*🍃እናት ሆይ ልጅሽን በስርዓቱ አጥቢ🍃*
ህጻናት ማጥባት ወላጆቻቸው ላይ ካላቸው ሐቅ መካከል አንዱና የመጀመሪያው ነው!
ለዚህም ጌታችን አላህ የሚከተለውን ብሏል፥
{"والوالدات يرضعن أولادهن حولين كاملين لمن أراد أن يتم الرضاعة وعلى المولود له رزقهن وكسوتهن بالمعروف..."} البقرة {233}
📖 {"እናቶች ልጆቻቸውን ለሁለት ሙሉ ዓመታት ያጥቡ ይህም የተሟላ ጥቢን ማጥባት ለሚፈልግ ሰው ነው
ልጅ የተወለደለት አባትም ለአጥቢዎች የሚያስፈልጋቸውን ልብስና ምግብ እንደ አቅሙና እንደተለመደው የማቅረብ ግዴታ አለበት..."} አል-በቀራ 233

🔸ብዙ የዘመናችን እናቶች በተለያዩ ምክንያቶች ልጆቻቸውን በተገቢው መልኩ ማጥባትን ትተው በላምና በዱቄት ወተቶች ሲያሳድጉ ይታያል። አብዛኛውን ጊዜም እንደምክንያት የሚቀርበው ስራ ነው!
ለዚህም ምላሽ አባት አጥቢዋን እንዲንከባከብ አላህ አዞታል። አንዳንዶቹ ደግሞ ከአጉል ዘመናዊነትና ከእናትነት ርህራሄ መጉደል በስተቀር ምንም ምክንያት የላቸውም፣
ለዙረት ወይም ለእንቅልፍ ብለው ማጥባትን የሚተውም ጥቂቶች አይደሉም! ሌላ ጊዜ ደግሞ ማጥባት እናትን ይጎዳል ሲባልም እንሰማለን!
እውነትም ጎጂ ቢሆን አላህ ለሁለት ዓመት አጥቡ ብሎ ባላዘዘ (ባልመከረ) ነበር❗
ይልቁንም ህጻናትን በስርዓቱ ማጥባት ለአጥቢዋም ለሚጠባው ህጻንም በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት

ከነዚህም መካከል፥
①የእናት ወተት ለህጻናት እድገትና የአካል እንዲሁም የአጥንት ጥንካሬ ዋነኛና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ምግብ ነው
①የእናት ወተት ለህጻናት እድገትና የአካል እንዲሁም የአጥንት ጥንካሬ ዋነኛና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ምግብ ነው
②የተለያዩ በሽታዎችንም ይከላከላል
③ለህጻናት ጨጓራ የማይከብድና በቀላሉ ሰውነታቸው ውስጥ የሚስራጭ ምግብ ነው
④ ከእናት ወተት ውጭ ለህጻናት ከሚሰጡ ወተትና ምግቦች ጋር አብረው ሊኖሩ ከሚችሉ ለህጻናት ጎጂ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ የጠራና ምንም ዓይነት በሽታና ጉዳትን የማያስከትል ተመጣጣኝና ተሰማሚ የሆነ ምግብ ነው
⑤ በአላህ ፈቃድ የጡት ካንሰርን ጨምሮ የተለያዩ የካንሰር ዓይነቶች ይከላከላል
⑥ማህጸን እና ሌሎችም በወሊድ ጊዜ የተዛቡና የተጎዱ የሰውነት አካላት ወደ ቀድሞ ስራና ሁኔታቸው በመመለስ ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል
⑦የእናትና ልጅ ትስስርና ቀረቤታ ይበልጥ እንዲጠነክር በማድረግ ልጅ ከእናቱ ሙሉ ክብካቤ፣ ርህራሄና ፍቅር እንዲያገኝ በማድረግ አልፎ አልፎ በሞግዚቶች በኩል የሚደርሱበትን በደሎችም ያስቀራል ወይም ይቀንሳል
⑧ብዙ ሳይለፉና ወጪ ሳይጠይቅ ሁሉም እናቶች በቀላሉ ለልጃቸው ሊሰጡት የሚችሉት ምግብ ነው
(አላህ ለሀብታሙም ለድሃውም ያበረከተው ልዩ ስጦታ ነው!)
🔸ሌሎችም በርካታ ጠቀሜታዎች አሉትና እናት ሆይ፥ ልጅሽን በስርዓቱ አጥቢ በተለይ የመጀመሪያ ዓመቱ ላይ!
(አላህ ለሀብታሙም ለድሃውም ያበረከተው ልዩ ስጦታ ነው!)
🔸ሌሎችም በርካታ ጠቀሜታዎች አሉትና እናት ሆይ፥ ልጅሽን በስርዓቱ አጥቢ በተለይ የመጀመሪያ ዓመቱ ላይ!
✨ኃይማኖቴን ሙሉና ድንቅ የሆነው "ኢስላም' መመሪያዬን ተዓምራዊው "ቁርኣን" ያደረገልኝ ጌታዬ አላህ የላቀ ምስጋና እና ውዳሴ ይገባው الحمد
لله
✍በኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
እሁድ 29/7/1439 ዓ .ሂ @ዛዱል መዓድ
🔸 🔹 🔸 🔹 🔸
እሁድ 29/7/1439 ዓ .ሂ @ዛዱል መዓድ
🔸 🔹 🔸 🔹 🔸
0 Comments