Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በረመዳን ወር ቀን ላይ ከወር አበባ ደም የጠራች ሴት ቀሪውን የቀኑን ክፍል ከሚያስፈጥር ነገር የመቆጠብ ግዴታ አለባትን?




በረመዳን ወር ቀን ላይ ከወር አበባ ደም የጠራች ሴት ቀሪውን የቀኑን ክፍል ከሚያስፈጥር ነገር የመቆጠብ ግዴታ አለባትን?
አንዲት ሴት የወር አበባ ደም ላይ በመሆኗ ሳትፆም ቀርታ ቀን ላይ ከደሙ ብትጠራ ከምግብና ከመጠጥ የመቆጠብ ግዴታ እንዳለባት የሚያስቡ ብዙ ናቸው፡፡ በርግጥም ይህን አቋም የመረጡ ዐሊሞች አሉ፡፡ ነገር ግን ይሄ አቋምለቀኑ ክብርበሚል ወይም ጤነኛ ያልሆነን ቂያስ በመጠቀምና መሰል ምክንያት እንጂ ቀጥተኛ ማስረጃ የሚደግፈው አይደለም፡፡ ፆመኛ ያልሆነን ሰውባንተ ላይ መመገብና መጠጣት ሐራም ነው፤ ያለበለዚያ ወንጀለኛ ነህማለት ግልፅ ማስረጃ ይፈልጋል፡፡
ለምሳሌ አንዲት ሙስሊማ የወር አበባ ደም ካየች በሷ ላይ ፆም መፆም ሐራም ነው፡፡ መፆም በሷ ላይ ሐራም የሆነባትን ሴትመመገብም ባንቺ ላይ ሐራም ነውማለት ትክክል አይደለም፡፡መብላት የለባትምከተባለ ግን እራት ከበላችበት ሰዓት ጀምሮ ወይም ልክ እንደ ፆመኛ ሌሊት ተነስታ ሱሑር ከበላችበት ሰዓት ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ያለምግብና ያለውሃ መቆየት አለባት ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ኋላ ቀዷ ማውጣቷ የማይቀር ከመሆኑ ጋር ነው፡፡ ይሄ እይታ ትክክል እንዳልሆነ በርካታ ዑለማዎች ገልፀዋል፡፡
ሶሐባው ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “በቀኑ መጀመሪያ ላይ የበላ ሰው በመጨረሻውም ይብላ፡፡
ይህ ምን ማለት ነው? በሆነ ምክንያት ፆመኛ ባለመሆኑ ሳቢያ በቀኑ የመጀመሪያ ክፍል ላይ መመገብ የተፈቀደለት ሰው በየትኛውም የቀኑ ክፍል መመገብ እንደሚችል የሚጠቁም ነው፡፡ ይህ አቋም የታቢዒዮቹ ጃቢር ኢብኑ ዘይድና አጧዕ ኢብን አቢ ረባሕ፣ የኢማሙ ማሊክ፣ የሻፍዒይ፣ የአሕመድ በአንድ ዘገባ፣ የኢብኑ ሐዝም፣ የኢብኑ ዑሠይሚን እና የሌሎችም የብዙሃን ዑለማእ እይታ ነው፡፡
ይህ እንግዲህ በረመዳን ወር በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከወሊድ ደም የጠራችን፣ ከህመሙ ያገገመን፣ ከመንገድ የተመለሰንና መሰል ሸሪዐ ዑዝር ያላቸውንም ጭምር የሚመለከት ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
የሚያፈጥርበት ምክንያት ለሰዎች የሚሰወር የሆነ ሰው ሲመገብም ሆነ ሲጠጣ በተቻለ ከሰዎች እይታ ቢርቅ በዲኑ በክፉ ከመጠርጠር ይረዳዋል፡፡ ዑዝሩ ወይም ሰበቡ በውል የሚታወቅ ከሆነ ግን በግልፅም ቢመገብና ቢጠጣ ችግር የለውም፡፡ ወልላሁ አዕለም
(
ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 13/2010)

Post a Comment

0 Comments