Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድ የእውቀቶች ቁንጮ


ተውሂድ የእውቀቶች ቁንጮ

ከኢትዮጵያዊው ሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚ (ረሂመሁላህ) ምርጥ ምክሮች የተጨለፈ

🍃 …… ተውሂድ አል-ዒባዳ (አምልኮትን የተመለከተው ተውሂድ) የተማረውንም ያልተማረውንም ሁሉንም የሚያሳስብ ጉዳይ ነው። ተውሂድ አልዒባዳን በማጣራት ማረጋገጥ "ከአላህ ውጭ በሀቅ የሚመለክ አምላክ የለም" የሚለውን ቃል ማረጋገጥ ነው። 

እስልምናን ማጥራት ነው። እስልምናህን፣ ኢማንህን ማጥራትህ ነውና ይህ ጉዳይ አሳሳቢ ነው። 

በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ጉብኝት ሳደርግ ትናንሽ የሆኑ ተማሪዎችን ጠየቅኳቸው፤ ለትልቁ ሽርክ የሚሆን ምሳሌ፣ ለትንሹ ሽርክም ምሳሌ እንዲሁም ለስውሩ ሺርክ የሚሆን ምሳሌ ሊነግሩኝ እንደምፈልግ ነገርኳቸው።

የስውሩ ሽርክና የትንሹ ሽርክ ልዩነትንም እንዲያስረዱኝ ጠየቅኳቸው።

ወደ ሀምሳ ከሚጠጉት ተማሪዎች አብዛኞቹ ትክክለኛውን ምላሽ አልሰጡም። ጥቂቶች ከገሚስ ያነሱት ናቸው የመለሱት። ይኸ አሳዛኝ ነው።

አሳዛኙ ገፅታም እኛ የምንኖረው በተውሂድ ሀገር፣ የዓለም ህዝብ ትኩረት በሆነችው ሀገር ነው።

ዓለም ሁሉ የዚህን ሀገር ማህበረሰብ የተውሂድና የአቂዳ ማህበረሰብ መሆኑን ነው የሚመለከተው። 

አንድ ሰው ከውጭ ሀገር ይመጣና ወዳንተ ይቀርባል። አንተ ግን ያልተማርክ ነህ። ይሁንና በሁኔታህ የተውሂድ ሀገር ነዋሪ ነህ። (እሱ የሚያስብህ አዋቂ አድርጎህ ነውና) ስለተውሂድ የሆነ ጥያቄ ሊጠይቅህ ይችላል። 

"ብዙውን ግዜ ከናንተ የምንሰማው ሺርክ ምንድነው ? ሽርክ፣ ሽርክ፣ ትንሹ ሽርክ፣ ትልቁ ሽርክ፣ ስውሩ ሽርክ የምትሉት ምንድነው ቢልህስ … ለሱ አዲስ ነውና።

ነገር ግን ባንተ ላይ ግዴታ የሚሆነው በእውቀት ላይ ሆነህ ምላሽ መስጠት ነው። ያልተማርክ እንኳን ብትሆን ይህንን ጉዳይ ልትረዳው ይገባል።

ምክንያቱም ይህ ጉዳይ ላልተማረውም ቢሆን 
ዑዝር የሚያሰጥጥ አይደለም።
(ኣለመማሩ ምክንያት ሆኖለት ከተጠያቂነት አያድነውም።) …🍃»

ከሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚ (ረሂመሁላህ) 

الشيخ محمد أمان الجامي
نصيحة طلاب العلم والعوام بتعلم التوحيد 
https://youtu.be/ndTEi2dcuvo

________

ይህ ገጠመኝ እንግዲህ የተውሂድም ሆነ የሱንና ትምህርት ተስፋፍቶባት ከዳር እስከዳር በተዳረሰባት ሀገር ነው። በኛ እና በመሳሰሉትስ ገና ጥሬ በሆነበት ሀገር ምን ያህል ለተውሂድ መቆም አለብን ?!»

ስለሆነም ስለ ተውሂድና ሱንና የሚያስተምሩትን ተከታተሉ፣ አክብሩ፣ ውደዱ፣ ስሟቸውም፣ አሰራጩትም

👆📖 ተማር አንቺም ተማሪ


© ተንቢሀት

🌱 ዙልሂጃ 07/12/1436
Sep 21/09/2015

Post a Comment

1 Comments