የሚሰራውን መልካም ነገር አስተውሎ ለሚተገብር ሰው የኸይር በር ሠፊ ነው። እንደሚታወቀው አብዛኛው የኸይር ስራ ግዜ አይወስድ፣ ድካም የለው፣ ወጪም የለበትም። በተለይ ምንም አይነት ተግባር ከመፈፀማችን በፊት ኒያ የተሰኘቿን ዋነኛዋን የዓላማ ሞተር ካቀናናት በትንሽ ወጪ በርካታ ገቢዎችን እናካብታለን።
የአላህ መልእክተኛ የአላህ ውዳሴና ሠላም በሳቸው ላይ ይስፈንና ስለ ኒያ የተናገሩትን ዑመር ኢብነል ኸጣብ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና ሰምተው እንዳስተላለፉልን
” إِنَّمَا الأعْمَالُ بِالنِّيَّاتِ وَإِنَّمَا لِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى “
“ተግባራት በሙሉ በልብ በሚያድረው ፍላጎት መሰረት ነው የሚታዩት። እያንዳንዱ ግለሰብም ያሰበው ኣለለት።” ባሉት መሰረት ለምንፈፅመው ነገር ኒያችን ወሳኝ ሚና ኣለው።
የመስገዳችን አላማ፣ የመፆማችን አላማ፣ ዘካ ሆነ ሌላ ሰደቃ የመስጠታችን አላማ፣ ሐጅና ዑምራ የማድረጋችን
አላማ፣ ዳዕዋ ሆነ የማስተማራችን አላማ፣ ሌላው ሌላው ሁሉ በልባችን በምንመሰጥረው ፍላጎት መሰረት ነው የሚዳኘው።
ስለዚህም ይህንን ፍላጎት ማሳመርና ማስፋት ለስራችን ማማር ብሎም ተቀባይነት ማግኘትና ለአጅራችን መብዛት ወሳኝ
ነው። በዚህ መልኩ የምንተገብረው ትንሽ ነገር በራሳችንም ሆነ በዙሪያችን ላይ ከፍተኛ የሆነ መልካም ተፅዕኖ
ይፈጥራል።
ኒያችንን እንዴት ነው የምናሳምረው ወይም የምናሰፋው የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላልና ይህንኑ በመዲና ከሚገኙ ስመ-ጥር ምሁራንና በታላቁ መስጂድ ውስጥ ተከታታይ ትምህርት ከሚለግሱ ታታሪ ዑለሞች አንዱ የሆኑት ሸይኽ ዶክተር ሷሊህ ሲንዲ ሀፊዘሁላህ፤ ይህንኑ ቀለል ባለ መንገድ ከነምሳሌው ሲያስረዱን እንዲህ ይላሉ☞
«እዚህጋ ታላቅና የተከበረች በር አለች። ያቺን በር ጉጉቱ ከፍ ያለና የሰረፀ እውቀት ያካበተ እውነተኛ የሆነ ኸይር ፈላጊ እንጂ ሌላው አያስባትም።
ነገሩ እንዲህ ነው፤ አንድ ግለሰብ ወደ መልካም ስራ ይገባል። በልቡም ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ዓላማን ያቅድበታል። ከዚያም ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ዒባዳዎችን አሳክቶበት ይወጣል ማለት ነው።
እንደ ምሳሌነት ለመጥቀስ አንድ ሰው ሰላትን በጀማዓ ለመስገድ አስቦ መስጂድ ይሄዳል። በዚያው አጋጣሚ መስጂድ በመቀመጡ መላኢካዎች ከአላህ ምህረትን እንደሚለምኑለት ያስባል።
እንዲሁም ሃራም የሆነበትን ነገር ከመመልከት ዓይኑን ያቅብና ሰዎችንም ከማስቸገር ይቆጠባል። በዚያው አጋጣሚ ሃሜት ላይ ከመዘፈቅም አንደበቱን ይጠብቃል።
አስተውል እንግዲህ እነዚህ ሶስት ኒያዎች ናቸው። ሰውየው ከዚህም በላይ ሊያስብ ይችላል። ታዲያ ይህ ሰው በኣኺራ ተግባራት ላይ ጮሌ በመሆኑ ለአንድ ዒባዳ ገብቶ በበርካታ ዒባዳዎች ይወጣል።»
شرح كتاب التوحيد ص ٧٧٤
አላህ ይጠብቃቸውና መልእክቱ በሸይኽ ዶክተር ሷሊህ ሲንዲ የተነገረ ሲሆን፤ በነቢዩ አለይሂ አሰላቱ ወሰላም መስጂድ ውስጥ ሆነው ከሚያስተምሩበት የኪታቡ ተውሂድ ትንታኔ ገፅ 774 የተወሰደ ነው።
ا═•═📚═•═ا
በአረብኛ ከሚሰጡት ትንታኔዎች አጫጭር ፅሁፎችና ሙሉ የድምፅ መልእክቶች እንዲደርስዎት ከፈለጉ በቀጣዩ ማስፈንጠሪያ ከቴሌግራም አምዱ ይቀላቀሉ። ☞
قناة فوائد الشيخ أ.د.صالح سندي. t.me/Drsalehs
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
Abufewzan
ረመዳን 2/1439
18/05/18

0 Comments