Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፎቶና መዘዙ


#ፎቶ ማንሳትም ይሁን መነሳት በመሰረቱ ከከባባድ (ከባኢር) #ወንጀሎችና ኣኺራ ላይም ከፍተኛ ቅጣትን ከሚያስከትሉ ነገሮች መካከል አንዱ ነው፣ከመሆኑም ጋር #በዘመናችን ብዙ ሰዎች #በሄዱበት ሁሉ ፎቶ እየተነሱ ሚዲያ ላይ መልቀቅ ስራቸው ሆኗል!
🔹አልፎ ሁሉ የአላህ ሐቅ የሆኑ ዒባዳዎች ሳይቀሩ ያለ ምክንያት ተቀርጸው ሚዲያ ላይ ይወጣሉ
ሐጅና ዑምራ እያደረጉ ፎቶ ተነስቶ መልቀቅ ምን ምክንያት አለው?!
🔸ለማስታወሻ ከሆነ ፎቶን ማስታወሻ ብሎ ማስቀመጥ ክልክል (ሐራም) ነው::
💥ሰው ሐጅ አድርግ ብሎ ልኮን ከሆነና ለማስረጃነት መነሳቱ የግድ ከሆነ ይፈቀዳል ቢባልም ሚዲያ ላይ ማውጣቱ ምንም ምክንያት የለውም!
🔹 ሐጅና ዑምራ ላይ መሆንን ለሰዎች ለማሳወቅ ከሆነ ደግሞ (ሪያእ) ነው ይህ ደግሞ ሺርክ ነው!
💥 አላህ ሒጃብ እንድታደርግና የወንዶች ዓይን እንዳያርፍባት ሸሪዓው አጥብቆ አደራ ያለንን ሴትን እንኳ ከዙሪያቸው አድርገው ሆን ብለው ፎቶ የተነሱ ሰዎችም በመኖራቸው ጉዳዩ ብዙዎችን ግራ እያጋባ ነውና የዲኑን ህግ እናክብር! አላዋቂዎችንም ግራ አናጋባ!
🔹አዋቂ ናቸው የሚባሉት በይፋ ሸሪዓን ሲጻረሩ ማየት ላላዋቂዎች ትልቅ ፈተና ነው!
አሕመድ ሼኽ ኣደም
18/12/1439ዓ.ሂ @ዛዱል መዓድ
🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐https://telegram.me/ahmedadem

Post a Comment

1 Comments