Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በተውሂደ ሩቡቢያ ብቻ ማመን ከአላህ ቅጣት አያድንም!



በተውሂደ ሩቡቢያ ብቻ ማመን ከአላህ ቅጣት አያድንም!

ተውሂዱ ሩቡቢያ ከሶስቱ የተውሂድ ክፍሎች አንዱ ይሁን እንጂ ብቻውን የተውሂድን መልዕክት ሙሉ ለሙሉ አያሟላም። እናም አንድ ሰው እምነቱ በተውሂዱ ሩቡቢያ ብቻ ከተገደበ ሙወሂድ አይሰኝም።

ለዚህ ማስረጃው በነቢዩ ﷺ ወቅትም ሆነ ከዛ በፊት የነበሩትን ሙሽሪኮች አላህ ፈጣሪ፣ ለጋሽ አስተናባሪ መሆኑን ያምኑም ይመሰክሩም ነበር ግና ይህ እምነታቸው ሙስሊም አላደረጋቸውም። ነፍሳቸውንም ከቅጣት አላዳነም።

ምክንያቱም በአላህ ሩቡቢያ ከማረጋገጣቸው ጋር ከአላህ ውጪ ሌሎችን ያመልኩ ነበርና ነው።አላህ እንዲህ ሲል በቁርኣን ነግሮናል፦

«ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይላሉ፡፡ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ፡፡»
[ዙኽሩፍ-87]

«ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡»
[አንከቡት-61 ]

አብደላህ ኢብኑ አባስ እንዲህ ብለዋል፦

«እምነታቸው (የአጋሪዎቹ) - ሰማይን፣ ምድርን፣ ተራሮችን የፈጠረው ማን ነው? ሲባሉ አላህ በማለት ነበር የሚመልሱት ሆኖም ግን ያጋራሉ»

የመካ አጋሪዎች የሚያመልኳቸው አማልክት እንደማይፈጥሩ ፣ እንደማይጎዱ ፣ እንደማይጠቅሙም ያምኑ ነበር። ነገር ግን አላህ ዘንድ ያቃርቡናል ወይም ያማልዱናል የሚላቸውን ሷሊሆች ፣ ወሊዮች ፣ ጣኦታት ሰይቀር ይለምኑ፣ ይሳሉ፣ ያርዱላቸው…፤ ባጠቃላይ እነርሱን ያመልኩ ነበር። ይህ ስራቸው ደግሞ ከነቢዩ ﷺ መልዕክት ጋር የማይጣጣም ነበርና ጀነት በነርሱ ላይ እርም ሆነች።

«እነዚያም ከእርሱ ሌላ (ጣዖታትን) ረዳቶች የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም» (ይላሉ)፡፡ አላህ በዚያ እነርሱ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ አላህ እርሱ ውሸታም ከሓዲ የኾነን ሰው አያቀናም»
[ ዙመር-4]

‪#‎እምነትህን_ጠብቅ‬

የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት
https://m.facebook.com/emnetihintebiq