መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች የተለያየ መልክ አላቸው።
① በሺርክ የተጨማለቁ መንዙማዎች የሚዘመሩበት፣ ደረሶች መብራት አጥፍተው የሚጨፍሩበት፣ የቀብር አፈር ለመድሃኒትነት፣ ለበረካ፣ ወዘተ የሚወሰድበት፣ ብልግናዎች የሚፈፀሙበት፣ በቀብር ዙሪያ ብዙ ጥፋቶች የሚፈፀምባቸው፣ ወዘተ መውሊዶች አሉ።
② መጣጥፍ፣ ግጥሞች፣ ነሺዳዎች፣ ወጎች፣ ታሪኮች የሚቀርቡበት "የተማሩ" ሰዎች መውሊድ አለ። ይሄ በመውሊድ ሰሞን አንዳንድ እንግሊዝኛ የሚቀላቅሉ ሰዎች አዳራሽ ተከራይተው የሚደግሱት "ዘመናዊ" መውሊድ ነው። እነዚህ ክፍሎች የሆነ ጊዜ ከኢራን ኤምባሲ (ከሺዐዎች) ጋር ጭምር የሚተባበሩበት ጊዜ ነበራቸው።
③ ሴት ከወንድ የሚቀላቀሉበት፣ ሴቶች ሻሻቸውን እያውለበለቡ ከወንዶች ጋር ተፋጠው የሚጨፍሩበት፣… ወዘተ መውሊድ አለ።
④ ተሰብስበው በልተው የሚበተኑበት መውሊድ።
⑤ የመሻይኾች መውሊድ፣ የሴቶች መውሊድ።

የጥፋቱ ክብደት አቅፎ እንደያዘው የቢድዐ፣ የሺርክና ሌሎች ወንጀሎች መጠን ቢለያይም ሁሉም ግን ቢድዐና ጥመት ነው። ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(كل بدعه ضلالة ، وكل ضلالة في النار)
{ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ ወደ እሳት ነው።} [ሶሒሕ ሙስሊም።]
•
ሶሐባው ኢብኑ ዑመርም ረዲየላ፞ሁ ዐንሁ {ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው። ሰዎች መልካም ነው ብለው ቢያስቡትም} ብለዋል። [ዳሪሚ ዘግበውታል።]

0 Comments