¹) ይህን የሚያጠናክርልን ኢማሙ ቲርሚዚይ የዘገቡት ሐዲስ ነው

عن عبد الله بن مسعود قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : " لا تستنجوا بالروث ولا بالعظام، فإنه زاد إخوانكم من الجن ".
سنن الترمذي\١٨

የባህር ዳር አህሉ ሱና መሻይኾች ገፅ, [23.12.19 07:01]
አብደሏህ ብን መስኡድ رضي الله عنه የሚከተለውን ሀዲስ ከረሱል ሰምተው አስተላልፈዋል:–
"ከጅን የሆኑ ወንድሞቻችሁ ስንቅ ነውና በፋንድያና በአጥንቶች አትፀዳዱ።"
(ቲርሚዚይ/18)

(²) ይህን የሚያመላክተው የሚከተለው የረሱል ﷺ ሐዲስ ነው

في صحيح مسلم عن جابر بن عبد الله ، أنه سمع النبي صلى الله عليه وسلم يقول : " إذا دخل الرجل بيته، فذكر الله عند دخوله، وعند طعامه قال الشيطان : لا مبيت لكم، ولا عشاء. وإذا دخل فلم يذكر الله عند دخوله قال الشيطان : أدركتم المبيت. وإذا لم يذكر الله عند طعامه، قال : أدركتم المبيت والعشاء ".

ጃቢር ብን ዓብዲላህ رضي الله عنه ከአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሰማውን ሐዲስ እንደሚከተለው አስተላልፏል፡-
((አንድ ሰው ቤቱ ሲገባና ምግብ ሲመገብ አላህን ከዘከረ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) “ማደሪያም ራትም የላችሁም፡፡” ይላቸዋል፡፡ ቤት ሲገባ አላህን ካልዘከረ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) “ማደሪያ አገኛችሁ፡፡” ይላቸዋል፡፡ ምግብ ሲመገብ አላህን ካልዘከረ ደግሞ ሰይጣን “ማደሪያም ራትም አገኛችሁ፡፡” ይላቸዋል፡፡)) ሙስሊም፡ 2018(103)

(³). ይህን በግልፅ የሚያሳይ የሆነው ሌላኛው የቁርአን አንቀፅ በሱረቱ`ል ጅን ላይ አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ጅኖች እንዲህ ማለታቸውን ይናገራል

وَأَنَّا مِنَّا ٱلْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا ٱلْقَٰسِطُونَۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُو۟لَٰئِكَ تَحَرَّوْا۟ رَشَدًا

«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አልሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡

وَأَمَّا ٱلْقَٰسِطُونَ فَكَانُوا۟ لِجَهَنَّمَ حَطَبًا

በዳዮቹማ ለገሀነም ማገዶ ኾኑ፡፡

(ሱረቱል ጅን/14‐15)

(⁴) አያተል ኩርሲ በመባል የሚታወቀው የቁርአን አንቀፅ...

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْحَىُّ ٱلْقَيُّومُۚ لَا تَأْخُذُهُۥ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌۚ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِۗ مَن ذَا ٱلَّذِى يَشْفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذْنِهِۦۚ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَىْءٍ مِّنْ عِلْمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَۚ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَۖ وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفْظُهُمَاۚ وَهُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْعَظِيمُ

አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡

https://t.me/alateriqilhaq

Post a Comment

0 Comments