⭕ችግሮቻችን ⭕
🔸ሰው እንደመሆናችን ሁላችንም ብዙ ችግሮችና ጉድለቶች ይኖሩብናል፣ ብዙዎቻችን ዘንድ ጎልተው በተደጋጋሚ ከሚታዩት መካከል:-
① የራሳችንን መቸገር እንጂ የሌሎችን ችግር ልብ አለማለትና ራስ ወዳድነት፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሰው ቶሎ እመልሳለሁ ብለው የተበደሩትን ብር ወይም አደራ የተቀመጠባቸውን ገንዘብ አጥፍተው ባለ ገንዘቡ ሃቁን ሲጠይቅ "አሁን ችግር ላይ ነኝ ሳገኝ እሰጥሀለሁ ታገስ" የሚሉ ራስ ወዳዶችን በብዛት እንያለን
② የራሳችንን መቀየር (መበላሸት) ዘንግተነው በእኛው ሁኔታ መቀያየር ምክንያት ግራ ተጋብተው ባህሪያቸው የተቀየረብን/ ቀዝቀዝ ያሉብን ሰዎችን እንወቅሳለን! መኩራት ጀመረ/ች ተቀየረ/ች ወዘተ ብለን በልባችን ከማሰብና ከሌሎችም ጋር ሆነን ከማማታችን ይልቅ :-
~"ለምን ይሆን የተቀየረው/ችው?"
እያልን መንስኤውን እንፈልግ!
~እራሳችንም እንፈትሽ!
③ ከሀሜተኛ ወይም ሸረኛ ሰው የሰማነውን መሰረተ-ቢስ ወሬ ተመርኩዘን ሰዎችን መጥላትና ቂም መያዝ፥ እጅግ በጣም ብዙ ወዳጆችን ያለያየ፣ ዘመዶችን ያቆራረጠ፣ በርካታ ትዳሮችንም ያፈረሰና ልቦችን ሰላም የነሳ ችግር ነውና ልባችን እናጽዳ ወሬ ስንሰማም ቀድመን እናጣራ አርቀንና አስፍተንም እናስብ

✍ አሕመድ ሼኽ ኣደም 17/7/1439ዓ.ሂ@ዛዱል መዓድ
🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
0 Comments