Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን?


ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን?
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይዊ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:–
"የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል። ከሶስት ሲቀር።
① ቀጣይነት ያለው ሶደቃ፣
② ወይም ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣
③ ወይ ደግሞ ዱዓ የሚያደርግለት ጥሩ ልጅ።" [ሙስሊም]
የቱ ጋር አለህ? የቱ ጋር አለሽ?
① ከቻልን ህዝብ የሚጠቅም ሶደቃ ጥለን እንለፍ።
② ወይ ደግሞ ወይ አውቀን እናሳውቅ። ወይ የዑለማዎችን እውቀት እናስራጭ።
③ ልጆቻችንን ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ኮትኩተን እናሳድግ። ከሁሉም አለመኖር ግን አሳዛኝ ብክነት ነው።

Ibnu Munewor

Post a Comment

0 Comments