(አጠር ያለ የሐጅና ዑምራ አፈጻጸም)
ካለፈው የቀጠለ)የዙልሂጃ ስምንተኛው ቀን ላይ ከኢሕራማቸው የተፈቱ ሰዎች ካሉበት ቦታ በመሐረም ከዙህር በፊት ሁሉም ወደ ሚና በመጓዝ እዛ ተደርሶ ከዙህር ሰላትን ጀምሮ ሁሉንም በወቅቱ ሁለት ሁለት ረክዓ ይሰገዳል:: ዕለቱን በተልቢያና በዚክር እያሳለፉ እዛው ታድሮ በማግስቱ ጸሃይ እንደወጣች ወደ ዓረፋ ተራራ (ሜዳ) ጉዞ ይደረጋል እዛም ዙህርና አስርን በማሳጠርና ሁለቱም በዙህር ሰላት ወቅት ላይ ከተሰገዱ በኋላ ጸሃይ እስክትጠልቅ ድረስ ዱዓ እየተደረገ ይቆያል!!
ሀጅ ላይ ላልሆነ ሰው ይህን ቀን መጾም ሱናና ትልቅ አጅር የሚያሰጥ ሲሆን ሀጅ ላይ ያለ ሰው አይጾምም
ይልቁንስ እየበላና እየጠጣ ዱዓና ዚክር ላይ መበርታት ይኖርበታል::
የዚህን ቀን እድል ብዙ ሰዎች ተሰብስበው እያወሩና እየተጫወቱ ስያሳልፉት ይታያል! ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ግመላቸው ላይ ሆነው ዱዓ እያደረጉ ሳለ የግመላቸው ገመድ (ልጓም) አምልጧቸው ወድቆ አንድ እጃቸው ወደ ሰማይ እንደተነሳ በሌላኛው እጃቸው ነበር ያነሱት ( ለቅጽበት እንኳ ዱዓውን ማቋረጥ አልፈለጉም! ከደከመን ሀላል በሆነ መልኩ የተወሰነ እረፍት ብናደርግ ምንም ችግር የለውም:: አሏህ ብዙ ሰዎችን የሚምርበት ዕለት በመሆኑም ሸይጧን የሚያፍርበትና የሚናደድበትም ቀን ነው:: የአሏህን ምህረት እናገኝ ዘንድ እራሳችንን ማዘጃገትና እሱንም መለማመጥ ይጠበቅብናል:: በተለይም ከቀኑ የመጨረሻው ሰዓት ላይ!!!
ይሄንን ምርጥና አስኳል ሰዓትም እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች ቀደም ብለው ለመውጣት እየቸኮሎ በአግባቡ አይጠቀሙትም!!
ልክ ጸሃይ መጥለቋ እንደተረጋገጠ ወደ ሙዝደሊፋ ጉዞ ይጀመራል እዛም እንደተደረሰ መግሪብና ኢሻ አንድ ላይ ይሰገዳል:: መንገድ ላይ ከረፈደና ሙዝደሊፋ ሳይደረስ እኩለ ሌሊት ያልፋል ተብሎ ከተሰጋም በደረሱበት ሰላቶች ይሰገዳሉ::
ሙዝደሊፋ እንደተደረሰም እረፍት ተደርጎ ይታደርና በማግስቱ ሱብሂ ከተሰገደ በኋላ እስኪነጋጋ ድረስ ዱዓና ዚክር እየተደረገ ተቆይቶ ከዛም ወደ ሚና ጎዞ ይጀመራል
አቅመ ደካሞችና ከነሱ ጋር አብረው የሚጓዙ ሰዎችም ከእኩለ ሌሊት በኋላ ሙዝደሊፋን ለቀው በመውጣት ወደ ሚና መሄድ ይፈቀድላቸዋል::
ሚና እንደተደረሰም ተልቢያ / ለበይከሏሁመ ለበይክ/ ማለትን በማቆም (የጀምረቱል ዐቀባ) ጠጠር ይወረወራል:: የሚወረወረው 7 ፍሬ ባቄላ የሚያካክል ጠጠር ሲሆን እሱንም ከፈለጉት ቦታ መልቀምና መሰብሰብ ይቻላል ከእየንዳንዱ ጠጠር ጋር አሏሁ አክበር የሚባል ሲሆን በትክክል ጉርጓዱ ላይ መግባት አለመግባቱን ማረጋገጥ የግድ ይሆናል ሰባቱን በአንድ ግዜ መወርወር አይቻልም እዚህ ጋር እንደተወረወረ ዱዓ አይደረግም ቦታውም ላይ አይቆምም ወርወረው እንደጨረሱ ወዲያው ከቦታው ዞር ማለት ተገቢ ነው::
ከዛም ሀዲይ የያዘ ወይም ያለበት ሰው ያርዳል ከዛም ወንዶች ጸጉራቸውን በምላጭ ካልሆነም በመቀስ ወይም በማሽን ያስነሳሉ ሴቶች ደግሞ ጸጉራቸውን ወደ ኋላ ወይም ወደፊት ሰብስበውት ከጫፉ ሁለት ሳንቲ ሜ/ር ያህል ይቆርጣሉ::
እነዚህን ከተደረጉ በኋላ በሀጅና ዑምራ ምክንያት ተከልክለው የነበሩ ነገሮች በሙሉ ይፈቀዳሉ { የተቃራኒ ጾታ ግንኙነትና በስሜት መነካካት ሲቀር}
ከዛም ወደ ከዓባ በመመለስ ጠዋፈል ኢፋዷ እንዲሁም ቀድሞ የሀጅ ሰዕይ ያላደረገ ሰው ከሆነም ሰዕይ በማድረግ በሀጅና ዑምራ ምክንያት ተከልክለው የነበሩ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ይፈቀዳሉ::
ከዛም ወደ ሚና በመመለስ ተከታታይ ሶስት ቀናትን እዛው እየዋሉና እያደሩ በየቀኑ ሶስት ጉርጓዶች ላይ እያንዳንዱ ጉርጓድ ላይ 7 ጠጠር ከላይ በተዘረዘረው መሰረት እየወረወሩ ይቆያል:: የሚቸኩል ሰው ከኢድ ቀን ውጪ ሁለት ቀን ብቻ ከቆይ በኋላ ሁለተኛው ቀን ላይ ጸሃይ ከመጥለቋ በፊት ሚናን ለቆ መውጣት ይችላል መውጣት እየፈለግ ሳይወጣና ጉዞ ሳይጀምር ጸሃይ የጠለቀች እንደሆነ እዛው ማደርና ቀጣዩንም ቀን እዛው በመዋል ጠጠር መወርወር ይጠበቅበታል::
የሚና ቀናት ካበቁ በኋላ ሚናን በመልቀቅ ወደ መካ ጉዞ ይደረጋል ወዲያው ወደ መጡበት ሀገር የሚመለሱ ወይም መካን ለቀው የሚወጡ ከሆነ ወደ ሀረም (ከዕባ) በመግባት ጠዋፈል ወዳዕ ማድረግ ግዴታ ይሆናል ይሄን ጠዋፍ የወር አበባና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች ትተውት ቢሄዱ ምንም ችግር የለውም::

በዚህም ሐጅ ይጠናቀቃል!!!
ሐጂ! ሐጆን አሏህ ይቀበሎት" እናም ለፍተው፣ ደክመውና አሏህ ወፍቆዎት የሰሩትን ሀጅ በይዩልኝና በይስሙልኝ አያበላሹት!!
ከወንጀሎ ከጸዱ በኋላም ዳግም ወደ ወንጀል ተመልሰው ልቦን አያቁሽሹ!!
ከወንጀሎ ከጸዱ በኋላም ዳግም ወደ ወንጀል ተመልሰው ልቦን አያቁሽሹ!!
=== ማሳሰቢያ፥ ይህ እጅግ በጣም አጠር ተደርጎ የተዘጋጀ ጽሁፍ ሲሆን ለበለጠ መረጃ (የሐጅና ዑምራ አፈፃጸም) በሚል ርእስ የተለቀቁ 3 ተከታታይ ኦዲዮዎችን ያድምጡ