ፆመኛ ሆኖ ምራቅን መዋጥ
ምራቅን መዋጥ ፆምን የሚያበላሽ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ቦታ ከተቀመጡ አካባቢያቸውን ምራቅ በምራቅ ሲያደርጉት ያጋጥማል፡፡ ምራቅ ፆም ያበላሻልን?
1. መደበኛ ወይም ከወትሮው ያልበዛ ከሆነ
ከተለመደው ያልተጋነነ ምራቅ ከአፍ አውጥተው ካልመለሱት በስተቀር ባለበት ሁኔታ ቢዋጥ ፆም እንደማያበላሽ ኢብኑ ሐዝምና ነወዊ #ኢጅማዕ ጠቅሰዋል፡፡
2. ታስቦበት ባልሆነ መንገድ ከበዛና ከተጠራቀመስ?
ሆን ብለን ሳናጠራቅመው እንዲሁ ወሬ ስናወራ ወይም ቁርኣን ስንቀራ፣… ምራቃችን ሊበዛ ይችላል፡፡ ይህንንስ የዋጠ ፆሙ ይበላሻል? ነወዊ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ሳይታሰብበት ብዙ ምራቅ ቢጠራቀም፣ ለምሳሌ ንግግሩ በመብዛቱና መሰል ሰበብ የተነሳ ሆን ብሎ ሳያደርገው ቢበዛና ቢውጠው (በሻፍዒያ መዝሀብ) ያለ ልዩነት ፆሙ አልተበላሸም፡፡” ይሄ የብዙ ዑለማዎች አቋም ነው፡፡
3. ታስቦበት ከተጠራቀመስ?
አንድ ሰው ስራየ ብሎ ምራቁን ካጠራቀመ በኋላ ቢወጠው ፆሙ ይበላሻል ወይስ አይበላሸም በሚለው ላይ ውዝግብ አለበት፡፡ በሻፍዒያ መዝሀብ ትክክለኛው አቋም ሐንበልያም ዘንድ እንዲሁ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለው ነው፡፡ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚንም ረሒመሁላህ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለውን መርጠዋል፡፡ ሆኖም ግን እራስን ከውዝግብ ማራቅ ተገቢ ነውና መጠንቀቁ ሰላማዊ ምርጫ ነው፡፡
አክታን መዋጥስ?
4. ከአቅም በላይ ከሆነ
ማስወገድ በማይችለው መልኩ ከጭንቅላቱ ቀጥታ ወደታች የሚወርድ አክታ ከሆነ ሊጠነቀቀው አይችልም፡፡ አላህ ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ነገር አይዝም፡፡
5. መቆጣጠር ሲቻል ቢዋጥስ?
ነገር ግን ስራዬ ብሎ አውጥቶ አፉ ጋር ካደረሰው በኋላ መትፋት ሲችል ቢውጠው ፆሙ ይበላሻል ያሉ ዐሊሞች አሉ፡፡ ከፊሎቹ ግን ይህም ቢሆን አይበላሽም ብለዋል፡፡ ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን ረሒመሁላህ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለውን መርጠዋል፡፡ ታዲያ “ፆሙ አያበላሽም” ይበሉ እንጂ ድርጊቱ ፆመኛ ለሆነም ይሁን ላልሆነ ነው ሐራም እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ አንደኛ አፀያፊ ነው፡፡ ሁለተኛ ምናልባትም በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን የተሸከመ ሊሆን ስለሚችል ወደ ሆድ ሲገባ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚል ነው፡፡ [ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 6/428] እራስን ከውዝግብ ለማራቅ ሲባል መራቁም እራሱን የቻለ ዋጋ አለው፡፡ ወልላሁ አዕለም፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 14/2010)

0 Comments