Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሴት ልጆች አባት ሆይ ተበሰር

 بشرى لأبو البنات 
 የሴት ልጆች አባት ሆይ ተበሰር 

┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅┄┅
~~~~~~~~~~~ قال الله تعالى:- ~~~~~~~~

((٤٢:٤٩)) لِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ يَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ إِنَاثاً وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ
((٤٢:٥٠)) أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَاناً وَإِنَاثاً
وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيماً
إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ

( الشورى : 49 - 50 )
====> አምላካችን አላህ እንዲህ ይለናል:-

((42:49)) "የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡"
======
((42:50)) "ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መሃን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡"
=====> (አሽሹራ 49 - 50)

⊙) ልጆች የዐይን ማረፍያ ፣ የልብ መርጊያ ፣ ምትክ ዘሮች ናቸው። የአላህን መንገድ አመላክቷቸው በኢስላም ላነፃቸው በዱንያም ሆነ በአኼራ መኩሪያውና መከበሪያው ይሆናሉ ፤ ደረጃውንም ያልቁታል። አጀሉ ደርሶ ዱንያን ቢሰናበትም በሰናይ ተግባራቸው ይጣቀማል።
(إذا مات الإنسان انقطع عمله إلا من ثلاث ... أو ولد صالح يدعو له)
" አንድ ሰው ሲሞት ሦስት ነገሮች ብቻ ሲቀሩ ስራው ሁሉ ይቋረጣል ፤ ከነዚህ መሃከል… ዱዓ የሚያደርግለት ደግ ልጅ ነው"

⊙) በጀነትም የላቁ ፀጋዎችን በነሱ ምክንያት ያገኛል። 
قال عليه الصلاة والسلام: (إن الرجل لترفع درجته في الجنة فيقول: أنى هذا؟ فيقال: باستغفار ولدك لك)
" አንድ ሰው በጀነት ውስጥ ደረጃው ከፍ ያለ ግዜ ፤ ምክንያቱን ሲጠይቅ ይህ መልካም ልጅህ ባደረገልህ ኢስቲግፋር ምክንያት ነው " ይባላል። 
(⊙) በተለይም ሴት ልጆችን በተርቢያ ማሳደጉ ፤ መስመር ሳይስቱ ሳይሆኑም ገልቱ ለቁም ነገር ማድረሱ ልፋትና ክብደቱ እሙን ነው። በመሆኑም አላህ ረድቶት ለዚህ እርከን የበቃ ወላጅ የምስራች! !

فقال النبي صلى الله عليه وسلم: (من ابتلي من هذه البنات بشيء فأحسن إليهن كن له ستراً من النار)رواه البخاري.
" በነዚህ ሴት ልጆች ተፈትኖ ወደነሱ ካሳመረ፤ ከእሳት መከላከያ ይሆኑለታል"

⊙)ልብ በል አላዋቂው ማ/ሰብ የሴት ልጅ መወለድን እንደ ክፋት ስለሚያየው ፣ እይታውም ግርድፍ በመሆኑ የተከበሩት መልዕክተኛ ይህን ሰንካላ አመለካከት በመስበር ፤ እንዲሁም ለነሱ ከወጪ አንፃር አቅም የቻለውን ማድረግና እዝነትና ርህራሄን መላበስ ስለሚያስፈልግ ከላይ የጠቀስነውን ሃዲስ ተናግረዋል።
⊙) ~~ ሴት ልጆችን ለአካለ መጠን እስኪደርሱ በአግባቡ ያሳደገ ሰው ይበሰር!
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: (من عال جاريتين حتى تبلغا جاء يوم القيامة أنا وهو) 
" ሁለት ሴት ልጆችን ለአካለ መጠን እስኪበቁ ( በአግባቡ) ያሳደገ እኔ እና እሱ በጀነት እንዲህ ነን ( ሁለት ጣቶቻቸውን በማቆራኘት) " ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ።

⊙) ነብያችን ( صلى الله عليه وسلم) ለሴት ልጅ ልዩ ቦታን ይሰጣሉ ፤ በዚህ ረገድ የሚንፀባረቁ አጓጉል አስተሳሰቦችንም ይዋጋሉ። የልጃቸውን የዘይነብን ሴት ልጅ ኡማማን ተሸክመው ይሰግዳሉ። እንዲሁም በአረማመዷ ቁጭ እሳቸውን የሆነችው ልጃቸው ፋጢማን ቆመው (مرحباً يابنتي)
" እንኳን ደህና መጣሽ ልጄ" በማለት ይቀበሏታል።

اللهم أعنا على تربية أبنائنا وبناتنا، اللهم إنا نسألك أن تهب لنا من أزواجنا وذرياتنا قرة أعين، وأن تجعلنا للمتقين إماماً ••• اللهم امين!
Al ilmu Nurun !

Post a Comment

0 Comments