⭐የሰለፎች ግንዛቤ ማለት ለምን አስፈለገ?!
💥 የደዕዋ መሰረቱ
ሶስት ምሰሶዎች ናቸው
ሶስት ምሰሶዎች ናቸው
1- ቁርኣን
2-ሰሒሕ ሐዲሥ
3- ቁርኣንና ሐዲሥን በሰሓባዎችና በተከታዮቻቸው/ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መሰረት መረዳት ናቸው!
2-ሰሒሕ ሐዲሥ
3- ቁርኣንና ሐዲሥን በሰሓባዎችና በተከታዮቻቸው/ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መሰረት መረዳት ናቸው!
💥("መስመር የሳቱና የጠመሙ ግሩፖች የቀድሞዎችም ይሁን አዳዲሶች የመጥመማቸው ሰበብ እነዚህን ሶስት መሰረቶች በሚገባ አለመያዛቸው ነው")
📂አል ኢማም አልባኒይ ረሒመሁላህ (አል አሷለ ገጽ 27
📂አል ኢማም አልባኒይ ረሒመሁላህ (አል አሷለ ገጽ 27
በዘመናችን ያሉ አንዳንድ ዳዒ ነኝ ባይና በዲናቸው የሚጫወቱ ሰዎች ዲኑና ደዕዋውን እንዳሻቸው ለማድረግ እንዲመቻቸው("የደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ የሚባል ነገር የለም ሁሉም የራሱን ግንዛቤ መከተል ይችላል") ይሉናል!
አላህን ፍሩ ሐቅን ከባጥል አትቀላቅሉ ዐቂዳና እምነትን በተመለከተ ከሰለፎች መንገድና ግንዛቤ መብቃቃት በፍጹም አይቻልም
💥አራቱ የዲን መሪዎችም ይሁኑ ሌሎች የዲን መሪዎች/ኢማም ወይም መሪ የተባሉት የደጋግ ቀደምቶችን/የሰለፎችን ግንዛቤ ትተው ለራሳቸው አዲስ መንገድ ፈጥረው አይደለም ይልቁንስ እያንዳንዳቸውም የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ እንድንከተል አደራ ብለዋል!
በየትኛውም ዘመን ላይ ወቅታዊና የፊቅህ ጉዳዮች ላይ ከቁርኣንና ከሐዲሥ ግልጽ የሆነ መመሪያ ካልተገኘ ብቃቱ ያላቸው ዓሊሞች (የት፣ እንዴትና ማን ጋር እንደቀሩ የማይታወቁ በምናቸውም ከዓሊሞች ጋር የማይመሳሰሉ በዲን ተጫዋቾች ሳይሆን) ዓሊሞች ማስረጃዎችን ካገላበጡ በኋላ አላህን ከመፍራትና ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር የራሳቸውን አስተያየት ሊያስቀምጡ ይችላሉ እንጂ ሁሉም ዲኑን በራሱ አቅል እንደመሰለው መረዳት ይችላል አይባልም
በራሴ ግንዛቤ መብቃቃት እችላለሁ የሚል ሰውም ጥመት ላይ ነው ያለው ተጠንቀቁት!
ምክንያቱም ሁሉም የራሱ የሆነ ጭንቅላትና ከሌሎች የተለየ አስተሳሰብ አለው የዕምነት ጉዳይ ላይ ሁሉም በመሰለውና በራሱ ግንዛቤ መሰረት ይጓዝ ማለት ደግሞ በዲን ላይ መለያየትና መከፋፈል እንዲመጣ ያደርጋል።
ሰዎችን አንድ ሊያደርግ የሚችለው በቅንነት አላህ የመሰከረላቸውን የደጋግ ቀደምቶችን ግንዛቤ መሰረት አድርገን ቁርኣንና ሐዲሥን ስንከተል ብቻ ነው

💥እንንቃ ያብለጨለጨ ሁሉ ወርቅ አይምሰለን ዓረቢኛ ያወራ ሁሉም ወደ ሐቅ ተጣሪ አይምሰለን❗
✍ ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
23/7/1438ዓ.ሂ@ዛዱልመዓድ
23/7/1438ዓ.ሂ@ዛዱልመዓድ
0 Comments