Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሰውነታችን ላይ ማስወገድ የሚፈቀደውና የሚከለከለው ፀጉር የቱ ነው?



ከሰውነታችን ላይ ማስወገድ የሚፈቀደውና የሚከለከለው ፀጉር የቱ ነው?
ሰውነት ላይ የሚወጣ ፀጉርን በተመለከተ ዐሊሞች ለ 3 ይከፍሉታል።

① ይወገዱ ዘንድ ሸሪዐዊ ትእዛዝ የመጣባቸው የፀጉር አይነቶች።:– ለምሳሌ 
– የብብት ፀጉር፣
– የብልት አካባቢ ፀጉር፣
– የቀድሞ ቀመስ ፀጉር (ማሳጠር)፣
– በሐጅ/ በዑምራ የእራስን ፀጉር መላጨት ወይም ማሳጠር

② መወገዳቸው የተከለከሉ የፀጉር አይነቶች። ለምሳሌ:–
– የቅንድብን ፀጉር ማስወገድ (ከከባባድ ወንጀሎች ነው)፣
– ፂምን መላጨት (በኢጅማዕ የተወገዘ ነው)

③ ክልከላም ይሁን ትእዛዝ ያልመጣባቸው የፀጉር አይነቶች። ለምሳሌ:–
– የክንድ ላይ ፀጉር፣
– የእግር / የጭን ላይ ፀጉር፣
– የደረት ፀጉር፣
– የአፍንጫ ፀጉር፣ ወዘተ
በነዚህ ላይ ዐሊሞች ተወዛግበዋል። ከፊሎቹ ተፈጥሮን ከመቀየር ጋር በማያያዝ ሲከለክሉ፣ ሌሎች ግን ሸሪዐው ዝም ስላለው መሰረቱ ፍቁድነት ነው ብለዋል። ይህም በፍቃድም ይሁን በክለከላ መልክ ሸሪዐው ያልገለፀው ነገር ባለበት የመተውም ይሁን የማስወገድ ምርጫ አለው ማለት ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
★ "ሐላል ማለት አላህ በመፅሐፉ የፈቀደው ነው።
★ ሐራም ማለት አላህ በመፅሐፉ የከለከለው ነው።
★ ከሱ ዝም ያለው የተተወ (ያልተከለከለ) ነው።" [ሶሒሕ አትቲርሚዚ]
ስለዚህ በማስወገድም ይሁን በመተው ቁርኣንና ሐዲሥ ላይ ያልተገለፁት አይነቶች ከሶስተኛ ምድብ ላይ ያርፋሉ ማለት ነው። እናም ባለበት የመተውም ይሁን የማስወገዱ ምርጫ ለባለቤቱ የተተወ ነው።
ይህንን አቋም በርካታ ዐሊሞች መርጠውታል። ለምሳሌ ያክል የሳዑዲ ዑለማዎች ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ (ለጅነተ አድዳኢማህ) "ለሴት የሰውነቷን ፀጉር ማስወገድ ብይኑ ምንድን ነው?" ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መልሰዋል:–
"ከቅንድብና ከእራስ ፀጉር ውጭ ያለውን ማስወገድ ይፈቀድላታል። እነዚህን ግን ልታስወግዳቸው አይፈቀድላትም። …" [ፈታዋ ለጅነት አድዳኢማህ: 5/194]
በተለይ ደግሞ ፀጉሩ ባልተለመደ መልኩ የወጣ ከሆነ ለምሳሌ የሴት ፂም ወይም ቀድሞ ቀመስ ገፅታዋን ስለሚያበላሽ ማስወገድ ትችላለች።

ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰበ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 02/2010)

Post a Comment

0 Comments