Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ ከአርሽ በላይ ስለመሆኑ የኢማም ማሊክ ድንቅ ምላሽ



አላህ ከአርሽ በላይ ስለመሆኑ 
የኢማም ማሊክ ድንቅ ምላሽ

የአላህ ከዓርሽ በላይ መሆንን በተመለከተ፤ አላህ ከዓርሽ በላይ መሆኑን ማመን ተፈጥሯዊ እምነት እንደሆነ እና በዚህ ላይ የሚነሱ ማምታቻዎችና ብዥታዎች የፈጠራ ሰዎች መገለጫ መሆናቸውን ታላቁ የነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም መስጅድ አስተማሪ እና የመዝሀብ መሪ የሆኑት አል-ኢማም ማሊክ ኢብኑ አነስ ገልጸዋል። 

ስለ አንቀጹ ተጠይቀው የመለሱት ምላሽ እንደሚከተለው ይነበባል።

ﻗﺎﻝ ﺍﻷﻣﺎﻡ ﻣﺎﻟﻚ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ - ﻭ ﻗﺪ ﺳﺌﻞ ﻋﻦ ﻗﻮﻟﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ
ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﺳْﺘَﻮَﻯ
ﻛﻴﻒ ﺍﺳﺘﻮﻯ؟ ﻓﻘﺎﻝ ‏« ﺍﻻﺳﺘﻮﺍﺀ ﻏﻴﺮ ﻣﺠﻬﻮﻝ، ﻭﺍﻟﻜﻴﻒ ﻏﻴﺮ ﻣﻌﻘﻮﻝ، ﻭ ﺍﻹﻳﻤﺎﻥ ﺑﻪ ﻭﺍﺟﺐ، ﻭ ﺍﻟﺴﺆﺍﻝ ﻋﻨﻪ ﺑﺪﻋﺔ
ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﺳْﺘَﻮَﻯ

“አረሕማን ከዐርሽ በላይ ሆነ (ከፍ አለ)” (ጣሃ 5)

ኢስቲዋዕ እንዴት እንደሆነ ተጠየቁ።

“አላህ ከዓርሽ በላይ ከፍ ያለው እንዴት ነው?” ተባሉ። እርሳቸዉም እንዲህ ብለው መለሱ፦ “የአላህ ከዓርሽ በላይ መሆን “ኢስቲዋዕ” ለማንም ሰው ግልጽ ነው። ‘እንዴት?’ የሚለው ጥያቄ በአዕምሮ ምርምር የሚደረስበት አይደለም፤ ይህንንም ተቀብሎ ማመን ግዴታ ነው፤ ስለዚህ መጠየቅ በዲን ዉስጥ የመጣ ፈጠራ “ቢድዓ” ነው” ። 

📚 [ይህ አሰር ሰሂህ ነው። አል-ኢማም አለለካዒይ “ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሊሱናህ” በተባለው መጽሀፍ ቅጽ 2 ገጽ 398 ፣
ዳሪሚይ “አል ረድ አለልጃህሚያህ” ገጽ 33 ፣
አልበይሀቂይ “አል አስማዕ ወሲፋት” ቅጽ 2 ገጽ 150-151 አቡ ዑስማን አሷቡኒይ “ዓቂደቱሰለፍ” ገጽ 17-19፣
ኢብኑ አብድልበር “ተምሂድ” ቅጽ 7 ገጽ 151 ሌሎችም በስፋት ዘግበውታል።

ኢብኑ ሀጀርም በይሀቂይ ከ አብዱላህ ኢብኑ ዋህብ መልካም በሆነ ሰነድ እንደተዘገበ ጽፈዋል(ቅጽ 13፡ ገጽ 407)። ይህንን አሰር ዶክተር አብዱረዛቅ አልበድር “አልአሰር አልመሽሁር ዓኒል ኢማም ማሊክ ቢን አነስ” በተሠኘ ድንቅ ጽሁፍ ሰነዱንና መለዕክቱን አብራርተዋል። አል ኢማም አዘሀቢይ «ይህ ከኢማም ማሊክ የተገኘ ማጽደቅ “ኢስባት” ነው። ልክ እንደዚሁ ከማሊክ ሽይኽ ረቢዓህ ተዘግቧል። እንደዉም የአህሉሱና ሁሉ ንግግር ነው» ።]

____________
📙የአማኞች ጋሻ 📙

አድራሻችን ፡-

🔎 ቴሌግራም https://t.me/asmaewesifat

🔎 ፌስ ቡክ www.fb.com/asmaewesifat

Post a Comment

0 Comments