Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‎መፈተኛይቱ አንቀጽ




«አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኋልና ኃጢያቶቻችሁን ለእናንተ ይምራልና ፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነው። በላቸው፡፡ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» (አል ዒምራን 31-32)
ታላቁ የቁርዓን ሙፈሲር ኢብኑ ከሲር ይህንን አንቀጽ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፤
«ይህ አንቀጽ ‘አላህን እወዳለሁ’ እያለ ነገር ግን ነብያዊ ፈለግን እና ዲንን በማይተገብር ማንኛውም ሰው ላይ ፈራጅ ነው።በትክክለኛ ሀዲስ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፤:-
“የኛ ትዕዛዝ የሌለበትንማንኛውንም ስራ የሰራ ሰው ስራው ወደራሱ ይመለሳል (ተቀባይነት አይኖረዉም)”
ስለዚህም፤ በማንኛውም ንግግሩ እና ሁኔታው የነብዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ፈለግ እና ዲን ሊከተል ይገባዋል።»
[ተፍሲር ኢብኑ ከሲር ገጽ 237 (ዳሩሰላም እትም)]
ስለዚህም፤ አላህን እና ነብያችንን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሚወድ ሰው ለትእዛዛቸው ማደር ይኖርበታል። አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና አል-ኢማም ሐሰን አል በስሪ እና ሌሎችም ኡለማዎች፤ ይህ አንቀጽ ከተግባር የራቁ ሆነው ነብዩን እንወዳለን እያሉ የሚሞግቱ ሰዎችን አላህ የፈተነበት አንቀጽ መሆኑን ገልጸዋል። ስለዚህ፤ ይህ አንቀጽ እውተኛ ዉዴታን ከሀሰተኛ ዉዴታ የሚለይ ወሳኝ መመዘኛ ነው። ማንኛውም ሰው ለአላህ እና ለመልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ያለዉን ውዴታ ሊገመግምበት ይገባል። ነቢዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መከተል የዉዴታችን መለኪያ ስለሆነ በዲን ጉዳይ ላይ እርሳቸው የሰሩትን በመስራትና የተዉትንም በመተው ውዴታችንን በተግባር ማረጋገጥ ይጠበቅብናል።
አላህ እውነተኛ የረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወዳጅ ያድርገን። አላሁመ አሚን !!!
መሰረታዊ የተውሂድ ዕውቀትን መማር የሚፈልግ ሁሉ like ሊያደርገው የሚገባ ፔጅ
--------------------------------------
Haider Khedir

Post a Comment

1 Comments