Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሺርክ ዶፍ ከሙሐመድ አወል መንዙማ

የሺርክ ዶፍ ከሙሐመድ አወል መንዙማ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
"ጌታዬ ለመንኩህ ባንቢዎቹ ስር
በሩሱል ባውሊያ አንድ እንኳን ሳይቀር
አቤት ብየ ልጩህ እባሮቹ በር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(وَيَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنْفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِنْدَ اللَّهِ ۚ قُلْ أَتُنَبِّئُونَ اللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ)
((ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይገዛሉ፤ እነዚህም አላህ ዘንድ #አማላጆቻችን ናቸው ይላሉ። «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡)) ዩኑስ፡ 18

"ቀልቤን ወደሳቸው አድርጌ ሰንዘር
አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنْ يَدْعُو مِنْ دُونِ اللَّهِ مَنْ لَا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَنْ دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ)
((ከአላህ ሌላ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ መልስ የማይሰጠውን እንደሚጣራ ሰው የጠመመ ማነው እነሱ ከመጠራታቸው የዘነጉ ሆነው ሳለ)) (አልአሕቃፍ፡ 5)

"ተሙስጠፋ ይዤ እስተ አቡል በሸር
አንቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ)
((እነዚያ ከሱ ሌላ የምትጠሯቸው የናንተው አምሳያ ባሪያዎች ናቸው፡፡ ጥሯቸው እስኪ ይመልሱላችሁ እውነተኞች ከሆናችሁ)) (አዕራፍ፡ 194)

"ደሞ አራተኛቸው ዐልዩ ሐይደር
ነበረ ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር
ዒልመል ገይብ ተሱ ይጠየቅ ነበር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(قُلْ لَا يَعْلَمُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ ۚ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ)
(በሰማያትም በምድርም ያለን የሩቅን ምስጢር አላህ እንጂ ማንም አያውቅም፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም በላቸው) (ነምል፡ 65)

"በዘበን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር
ቀኝ አጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِنْ شِرْكٍ وَمَا لَهُ مِنْهُمْ مِنْ ظَهِيرٍ * وَلَا تَنْفَعُ الشَّفَاعَةُ عِنْدَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ ۚ حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَنْ قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ)
((እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በነሱ ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡)) (ሰበእ: 22-23)

"ሺሊላ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር
መቼም አለናንተ ሁሉም አያምር
በናንተ የሸሸ ምነዜም አያፍር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِنْ دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنْكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنْكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ)
((የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር))፡፡ (አል-ዐንከቡት፡ 41)

"ጌቶቼ አትለፉኝ አደቤም ባያምር
አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር
ባሪያ ሲባል ማጥፋት እለት ነው እድር
ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር
ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር
በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(لَهُ دَعْوَةُ الْحَقِّ ۖ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُمْ بِشَيْءٍ إِلَّا كَبَاسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى الْمَاءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَالِغِهِ ۚ وَمَا دُعَاءُ الْكَافِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَالٍ)
((እውነተኛ ጥሪ ለሱ ነው፡፡ እነዚያም ከሱ ሌላ የሚጠሯቸው በምንም ነገር መልስ አይሰጧቸውም፤ ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ (ከሩቅ ሆኖ) ወደ ውሃ መዳፎቹን እንደሚዘረጋ ሰው ምሳሌ እንጂ፡፡ ነገር ግን ወደ አፉ ደራሽ አይደለም፡፡ የከሃዲዎችም ጥሪ ከንቱ እንጂ (ሌላ) አይደለም፡፡)) (አል-ረዕድ፡ 14)

"ሊለግስ ነው መሰል ዳመናው ዟዟረ
የስልካችሁ ንባብ ይሰማ ጀመረ።"

አላህ ግን የኢብራሂምን ንግግር እንዲህ ይተርክልናል፡-
(الَّذِي خَلَقَنِي فَهُوَ يَهْدِينِ * وَالَّذِي هُوَ يُطْعِمُنِي وَيَسْقِينِ * وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ * وَالَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحْيِينِ * وَالَّذِي أَطْمَعُ أَنْ يَغْفِرَ لِي خَطِيئَتِي يَوْمَ الدِّينِ * رَبِّ هَبْ لِي حُكْمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ * وَاجْعَلْ لِي لِسَانَ صِدْقٍ فِي الْآخِرِينَ * وَاجْعَلْنِي مِنْ وَرَثَةِ جَنَّةِ النَّعِيمِ * وَاغْفِرْ لِأَبِي إِنَّهُ كَانَ مِنَ الضَّالِّينَ * وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَ * يَوْمَ لَا يَنْفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ * إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ)
((እርሱ ያ የፈጠረኝ ነው፡፡ እርሱም ይመራኛል፡፡ ያም እርሱ የሚመግበኝና የሚያጠጣኝ ነው፡፡ በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል፡፡ ያም የሚገድለኝ ከዚያም ህያው የሚያደደርገኝ ነው፡፡ ያም በፍርዱ ቀን ወንጀሌን እንዲምርልኝ የምከጅለው ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ! ጥበብን አድለኝ፡፡ ከደጋጎቹም አስጠጋኝ፡፡ ከኋለኞቹ ትውልዶችች ዘንድም መልካም ዝናን አድርግልኝ፡፡ ሰቀንም አታዋርደኝ፡፡ ያኔ ገንዘብም ልጆችም የማይጠቅሙበት በሆነው ቀን፡፡ ወደ አላህ በንፁህ ልብ የመጣ ሰው ቢሆን እንጂ፡፡)) (አሽሹዐራእ: 78–89)

"አህለል በይት ሁላ ተዳር እስተዳር
ሁሉም ባንድ ሁኖ እሞስጦፋ ጋር
ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ لَنْ يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِنْ يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَا يَسْتَنْقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ)
((እናንተ ሰዎች ሆይ! ምሳሌ ቀርቧልና አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው ዝንብ አይፈጥሩም፣ ለዚሁ አላማ ቢሰበሰቡ እንኳን፡፡ ዝንቡ የሆነን ነገር ቢነጥቃቸውም አያስጥሉትም፡፡ ከጃይም ተከጃይም ደካሞች ናቸው፡፡)) (አል-ሐጅ፡ 73)
((ወይስ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ ማነው? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡)) (ነምል፡ 62)

"ሙሐመዱሰማን ገፍታሪው ቀደር
የመዕሪፋ አረቂ አቅምሶ እሚያሰክር።"

ሱብሓነላህ!!
(وَلَا يَحْزُنْكَ الَّذِينَ يُسَارِعُونَ فِي الْكُفْرِ ۚ إِنَّهُمْ لَنْ يَضُرُّوا اللَّهَ شَيْئًا ۗ يُرِيدُ اللَّهُ أَلَّا يَجْعَلَ لَهُمْ حَظًّا فِي الْآخِرَةِ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ)
((እነዚያም ወደ ክህደት የሚቻኮሉት አያሳዝኑህ፡፡ እነርሱ ፈፅሞ አላህን በምንም አይጎዱምና፡፡ )) (ኣሊ ዒምራን፡ 176)

Post a Comment

0 Comments