Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የበኒ ቀረይዟ ዘመቻ እና የአላህ ከዐርሽ በላይ መሆን!


የበኒ ቀረይዟ ዘመቻ እና የአላህ ከዐርሽ በላይ መሆን!

(ሐይደር ኸድር)

ከታሪክ ማህደራችን የምናኘው የጠራ ተፈጥሯዊ እምነት። 

ከታሪክ ገፆቻችን የተቀነጨበ…

በኒ ቁረይዛዎች በነብዩ ﷺ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ መልዕክተኛው እንዲያዝኑላቸው ተማፀኑ።

ነብዩም ﷺ በእነርሱ ላይ " ሰዕድ ቢን ሙዓዝ" ፍርድ ይሰጥባቸው ዘንድ ጠየቋቸው።

እነርሱም "ወደነዋል ተቀብለነዋል።" አሉ!

ሰዕድ በኸንደቅ ዘመቻ ቆስሎ ስለነበር በዚህ ዘመቻ አልመጣም ነበር። በአህያ ላይ አስቀምጠው ከመዲና አመጡት።

ሰዕድ በቦታው እንደደረሰም ቁረይዟዎች የእርሱን ፍርድ እንደሚጠባበቁ ተነገረው።

የፍርድ ውሳኔውን ሰዐድ ቢን አቢ ወቃስ ይተርክልናል፦

ሰዕድ በበኒ ቁረይዛህ ላይ የሚከተለውን ፍርድ አስተላለፈ፦

"ለጦር ሜዳ የበቁ ወንዶቻቸው እንዲገደሉ ፣ ሴትና ልጆቻቸው በምርኮነት እንዲያዙና ንብረታቸው እንዲከፋፈል ፈረደ። "

የአላህ መልዕክተኛም ﷺ ይህን ሲሰሙ እንዲህ አሉ፦

"በእርግጥም በእነርሱ ላይ በአላህ ፍርድ ፈርደሀል፣ በዚያ ከሰባት ሰማያት በላይ ሆኖ በሰጠበት ፍርድ።"¹

¹[ኢማሙ ነሳኢይ ((አስ’ሱነን አል ኩብራ)) (5906) የሐዲሡ ለፍዝ የሳቸው ነው፣
አል በዝዛር ((ሙስነድ አልበዝዛር)) (1091) ፣
ሐኪም ((ሙስተድረክ አል’ሐኪም)) (2/124) ፣
ሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር ሐዲሡን ሐሰን ብለውታል ((ሙዋፈቀቱ አል’ኹብር አል’ኸበር)) (2/439) ፣ ((አል’ሲልሲለቱ አስ’ሶሒሓ 2745 ይመልከቱ)) ላይ ዘግበውታል።]

ሰዕድ ማን እንደሆነ ግን አውቃችኃል?!

በሞቱ የአርረሕማን ዐርሽ የተንቀጠቀጠለት ታላቅ ሰሐቢይ ነው!

የአረሕማንንም ከዐርሽ በላይ መሆን በእርሱ ፍርድ ምክንያት ሌላ ተጨማሪ መረጃ ያገኘንበት።

መልዕክተኛው ﷺ የአላህን ከሰባት ሰማያት በላይ ከዐርሽ በላይ መሆኑን በግልፅና በማያሻማ ቃል ተናገሩ!

ወገኖቼ ሆይ! ከዚህ በኃላ ወዴት ነው የምትዞሩት? ???

Post a Comment

1 Comments