የሸህ አህመድ የህልም ደብዳቤ
https://islamqa.info/en/31833
https://islamqa.info/en/31833
የሸህ አህመድ ደብዳቤ እየተባለ የሚሰራጨውን መልእክት በተመለከተ
የኢስላም ሊቃውንት ውሸትነቱን አስረድተዋልና ከማሰራጨት እንቆጠብ።
የኢስላም ሊቃውንት ውሸትነቱን አስረድተዋልና ከማሰራጨት እንቆጠብ።
☞ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) ምንጭ፡- አል-ኢስላሙ ሱአሉን ወጀዋብ ጥያቄ ቁ 31833
https://www.binbaz.org.sa/article/26
https://www.binbaz.org.sa/article/26
☞ ሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን
http://www.alfawzan.af.org.sa/node/3736
http://www.alfawzan.af.org.sa/node/3736
አያሌ ስህተቶች ያሉበት ሲሆን ጥቂቶቹን
ከአንድ ወንድም ፅሁፍ ቀንጭቤ ላቅርብላችሁ።
ከአንድ ወንድም ፅሁፍ ቀንጭቤ ላቅርብላችሁ።
1ኛ ስህተት፦ የነቢያችን ሸፋዐ ትርኪ ምርኪ ያዘለ ወረቀት በማባዛት አይገኝም፡፡ የሳቸው ሸፋዐህ ከሚገኝባቸው መንገዶች መካከል፡-
ሀ. ከኡመታቸው ውስጥ በአላህ አምልኮ ላይ ምንንም ማንንም ሳያጋራ በተውሒዱ ላይ ጸንቶ የሞተ፡፡ ሙስሊም የዘገበው፡ ከአቢ ሁረይራህ ሐዲሥ ቁ 338.
ሀ. ከኡመታቸው ውስጥ በአላህ አምልኮ ላይ ምንንም ማንንም ሳያጋራ በተውሒዱ ላይ ጸንቶ የሞተ፡፡ ሙስሊም የዘገበው፡ ከአቢ ሁረይራህ ሐዲሥ ቁ 338.
ለ. ከልቡ በኢኽላስ "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" ያለ ሰው፡፡ ቡኻሪይ የዘገበው፡ ከአቢ ሁረይራህ ሐዲሥ ቁ 99
ሐ. ከአዛን በኋላ ያለውን ዱዓ ያደረገ፡ ቡኻሪይ የዘገበው፡ ከጃቢር ኢብኒ-ዐብዲላህ ሐዲሥ ቁ 614
اللَّهُمَّ رَبَّ هَذِهِ الدَّعْوَةِ التَّامَّةِ وَالصَّلَاةِ الْقَائِمَةِ آتِ مُحَمَّدًا الْوَسِيلَةَ وَالْفَضِيلَةَ وَابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا الَّذِي وَعَدْتَهُ
اللَّهُمَّ رَبَّ هَذِهِ الدَّعْوَةِ التَّامَّةِ وَالصَّلَاةِ الْقَائِمَةِ آتِ مُحَمَّدًا الْوَسِيلَةَ وَالْفَضِيلَةَ وَابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا الَّذِي وَعَدْتَهُ
መ. በሳቸው ሀገር በመዲና የኑሮም ይሁን ሌሎችን ችግሮችን በመቋቋም ጸንቶ የኖረና እዛው የሞተ ሙስሊም፡፡ ሙስሊም የዘገበው፡ ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ ሐዲሥ ቁ 477
ሠ. የሱንና ሶላቶችን ማብዛት፡፡ ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ሐዲሥ ቁ 16076
2ኛ ስህተት፡- ወረቀቱን ያባዛ አንድ ሰው ብዙ ዕድሎች ገጠሙት ይላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በኢስላም ዕድል የሚባል ነገር የለም፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የሚከናውኑ ክስተቶች ሁሉ አላህ ዘንድ ቀድሞ በታወቀው፡ ለውሐል መሕፉዝ ላይ በተጻፈው፡ አላህ በሻውና በፈቀደው መልኩ የቀዷ ወል-ቀደር ውጤት ናቸው እንጂ፡ እድል እና አጋጣሚ የሚባል ነገር የለም፡፡ እንደ ሰበብ ለመጠቀምም ካስፈለገ፡- አላህን መፍራት፡ ዝምድና መቀጠል፡ ሐላል ሪዝቅን ብቻ መከጀል እንጂ የወረቀት ኮፒ የስራ ዕድልን አያሰፋም፡፡
3ኛ ስህተት፡- ወረቀቱን ከማባዛት ችላ ያለው ሰውዬ ደግሞ፡ በዚህ ሰበብ በዘጠነኛው ቀን ሞተ ይላል፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ የምትሞተው አላህ የወሰነላትን ምድራዊ ቆይታ ስትጨርስ ብቻ ነው (አሊ-ዒምራን 145)፡፡ ሰዓቱ ሲደርስ ወደፊት ወደኋላ የለም፡፡ እንዴት የወረቀት ኮፒ አለማድረግ ለሰውየው ሞት ምክንያት ይሆናል? እስኪ ይሄ ወረቀት ደርሷቹ ችላ ያላችሁት ወይንም ቀዳችሁ የጣላችሁ ወንድምና እህቶች የላችሁም? ዘጠኝ ቀኑ አላለፈም እንዴ?
4ኛ ስህተት፡- ወረቁቱን ያሰራጨ ሰው ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀውን ነገር ያያል፡፡ ምንድነው ያልታየ ነገር እንደ አዲስ ማየት የሚጀምረው? እውነት በወቅቱ ወረቀቱን ባለማወቅም ይሁን በመፍራት ያሰራጨ ሰው አዲስ ነገር ማየት ጀምሯል? ለምንድነው ሰውን በፍርሀት ትብታብ ውስጥ መክተት ያስፈለገው?
Lies about a dream falsely attributed to the Watchman of the Prophet’s tomb
https://islamqa.info/en/31833
https://islamqa.info/en/31833
ሀሰት ከማሰራጨት እንቆጠብ!!
Abujunaid
Http://www.nesiha.com
Http://www.nesiha.com
0 Comments