Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቁርኣንን ስታዳምጥ ልብህ ወዴት ያመዝናል?


ቁርኣንን ስታዳምጥ ልብህ ወዴት ያመዝናል?
🖤⇄⇄⇄⇄⇄💚
እያንዳንዱ ሰው የራሱን ዝንባሌ ማወቅ ይችላልና ማወቅ አለበት። ህያው የሆነች ልብ ካለው ቁርኣን ሲነበብና ስትሰማ መልካም የሆነን ስሜት ታንፀባርቃለች። ይጥማታል። ትኩረቷን ይስባል። ደስደስ ይላታል። እንደ መልዕክቱ ደንገጥገጥም ያደርጋታል። በዚህ አይነት እያናገራት ያንቀሳቅሳታልና በነበራት መልካም ዝንባሌ ላይ እንድትገፋ ኢማኗን ይጨምራል። አላህ ለዚህ ያግራን።
ዝንጉ የሆነች ልብ ደግሞ እንደ ድክመት ደረጃዋ ይኸን ያህል ስሜት አይሰጣትም። ሰማች አልሰማች መልካም ለውጥ አይነበብባትም። የቁርኣን ኸበር አያስደነግጣት፣ ማስጠንቀቂያው አያስፈራት፣ ሽልማቱ አያጓጓት። እዚህ ግባ የሚሉት እንቅስቃሴ አይንፀባረቅባትም። ከዚህ አይነቱ ውድቀት አላህ ይጠብቀን።
ይህንኑ በተመለከተ ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሷሊህ ኢብን ዑሰይሚን ረሂመሁላህ አጠር ባለ ገለፃ ሲያስረዱና ራሳችንን እንድንለይ ሲጠቁሙ አንቀፁን በመተረጎም ይጀምራሉ☞
”وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ“ ۩ (الإنشقاق: 21)
{“በነሱ ላይ ቁርኣን በሚነበብበት ግዜ አይሰግዱም። (ለአላህ አይተናነሱም)” ብሏል። እዚህ ቦታ ላይ ስግደት የሚለው ቃል ትርጉሙ ለአላህ መተናነስ ለማለት ነው።
ወንድሜ ሆይ እስኪ ራስህን ሞክረው። ለመሆኑ ቁርኣን ሲነበብብህ ልብህ ለስለስ ዝቅ ይላልን? እንደዚያ ከሆነ አንተ ከነዚያ
”وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا“ (الأنفال: 2)
“አንቀፆቹ ስትነበነብባቸው ኢማንን ጨመረችላቸው።” ከተባሉት ነህ።
ልብህ እንደዚያ ካልሆነ ግን
”وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ“ ۩ (الإنشقاق: 21)
“በነሱ ላይ ቁርኣን በሚነበብበት ግዜ አይሰግዱም (አይተናነሱም።)” ከተባሉት ጋር የሚያመሳስል ነገር አለብህ ማለት ነው።} ብለዋል።
‏⁧ [الشيخ ابن عثيمين ⁩ رحمه الله]
በዚህ መልኩ እያንዳንዳችን ልቦናችንን፣ ዝንባሌያችንን መርምረን እንድንታከም አስታውሰዋልና የትነው ያለነው?
‏(وإذا قرئ عليهم القرآن لايسجدون): ‏أي :لا يخضعون لله، فالسجود هنا بمعنى الخضوع لله. ‏وجرب نفسك-ياأخي- إذا تلي عليك القرآن هل يلين قلبك ويذل ‏فإن كان كذلك فأنت ممن إذا تليت عليهم آياته زادتهم إيمانا. ‏وإن لم يكن قلبك كذلك ففيك شبه من الذين إذا قرئ عليهم القرآن لا يسجدون.
[الشيخ ابن عثيمين ⁩ رحمه الله]
💬💬💬💬
✍🏽Abufewzan
ዙል ቂዕዳ 29/1439
Aug 11 /2018

Post a Comment

0 Comments