Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰው ከሞተም በኃላ የልደት በዓሉ ይከበርለታል ?




መውሊድ?

ነብዩ ከሞቱ ከ1400 አመት በላይ ተቆጥሯል፡፡
ሰው ከሞተም በኋላ የልደት በአሉ ይከበርለታልን?
እንደ ውቡ፣ ሙሉው እስልምና ከሆነ፣ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተወለዱበትን ቀን አመት ጠብቀው በህይወት በነበሩበት ጊዜ እንኳን አንድም ጊዜ የራሳቸውንም ይሁን የሌሎች ነብያትን ወይንም የሌላን ግለሰብ አላከበሩም፡፡ አይደለም ሰው ሞቶ ልደቱ ሊከበር ቀርቶ፡፡
ግን አሳዛኙ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተወለዱበት ቀን በቁርጥ ባይታወቅም፣ የሞቱበት ቀን ግን አሁን ሰዎች ረቢአል አወል 12 እያሉ የሚጨፍሩበት ቀን ነው፡፡ እውነት የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወዳጅ የሞቱበትን ቀን የሺርክ ስንኝ ሲያቀነቅንበት፣ ሴት እና ወንድ ተደባልቆ ሲያጨበጭብ ሲጨፍርበት፣ ጫት ሲቅምበት ይውላል? ሰይጣን ይህን ያህል የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ዲን ነብዩን እንወዳለን በሚል ስም ሲንዱት ተግባራቸውን አሳምሮ አቀረበላቸው፡፡

አላህ በሱና ከሚብቃቁት ያድርገን፡፡ የነብዩን ሱና በቢድኣ ከመናድ ይጠብቀን፡፡

Post a Comment

0 Comments